1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሐረማያ ዩኒቨርስቲ የሕክምናና የቁሳቁስ ርዳታ

ማክሰኞ፣ ኅዳር 20 2015

በሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ስር በሚገኘው ህይወት ፋና ስፔሻላይዝድ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል የዓይን ህክምና ስፔሻሊስት ዶ/ር ደስታ ገነቴ ለዓይነ ስውርነት ሊዳርግ እንደሚችል የገለፁትን የዓይን ሞራ ችግር ለማቃለል ዘመቻው መደረጉን አስረድተዋል።

Äthiopien | Uniklinik Harar
ምስል Mesay Teklu/DW

ዩኒቨርስቲዉ በርዳታ ያገኘዉን ከ100 ሺሕ በላይ መነፅር እያከፋፈለ ነዉ

This browser does not support the audio element.

 

የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ከቱርክ ድርጅት ጋር በመተባበር የዓይን ሞራ ለሚጋርዳቸዉ 400 ያክል ሕሙማን  የቀዶ ህክምና አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን አስታወቀ። ዩኒቨርስቲዉ ከዉጪ ያሰባሰባቸውን አንድ መቶ ሺህ የዓይን መነፅሮች ምርመራ በማድረግ ለዓይን ሕሙማን እያደለ መሆኑን አንድ የዩኒቨርስቲዉ ባለስልጣን አስታዉቀዋል።ዩኒቨርሲቲው በዓይን ጤና ዙርያ እየሰጠ ባለው የነፃ አገልግሎት በአካባቢው የሚገኙ ነዋሪዎች ተጠቃሚ ስለመሆናቸው ገልፀዋል።

የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ ተሳትፎ እና ኢንተርፕራይዝ ልማት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ይስሀቅ ዩሱፍ ዩኒቨርሲቲው ከቱርክ ድርጅት ጋር በመተባበር አራት መቶ ለሚሆኑ የአካባቢው ነዋሪዎች የዓይን ሞራ ቀዶ ጥገና ህክምናን በነፃ እየሰጠ መሆኑን ገልፀዋል።

የዓዒይን ቀዶ ሕክምና በሐረማያ ዩኒቨርስቲምስል Mesay Teklu/DW

ለአካባቢው ህብረተብ በተለይ በዓይን ጤና ለሚቸገሩ ነዋሪዎች ዩኒቨርሲቲው አንድ መቶ ሺህ የሚሆኑ የዓይን መነፅሮችን ከውጭ በማሰባሰብ  ምርመራ አድርጎ እየሰጠ መሆኑንም ዶ/ር ይስሀቅ ጠቁመዋል።ሐረማያ ዩኒቨርሲ የኮሮና ምርመራ በሁለት ቦታ ጀመረ

በሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ስር በሚገኘው ህይወት ፋና ስፔሻላይዝድ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል የዓይን ህክምና ስፔሻሊስት ዶ/ር ደስታ ገነቴ ለዓይነ ስውርነት ሊዳርግ እንደሚችል የገለፁትን የዓይን ሞራ ችግር ለማቃለል ዘመቻው መደረጉን አስረድተዋል።

የዓዒይን ቀዶ ሕክምና በሐረማያ ዩኒቨርስቲምስል Mesay Teklu/DW

"አንድ አመት ሙሉ ዓይኔ አያይልኝም ። ምንም ነገር አያይልኝም ነበር" የሚሉት የቀርሳ ከተማ ነዋሪው አቶ ሱራፌል አባይነህ ባገኙት አገልግሎት ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ዩኒቨርሲቲው ከእዚህ በተጨማሪ በተፈጥሮ የእግር ጥመት እንዲሁም የከንፈር መሰንጠቅ ችግር ለገጠማቸው ሰዊችም ተመሳሳይ የነፃ ህክምና አገልግሎት እንደሚሰጥ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

 መሳይ ተክሉ

ነጋሽ መሐመድ

እሸቴ በቀለ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW