1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሐምሌ 26 ቀን 2013 ዓ.ም. የስፖርት መሰናዶ

ሰኞ፣ ሐምሌ 26 2013

የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች ኢታሎ ቫሳሎ ሐምሌ 23 ቀን 2013 ዓ.ም. በሕመም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። በጃፓን ኦሎምፒክ ኢትዮጵያ በ10 ሺሕ ሜትር በሰለሞን ባረጋ አማካኝነት የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳልያ ብታገኝም በልዑካን ቡድኑ መካከል ተፈጠረ የተባለው አለመግባባት ለስፖርት አፍቃሪዎች አሳዛኝ ክስተት ሆኗል።

Japan Tokio | Olympische Spiele 2020 | Selemon Barega
ምስል The Yomiuri Shimbun/AP Images/picture alliance

የሐምሌ 26 ቀን 2013 ዓ.ም. የስፖርት መሰናዶ

This browser does not support the audio element.

የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች ኢታሎ ቫሳሎ ሐምሌ 23 ቀን 2013 ዓ.ም. በሕመም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። ኢታሎ ጉሮሯቸው ላይ በገጠማቸው ሕመም የቀዶ ሕክምና አድርገው መናገር ከማይችሉበት ደረጃ ደርሰው እንደነበር ለዶይቼ ቬለ የተናገሩት በቅርብ የሚያውቋቸው አቶ ፍቅሩ ኪዳኔ ከሚኖሩባት አስመራ ለሕክምና በተጓዙባት የጣልያኗ ሮም ማረፋቸውን አስረድተዋል። 
ኢታሎ እና ታላቅ ወንድማቸው ሉቺያኖ ቫሳሎ አራት ብሔራዊ ቡድኖች በተሳተፉበት ሶስተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተሰልፈው ከተጫወቱ መካከል ይገኙበታል። በዚህ ውድድር ኢትዮጵያ ግብጽን 4 ለ2 በማሸነፍ የአፍሪካ ዋንጫ ባለቤት ሆናለች። 
በጃፓን በመካሔድ ላይ በሚገኘው የኦሎምፒክ ውድድር ኢትዮጵያ በ10 ሺሕ ሜትር በሰለሞን ባረጋ አማካኝነት የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳልያ ብታገኝም በልዑካን ቡድኑ መካከል ተፈጠረ የተባለው አለመግባባት ለስፖርት አፍቃሪዎች አሳዛኝ ክስተት ሆኗል። የሞሮኮው ኤል ባካሊ የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት በሆነበት የ3000 መሰናክል ውድድር ኢትዮጵያዊው ለሜቻ ግርማ ሁለተኛ በመውጣት ለአገሩ የብር ሜዳሊያ አስገኝቷል።
የዛሬው የስፖርት መሰናዶ ከሚያተኩርባቸው ርዕሰ ጉዳዮች መካከል የኢታሎ ቫሳሎ ከዚህ ዓለም በሞት መለየት እና የኦሎምፒክ ጨዋታዎች ይገኝበታል።

ሃይማኖት ጥሩነህ
ነጋሽ መሐመድ
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW