1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

«የልሳነ ግፉዓን ድርጅት»እና «የኢትዮ ካናዳውያን ኔትወርክ ለማኀበራዊ ድጋፍ» ጥሪ

ሐሙስ፣ ኅዳር 1 2015

የልሳነ ግፉአን ድርጅትመንግስት እጅግ ላጓተተው ላለው የወልቃይት ሕዝብ የዐማራ ማንነት ጥያቄ በግልጸኝነትና በቁርጠኝነት አፋጣኝ ፍትህ እንዲሰጥ ጠይቋል። ኢትዮ ካናዳውያን ኔትወርክ ለማኀበራዊ ድጋፍ/ኢክናስ/በበኩሉ፣በኢትዮጵያ ለተደረሰው የሰላም ስምምነት አፈጻጸም፣ ሁሉም ኃላፊነት ወስዶ እንዲወጣ ጠይቋል።

Pretoria | Waffenstillstandsabkommen für Äthiopien
ምስል፦ SIPHIWE SIBEKO/REUTERS

«የልሳነ ግፉዓን ድርጅት»እና «የኢትዮ ካናዳውያን ኔትወርክ ለማኀበራዊ ድጋፍ» ጥሪ

This browser does not support the audio element.

መንግስት ለወልቃይት ሕዝብ የዐማራ ማንነት ጥያቄ በግልጽ፣ በቁርጠኝነት አፋጣኝ መልስ እንዲሰጥ ልሳነ ግፉዓን ድርጅት ጥሪ አቀረበ።ድርጅቱ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ባወጣው መግለጫ፣የወልቃይት ጉዳይ የፍትህ ጥያቄ እንደሆነ አመልክቶ፣ሰላም የሚጸናውም ፍትሕን በማረጋገጥ ብቻ ነው ብሏል። የኢትዮ ካናዳውያን ኔትወርክ ለማኀበራዊ ድጋፍ/ኢክናስ/በበኩሉ፣በኢትዮጵያ ለተደረሰው የሰላም ስምምነት አፈጻጸም፣ ሁሉም ኃላፊነት ወስዶ እንዲወጣ ጠይቋል።

ተቀማጭነቱን እዚህ ዩናይትድስቴትስ ያደረገው ልሳነ ግፉዓን ድርጅት ባወጣው መግለጫ፣የወልቃይት ጉዳይ የፍትህ ጥያቄ እንደሆነ አጽንኦት ሰጥቶታል።ድርጅቱ ፕሬዚዳንት አቶ አብዩ በለው፣ መግለጫውን አስመልክቶ ከዶቸ ቨለ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ የሚከተለውን ተናግረዋል።በተለይ በወልቃይት ጠገዴ ጠለምት ሕዝብ ላይ የተፈጸመው መከራና ግፍ፣በከፊል ሕዝባችን ከህወሓት አገዛዝ ነጻ ቢወጣም፣ነገር ግን አሁንም ይኼ የሕዝባችን ጥያቄ ሙሉ አይደለም።አስካሁን አልተመለሰም።በተለይ የወልቃይት ሕዝብ የዐማራ ማንነት ጥያቄ አንስቷል፤እኔ ዐማራ ነኝ ትግሬ አይደለሁም።እና የተፈጸመብን ግፍ ደግሞ አለ።የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ወንጀል ተፈጽሞብኛል ስለዚህ ፍትህ ይገባኛል ብሎ ጥያቄ ያቀረበ ሕዝብ ነው።ነገር ግን ያ ጥያቄው እስካሁን በመንግስት በኩል ጥርት ያለ ግልጽ የሆነ መልስ አላገኘምና ይሄ ድል ይሄ ነጻነት የሚረጋገጠው ፍትህን በማስፈን ነው።ያለ ፍትህ ሰላም፣ ያለ ፍትህ ድል የለም ይሄ ሰላም እንዲረጋገጥ የሕዝባችን በተለይም ቀጥተኛ ተጠቂ የነበረው ባለፉት አርባ ዓመታት በህወሓት ወረራ ወንጀል የተፈጸመበት ሕዝባችን ፍትህ አላገኘም።ስለዚህ ይህ ፍትህ ሳይረጋገጥ ሰላም ይወርዳል ብሎ ማሰብ ከንቱ ድካም ነው ብለን እናምናለን እና ይህ ፍትህ እንዲረጋገጥ ይህ ፍትህ እንዲበየን መንግስትን የጠየቅንበት መግለጫ ነው።"
ስለሆነም፣ድርጅቱ መንግስት እጅግ ላጓተተው ላለው የወልቃይት ሕዝብ የዐማራ ማንነት ጥያቄ ሀግልጸኝነትና በቁርጠኝነት አፋጣኝ ፍትህ እንዲሰጥ ጠይቋል።የወልቃይት ሕዝብ ጥያቄ፣ለኢትዮጵያ አንድነትና ሉዓላዊነት የተከፈለ የ 40 ዓመታት ሰቆቃና ግፍ መቋጫ እንደሆነም ድርጅቱ አመልክቷል።በኢትዮጵያ መንግስትና በህወሓት መኻከል ለተደረሰው የሰላም ስምምነት ስኬት ድርሻቸውን ለተወጡም አቶ አብዩ በድርጅታቸው ስም ምስጋና አቅርበዋል።"የኢትዮጵያ መንግስት በፖለቲካው መስክ ያስመዘገበው በተለይ በጦር ግንባር ያስመዘገበውን ድል፣በዲፕሎማሲው እንዲሁ ሃገርን እና ትውልድን በሚያኮራ ሁኔታጠላትን ያንበረከከበት ትልቅ ድል ነው ብለን እናምናለን። ይህንን ድል በትክክል እኛ በድርጅታችን ደስተኞች ነን።"
በሌላ በኩል፣ኢትዮ ካናዳውያን ኔትወርክ ለማኀበራዊ ድጋፍ/ኢክናስ/በኢትዮጵያ ለተደረሰው የሰላም ስምምነት አፈጻጸም  ሁሉም ኃላፊነት ወስዶ እንዲወጣ ባወጣው መግለጫ ጥሪ አቅርቧል።ዶይቸ ቨለ ያነጋገራቸው የድርጅቱ ፕሬዚዳንት ዶክተር ትሁት አስፋው፣ሠላምን ለማረጋገጥ የሁሉንም አካላት ተሣትፎን ጠይቀዋል።"አብረን ከእነዚህ በጣም ሲዋጉ ከነበሩት ከኢትዮጵያ መንግስትና ህወሓት ስምምነት ላይ የእኛ የሕዝቡ ድጋፍ በሁሉም በኩል ወደ አንድ ዐሳብ መጥተን፣ ይህንን ሰላም የምናይበትን ስራ ተባብረን እንድንሰራ ጥያቄ ለሕዝቡም ጭምር ለማቅረብ ነው።"ኢክናስ ካናዳ በሰሜን ኢትዮጵያ በተካሄደው ጦርነት፣ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች አጣዳፊ ህይወት አድን ህክምና እንዲያገኙ ድጋፍ በማድረግ የሚታወቅ ድርጅት ነው።

ታሪኩ ኃይሉ 

ኂሩት መለሰ

ማንተጋፍቶት ስለሺ
 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW