1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ጤናሰሜን አሜሪካ

የልብ ህክምና ለማድረግ ከአትላንታ ወደ ኢትዮጵያ የተጓዘው የህክምና ቡድን

ሰኞ፣ ነሐሴ 13 2016

በኢትዮጵያ ከስድስት ሺህ በላይ ህሙማን ስቸኳይ የልብ ህክምና ለማግኘት በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ።በተለያዩ የልብ ህመሞች የሚሰቃዩ ህሙማንን ለማከም ዮናይትድ ስቴትስ አትላንታ ያለ ግብረ ሰናይ ድርጅት በጎ ፈቃደኛ የህክምና ባለሙያዎች ወደ ኢትዮጵያ በመጓዝ የሕይወት አድን ህክምና በመስጠት ላይ መሆናቸውን የድርጅቱ መሥራቾች ለዶይቸ ቨለ አስታውቀዋል።

Äthiopien | 
ምስል Tariku Hailu/DW

የልብ ህክምና ለማድረግ ከአትላንታ ወደ ኢትዮጵያ የተጓዘው የህክምና ቡድን

This browser does not support the audio element.


በኢትዮጵያ ከስድስት ሺህ በላይ ህሙማን አስቸኳይ የልብ ህክምና ለማግኘት በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ። በተለያዩ የልብ ህመሞች የሚሰቃዩ ህሙማንን ለማከም፣ዮናይትድ ስቴትስ አትላንታ የሚገኝ አንድ ግብረ ሰናይ ድርጅት በጎ ፈቃደኛ የህክምና ባለሙያዎች፣ወደ ኢትዮጵያ በመጓዝ የሕይወት አድን ህክምና በመስጠት ላይ መሆኑን የድርጅቱ መሥራቾች ለዶይቸ ቨለ አስታውቀዋል። በኢትዮጵያ እየተስፋፋ የመጣውን የልብ ህመም ችግር የመፍታት ተልዕኮ አንግቦ፣ አትላንታ የተቋቋመውን፣"ኸርት አታክ ኢትዮጵያ"የተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት ከባለቤታቸው ከዶክተር ተስፋዬ ጋር የመሰረቱት፣በሞርሐውስ የሕክምና ትምህርት ቤትና በግሬዲ ሆስፒታል የህክምና ባለሙያ ዶክተር ኦብሲኔት መርዕድ ናቸው።የጀርመን የህክምና ቡድን አባላት ነፃ የህክምና አገልግሎት

የልብ ህክምና ጉዞ ወደ ኢትዮጵያ

ዶክተር ኦብሲኔት እንደሚሉት፣ በአሁኑ ወቅት በልብ ህመም የሚሰቃዩ 100 ህሙማንን ለማከም ኢትዮጵያ ውስጥ እንቅስቃሴ ላይ የሚገኘው ግብረ ስናይ ድርጅታቸው፣ ከተቋቋመ ከአንድ ዓመት በላይ አስቆጥሯል።

የልብ ህክምና ጉዞ ወደ ኢትዮጵያምስል Tariku Hailu/DW

"ብዙ ጊዜ እንደምታውቀው፣ ኢትዮጵያን ስትጎበኝ ብዙ ሰው በድንገት እንደሚሞት እንሰማለን። ቁጭ ብሎ ቀረ እንደዚህ ዓይነት ነገር እንሰማለንና ያው ሊትሬቸሩን ሰናየው፣ የልብ ህመም በጣም እየበዛ በዓለም ላይ፣ኢትዮጵያ ውስጥም በቅርቡ እየሆነ ያለ ነገር ነውና እየበዛ በመምጣቱ፣በጣም ብዙ በሽተኞች እንዳሉ አሁን እኛ የምንሰራበት ማዕከል የልብ ህሙማን ማዕከል ነው።እዛ ራሱ  ወደ ስድስት ሺህ ሰው እየጠበቀ እንደሆነ ህክምና ለማግኘት ስንሰማ ይሄንን በማገናዘብ ነው እንግዲህ፣ኸርት አታክ ኢትዬጵያን ከዓመት በፊት እኔና ዶክተር ተስፋዬ ባለቤቴ አብረን የጀመርነው ማለት ነው።

አትላንታ በሚገኘው ፔዲሞንት ሆስፒታል የልብ ሀኪም የሆኑት ዶክተር ተስፋዬ ተሊላ በበኩላቸው፣ የልብ ህመም ኢትዮጲያ ውስጥ በወጣትነት ዕድሜ ክልል የሚገኙ ሰዎችን ጭምር በስፋት እየጠቃ፣ የሚያስፈልጋቸውን ህክምና በሚገባ እያገኙ ባለመሆናቸው ምክንያት፣ድርጅታቸው በኢትዮጲያ የህክምና ተልእኮ መጀመሩን አመልክተዋል።ከእንግዲህ የልብ ህሙማንን በአገር ዉስጥ ማከም ይቻላል

ተልዕኮውን ቀጣይ የማድረግ ግብ

"ኢትዮጵያ ይኼ አገልግሎት አለመኖሩ፣በምናውቀው ሰው ዘመዶቻችን ሕዝባችን እንደዚህ በተከታታይ እየሞተ ስናይ፣ይህንን ነገር የሆነ ነገር ማድረግ አለብን ብለን ነው የጀመርነው።እና አጀማመሩም በጣም ደስ የሚል ነው። እንግዲህ እግዚአብሔርን ከረዳን አሰራሩን በኢትዮጵያ ደረጃ፤ለማቋቋም ብቻ ሳይሆን ቀጣይነት እንዲኖረው አቅደን ነው እየተንቀሳቀስን ያለነው።"

ምስል Tariku Hailu/DW

ባለፈው ዐርብ ወደ ኢትዮጵያ በመጓዝ፣ ዛሬ የልብ ህመም ቀዶ ህክምና መስጠት የጀመረውና፣ 16 የህክምና በጎ ፍቃደኞችን ያካተተው የህክምና ቡድኑ፣የአሁኑ ሁለተኛው ጉዞ መሆኑ ነው።

በዚህ ጉዞው ከአንድ ነጥብ ሦስት ሚሊዮን በላይ የሚወጡ የልብ ህክምና መሳሪያዎችን ወደ ኢትዮጵያ አስገብቷል።የልብ ቀዶ ሐኪሙ ዶክተር አበበ ኪቢ ገመቹ 

እንደ ጎርጎሮሳዊው ጊዜ አቆጣጠር፣ ባለፈው የካቲት 2024 በተደረገው የመጀመሪያው ተልእኮ፣ የ 32 የልብ ህሙማንን ህይወት መታደግ መቻሉን ዶክተር ኦብሲኔት አመልክተዋል።

" ከተመሠረትን ከስድስት በኋላ ነው ወደ ኢትዮጵያ የሄድነው ለመጀመሪያ ጊዜ፣እኛ ስንሄድ ወደ ስድስት ሆነን ነው መጀመሪያ እና የረዳነው ያከምነው፣በመጠባበቅ ላይ ያሉ የልብ ህሙማን ማዕከል ላይ ሦስት አራት ዓመት እየተጠባበቁ ያሉ በሽተኞችን፣ አንድ 32 በሽተኞችን አክመን ነው የመጣነው።"

አስቀድሞ መከላከልና ግንዛቤ

ድርጅታቸው አስቸኳይ ህክምና የሚያስፈልጋቸው ወገኖችን ለመርዳት የበኩሉን ድርሻ መወጣት ቢጀምርም፣ ከችግሩ ስፋት አንጻር ሰፊ ጥረት እንደሚጠይቅ ያመለከቱት ዶክተር ተስፋዬ፣ስለበሽታው አስቀድሞ መከላከል ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ስራ ማካሄድ እንደሚገባም አሳስበዋል።

"ማስገንዘብ ሕዝቡን፤ስም ማውጣት አሁን ኸርት አታክ ስምም የለው በኢትዮጵያ አዲስ እሳቤ ነው። ስትሮክ ራሱ በጣም ብዙ ሰው እንደሚገድል ይታወቃል፤ ግን ግንዛቤው የለም ወደ ገጠር ወጣ ብለህ፣በከተማውም ቢሆን የለም።"ብለዋል።

ታሪኩ ኃይሉ
ኂሩት መለሰ 
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር 
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW