1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የሐምሌ 7 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ

ሰኞ፣ ሐምሌ 7 2017

የቡድኖች የዓለም እግር ኳስ ዋንጫን ቸልሲ ፓሪ ሳንጃርሞን ትናንት በአስደናቂ ሁኔታ 3 ለ0 አሸንፎ 40 ሚሊዮን ዶላር ተቀብሏል፥ ተሸናፊው ፓሪ ሳንጃርሞም 30 ሚሊዮን ዶላር ደርሶታል ። ለመሆኑ ፓሪ ሳንጃርሞን ምን ነካው? የፓሪስ ነዋሪዎችስ ምን አሉ? ቃለ መጠይቅ አድርገናል ።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ከቸልሲ ተጨዋቾች ጋር
የቡድኖች የዓለም ዋንጫ ከተጠናቀቀ እና ዋንጫውን የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ለቸልሲ ተጨዋቾች ካበረከቲ በኋላምስል፦ Seth Wenig/AP/picture alliance

ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ

This browser does not support the audio element.

የቡድኖች የዓለም እግር ኳስ ዋንጫን ቸልሲ ፓሪ ሳንጃርሞን ትናንት በአስደናቂ ሁኔታ 3 ለ0 አሸንፎ 40 ሚሊዮን ዶላር ተቀብሏል፥ ተሸናፊው ፓሪ ሳንጃርሞም 30 ሚሊዮን ዶላር ደርሶታል ። እጅግ ትርፋማ ከነበረው አጠቃላይ ውድድር 2 ቢሊዮን ዶላር መሰብሰቡ ተዘግቧል ። ለመሆኑ ፓሪ ሳንጃርሞን ምን ነካው? የፓሪስ ነዋሪዎችስ ምን አሉ? ቃለ መጠይቅ ይኖረናል ። እድሜያቸው ከ20 እና 18 ዓመት በታች የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን ለአፍሪቃ አትሌቲክስ ፉክክር ወደ ናይጄሪያ አቅንቷል ።  ተጨማሪ ዘገባዎችንም አካተናል ። 

አትሌቲክስ

ከረቡዕ ሐምሌ 9 ቀን፣ 2017 ዓ.ም እስከ እሁድ ሐምሌ 13 ቀን፣ 2017 ዓ.ም ድረስ በናይጄሪያ አቡከታ እድሜያቸው ከ20 እና 18 ዓመት በታች የአፍሪቃ አትሌቲክስ ፉክክር ይከናወናል ። ኢትዮጵያን ወክሎ የሚሳተፈው የአትሌቲክስ ልዑክ ቡድን የመጀመሪያው ተጓዥ ዛሬ ማለዳ ወደ ናይጄሪያ አቡኩታ ማምራቱ ተዘግቧል ።  የኢትዮጵያ ሁለተኛ ዙር የወጣቶች አትሌቲክስ ልዑክ ቡድን ዛሬ እኩለ ሌሊትም ወደ ናይጄሪያ እንደሚጓዝ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ገልጧል ።

የዘንድሮ ሻምፒዮንስ ሊግ፣ የፈረንሣይ ሊግ፤  የፈረንሳይ ዋንጫ እና የአሸናፊዎች ዋንጫ አሸናፊ ነበር፤ ፓሪ ሳንጃርሞ ። ኢንተር ሚላንን 5 ለ0 አደባይቶ የአውሮጳ ሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን ያነሳው ቡድን ፒኤስጂ ግን ትናንት በቸልሲ ጉድ ሁኗል ። በቡድኖች የዓለም ዋንጫ በቸልሲ እጅግ ተበልጦ 3 ለ0 ተሸንፏል ። ቸልሲ ዘንድሮ በኮንፈረንስ ሊግ ሪያል ቤቲስን 4 ለ1 ድል አድርጎ ዋንጫ ያነሳ ቡድን ነው ።

ቸልሲ የቡድኖች የዓለም ዋንጫን ወሰደ

የቡድኖች የዓለም ዋንጫ ላይ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ከፊፋ ፕሬዚደንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ ጋር በመሆን ጨዋታው ከተጠናቀቀ በኋላ ሜዳሊያዎችን እና ዋንጫዎችን ለተጨዋቾች ሸልመዋል ።

የቡድኖች የዓለም ዋንጫ ላይ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ከፊፋ ፕሬዚደንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ ጋር ምስል፦ Pamela Smith/AP/picture alliance

ጂያኒ ኢንፋንቲኖ እና ዶናልድ ትራምፕ ጨዋታው ከተጠናቀቀ በኋላ ሜዳሊያዎችን እና ዋንጫዎችን ለተጨዋቾች ሸልመዋል ። የቡድኖች የዓለም እግር ኳስ ዋንጫን  ፓሪ ሳንጃርሞን ትናንት በአስደናቂ ሁኔታ 3 ለ0 አሸንፎ  የወሰደው ቸልሲ 40 ሚሊዮን ዶላር ተቀብሏል፥ ተሸናፊው ፓሪ ሳንጃርሞም 30 ሚሊዮን ዶላር ደርሶታል ። እጅግ ትርፋማ ከነበረው አጠቃላይ ውድድር 2 ቢሊዮን ዶላር መሰብሰቡ ተዘግቧል ። 

የሜዳ ቴኒስ

በሐምቡርግ የአውሮጳ የቴኒስ መክፈቻ የሜዳ ቴኒስ ዛሬ ተከናውኗል ። በሴቶች ውድድር፦ የፈረንሳዩዋ ዲያነ ፓሪ የክሮሺያዋን ታራ ቩርዝ 7 ለ6 እባ 11 ለ9 አሸንፋለች ። በወንዶች የማጣሪያ ፉክክር ደግሞ የኦስትሪያው ፊሊፕ ሚሶሊች የስዊድኑ ዖሌ ዋሊንን 7 ለ6 እና 6 ለ2 ድል አድርጓል ። የብራዚሉ ቲያጎ ሞንቴሪዮ ደግሞ  የሉታኒያውን ቪሊዩስ ጋውቡስን  6 ለ2 እና 6 ለ3 ድል አድርጓል ። የሰኔ 30 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ

ስለ ቡድኖች የዓለም ዋንጫ ከሃይማኖት ጋር የተደረገውን ሙሉ ቃለ መጠይቅ በድምፅ ማድመጥ ይቻላል

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ሃይማኖት ጥሩነህ

 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW