የሊቢያ ለዉጥ አንደኛ ዓመት8 የካቲት 2004ሐሙስ፣ የካቲት 8 2004በሊቢያ የኮሎኔል ሞአመር ኤል ጋዳፊን የ40ዓመት አገዛዝ ለመገርሰስ ህዝባዊ አመፅ ከተቀጣጠለ ትናንት አንድ ዓመቱን ደፈነ። አገሪቱ ወደታለመላት የዴሞክራሲ ሥርዓት የምታደርገዉ ጉዞ ግን እንደተገመተዉ ቀላል እንደማይሆን ነዉ ሁኔታዉ ያመላከተዉ።ማገናኛዉን ኮፒ አድርግምስል APማስታወቂያ አገሪቱ ከአምባገነን ሥርዓት መላቀቋ አንድ ቢባልም፤ ጋዳፊን ከመንበረ ሥልጣናቸዉ ያስወገደዉ የሚሊሺያ ኃይል ሊቢያ ዉስጥ የሚፈፅመዉ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት በዓለም ዓቀፍ የመብት ተሟጋቾች እየተተቸ ነዉ። የፖለቲካ ተንታኞች በበኩላቸዉ ሊቢያ ያላትን ጥሬ ሃብት በአግባቡ ሥራ ላይ ብታዉል የተሻለ ነገር ማየት እንደሚቻልም ይናገራሉ። ሸዋዬ ለገሠ ሂሩት መለሰ