የልጅነት ልምሻ «ፖልዮ»ክትባት ዘመቻ
ዓርብ፣ ነሐሴ 8 2007ማስታወቂያ
አፍሪቃ ቀንድ የልጅነት ልምሻ ወይም ፖሊዮ እንዳይዛመት የተጠናከረ የክትባት ዘመቻ በመካሄድ ላይ መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት የህፃናት መርጃ ድርጅት በምህፃሩ UNICEF አስታወቀ ። ድርጅቱ እንዳለው በተለይ በኢትዮጵያ ከጎረቤት ሃገራት ጋር በሚያዋስኑ አካባቢዎች ክትባቱ በሰፊው እየተሰጠ ነው ። ከአንድ ዓመት በፊት የመጨረሻ የተባለው የፖልዮ ተጠቂ በሶማሊያ ከተገኘ በኋላ ክትባቱ በዘመቻ ሲሰጥ ቆይቷል ። በናይጀሪያም የፖልዮ በሽተኛ ከተገኘ ባለፈው ሀምሌ አንድ ዓመት አለፈ ። ሆኖም አፍሪቃ ከፖልዮ ነፃ ነች ለማለት ተጨማሪ ሁለት ዓመታት መጠበቅ እንዳለበት UNICEF አስታውቋል ።በሽታውን ለሚከላከለው ክትባት መግዣ የአውሮፓ ህብረት እርዳታ መስጠቱን የአዲስ አበባው ወኪላችን ዘግቧል ።
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ኂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ