1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የለገጣፎ እና የለገዳዲ ገበሪዎች ስሞታ

ዓርብ፣ መስከረም 25 2005

በኦሮምያ ክልል አዲስ አበባ ዙርያ የሚገኙ ለገጣፎ እና ለገዳዲ በተሰኙ የገጠር ቀበሌ ማህበራት ጤፍ እና ሌሎች ሰብሎችን እያመረቱ ይተዳደሩ የነበሩ ገበሪዎች፤ መሪታቸዉን ተመጣጣኝ ባልሆነ ካሳ አልያም ካሳ ሳይከፈላቸዉ ከቦታዉ ተፈናቅለዉ

ምስል DW

በኦሮምያ ክልል አዲስ አበባ ዙርያ የሚገኙ ለገጣፎ እና ለገዳዲ በተሰኙ የገጠር ቀበሌ ማህበራት ጤፍ እና ሌሎች ሰብሎችን እያመረቱ ይተዳደሩ የነበሩ ገበሪዎች፤ መሪታቸዉን ተመጣጣኝ ባልሆነ ካሳ አልያም ካሳ ሳይከፈላቸዉ ከቦታዉ ተፈናቅለዉ ችግር ላይ መዉደቃቸዉ ተሰምቶአል። ገበሪዎቹ ወደ ሚመለከተዉ ክፍል ሄደዉ አቤት ቢሉም መልስ ማጣታቸዉ ተነግሮአል።  በአካባቢዉ የሚገኙ አንድ ሽ ያህል ገበሪዎች የፊርማ ድጋፍ ማሰባሰብ ስሞታቸዉን ለዉጭ መገናኛ ብዙሃን ማስተወቃቸዉ ተገልጾአል። በሐምሌ ወር 1998 ዓ,ም ለገጣፎ እና ለገዳዲ የተሰኙት የኦሮምያ ገጠር ቀበሌ ማህበራት በከተማነት መቆርቆራቸዉን ወኪላችን ዮሃንስ ገ/ እግዚአብሄር የላከልን ዘገባ ያመለክታል።


ዮሃንስ ገ/ እግዚአብሄር
አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሃመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW