የለጋሽ ድርጅቶች ዕርዳታ መቀነስ በጋምቤላ በሚገኙ ስደተኞች ላይ ያደረሰው ተጽዕኖ
ቅዳሜ፣ ነሐሴ 3 2017
ድንበር የለሽ የሀኪሞች ቡድን የተባለው የግብረ ሰናይ ድርጅት የእርዳ መቋረጥ በጋምቤላ ክልል በሚገኙ የስደተኞችን አኗኗር ፈጣኝ እያደረገ ነው ሲል አመልክተዋል፡፡ ቁልፍ የተባሉ እንደ ዩኤስ፣አይ.ድ ያሉ ለጋሽ ድርጅቶች እርዳታ መቋረጥ በጤና፣ትምህርት እና በሽታ መከላከል እያዳከመ መሆኑን ጠቅሶ በዚህም 80ሺየሚደርሱ ህጻናት ለተመጣጠነ የምግብ እጥረት መጋለጣቸውን አመልክተዋል፡፡የስዴተኞች እና ተመላሾች አገልግሎት በበኩሉ ያጋጠሙ ችግሮችን ለመቅረፍ ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ተገቢውን ድጋፍ ማድረግ እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡
በ4 ካምፕች 80ሺ የሚደርሱ ከ5 ዓመት በታች ህጻናት ለምግብ እጥረት ተጋልጠዋል
በጋምቤላ ክልል ከ395ሺ በላይ ስደተኞች በ7 የተለያዩ ጣቢዎች እንደሚገኙ የገለጸው የድንበር የለሽ የሀኪሞች ቡድን ኩሌ በተባለው አንዱ ስደተኞች ጣቢያ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ አመልክተዋል፡፡ ድርጅቱ ከሁለት ቀን በፊት ባወጣው ዘገባም የዓለማ አቀፍ ድርጅቶች እርዳታ መቋረጥና እና መቀነስ በስደተኞች ላይ በተለያዩ ዘርፍ ጫና እያሳደረ እንደሚገኝ አብራርተዋል፡፡
ሶስት ስደተኞችን ምስክረነትን ጠቅሶ ደርጅቱ እንዳመለከተው ሰብአዊ ድጋፍ መቀነሱ ስደተኞችን ኑሮ ፈታኝ ማድረጉ እና ለህክምና እርዳታ ከአንዱ ጣቢያ ረጅም ርቀት በመጓዝ ኩሌ በተባለው ጣቢያ እርዳታ እያገኙ እንደሚገኙ አስታውቀዋል፡፡ ከዚህ ቀደም አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ስፍራውን መልቀቃቸውን ተከትሎ በጤናው ዘርፍ የሚስተዋለውን ክፈተት ከፍተኛ መሆኑን ዘገባው አመልክተዋል፡፡
በኢትየጵያ ከ1.1 ሚሊዩን በላይ ስደተኞችን ተመዝግቦ እንደሚገኙ ያስታወቀው የስደተኞች እና ተመላሾች አገልግሎትም የተስተዋሉ ከፍተቶችን ለመቅረፍ ዓለም አቀፍ ማህበረሰቡ ተገቢውን ድጋፍ መስጠት እንዳለበት አመልክተዋል፡፡ የስደተኞችና ተመላሾች ምክትል ዳይሬክተር አቶ ሙሉዓለም ደስታ ለጋሽ ድርጅቶች በተለይም አብዛኛውን ሰብአዊ ድጋፍ የሚሰጡ እንደ ዩኤስ. ኤድ ያሉ ድርጅቶች እርዳታ መቀነስ በጤና እና ትምህርት ላይ ተጽህኖ ማሳደሩን አቶ ሙሉዓለም ጠቁመዋል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞም በጤና እና ትምህርት ላይ እያደረሰ ያለውን ተጽህኖ አብራርተዋል፡፡
በጋምቤላ አዲስ የስደተኞች ጣቢያ እየተቋቋመ ነው
ሀገርቷ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ስደተኞችን እያስተናገደች እንደሚትገኝ በመግለጽ ዓለም አቀፍ ማህሰረብ እና ተቋማት ተገቢውን ድጋፍ ማድረግ አለባቸው ብሏል፡፡ ከዚህ ቀደም ድጋፍ ለማድረግ ቃል ከገቡት መካከልም ሁለት ሀገሮች ኔዘርላንድ እና ጀርመን ድጋፍ ማድረጋቸውንም ጠቁመዋል፡፡
በደቡብ ጎንደር ዞን በድርቅ ምክንያት ከ175ሺህ በላይ ሠዎች እርዳታ ይፈልጋሉ
በጋምቤላ ክልል ከሚገኙት 7 የስደተኞች ጣቢዎች በተጨማርም በቅርቡ ከደቡብ ሱዳን ወደ ኢትዮጵያ የሚሻገሩ ስደተኞች ቁጥር መጨመርን ተከትሎ አዲስ የስደተኞች ጣቢያ እየተቋቋመ እንደሚገኝ አቶ ሙላለም ደስታ አመልክተዋል፡፡
የድንበር የለሽ ሀኪሞች ቡድን በስደተኞች ካምፕ አስፈላጊ የሆኑ የጤና አገልግሎቶችን እየሰጠ እንደሚገኝ የገለጸ ሲሆን ከሌሎች ተዋናዮች አስቸኳይ ድጋፍና ጣልቃ ገብነት ካልተገኘ ቀውሱ ተባብሶ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ህይወት የበለጠ
አደጋ ላይ ሊጥል ይችላል ሲል ስጋቱን ገልጸዋል፡፡ የስደተኞች እና ተመላሾች አገልግሎት ችግሮችን ለመቅረፍ ከተቀባይ ማህበረሰብ በተጨማረ ዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ ትኩረት ሊያደርግ እንደሚገባ አመልክተዋል፡፡
ነጋሳ ደሳለኝ
እሸቴ በቀለ