የሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ ጉብኝት
ሐሙስ፣ ጥር 11 2009ማስታወቂያ
በዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪቃ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ሊንዳ ቶማስ ግሬን ፊልድ ዛሬ አዲስ አበባ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል ። ከዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በተሠራጨው መረጃ መሠረት ሚኒስትሯ በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ከኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፣ ከአፍሪቃ ኅብረት ኮሚሽን ባለሥልጣናት እና ከአሜሪካን ኤምባሲ ሠራተኞች ጋር ይወያያሉ። ሆኖም ከዚህ የዘለለ ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል። ዶቼ ቬለ የጠየቃቸው ዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ የሥራ ኃላፊ ስለ ሚኒስትሯ ጉብኝት መረጃ እንደሌላቸው አስታውቀዋል። አንድ የአካባቢው የጂኦ ፖለቲካ ምሁር ግን ሚኒስትሯ ኢትዮጵያን የሚጎበኙት በኢትዮጵያ የረገበ የመሰለው አመጽ አሜሪካንን በእጅጉ ስለሚያሳስባት ነው ይላሉ። የዋሽንግተን ዲሲው ወኪላችን ዝርዝር ዘገባ አለው።
መክብብ ሸዋ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ