1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሐሮማያ ሐይቅ በእርግጥ ተመልሶ ይሆን?

ሐሙስ፣ መስከረም 7 2013

ከ1990ዎቹ ጀምሮ በሶስትና አራት አመታት ከገፀ ምድሩ ላይ የጠፋው የሀረማያ ሀይቅ በሀይቁ  ቦርቀው ላደጉ ፣ የማይረሳ ጊዜን ላሳለፉ እና በሩቅ ለሚያውቁት ሁሉ አሳዛኝ ክስተት እንደሆነ በቁጭት አመታት ተቆጥረዋል፡፡ እንደ ደረቀ ሁለት አስርት ዓመታት ሊሞላው ያለው ሀይቁ በክረምቱ ወደ ቀድሞ የመመለስ ተስፋ ማሳየቱ ብዙዎችን አስደስቷል ፡፡

Äthiopien See Haremaya
ምስል DW/M. Tekelu

የሐሮማያ ሐይቅ ተመልሶ ይሆን?

This browser does not support the audio element.

ከ1990ዎቹ ጀምሮ በሶስትና አራት አመታት ከገፀ ምድሩ ላይ የጠፋው የሀረማያ ሀይቅ በሀይቁ  ቦርቀው ላደጉ ፣ የማይረሳ ጊዜን ላሳለፉ እና በሩቅ ለሚያውቁት ሁሉ አሳዛኝ ክስተት እንደሆነ በቁጭት አመታት ተቆጥረዋል፡፡ በተለይ የክረምት ወራት ከሚይዘው መጠነና ውሀ ባለፈ በጋውን እንደ ደረቀ ሁለት አስርት ዓመታት ሊሞላው ያለው ይህ ሀይቅ በተገባደደው ክረምት ወደ ቀድሞ የመመለስ ተስፋ ማሳየቱ ብዙዎችን አስደስቷል ፡፡በእርግጥ የሐሮማያ ሐይቅ ተመልሶ ይሆን? ።ዶ/ር ክበበው ክብረቴ በሀረማያ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮ ሀብት አያያዝና የአካባቢ ሳይንስ ትምህርት ክፍል የተፈጥሮ ሀብት ባላሞያ ናቸው፡፡ ከአመታት በኋላ ተስፋ ስለታየበት የሐይቁ ክስተት ለዶይቸ ቬለ ተከታዩን ምላሽ ሰተዋል፡፡በተገባደደው የክረምት ወራት እየጣለ ያለው ዝናብ ገፅታውን የቀየረለት የሀረማያ ሀይቅ ወደ ቀድሞ ሁኔታው ተመልሷል ማለት ይቻላል ወይ? ለሚለው ጥያቄ ባለሞያው እንዳሉት እንደዚያ ብሎ ለመደምደም ጊዜው ገና ቢሆንም ነገር ግን ምልክት ታይቶበታል ፡፡ዶ/ር ኢንጅነር ተሾመ ስዩም በዩኒቨርሲቲው የሀይድሮሊክስ እና በውሀ ሀብት ምህንድስና ተባባሪ ፕሮፊሰር ናቸው፡፡ከአመታት በኃላ በጥሩ ሁኔታ የመመለስ ምልክት አሳይቷል ያሉት የሀረማያ ሀይቅን ጠብቆ ለማቆት ስራዎች መሰራት አለባቸው ብለዋል - ለዚህ አንዱ ደለል ማፅዳት ነው ፡፡የውሀ አጠቃቀም አስተዳደር ስርዓት እንዲኖር ማድረግ እንዲሁም የአፈርና ውሀ ጥበቃ ስራዎችን ማከናወን ይገባል ያሉት ዶ/ር ተሾመ አስፈላጊ ካሉት መፍትሄ ሌላኛው ሀይቁ የራሱ ክልል እንዲኖረው ማስቻል ነው፡፡ሁለቱ ባለሞያዎች በዋነኛነት በክረምቱ ዝናብ ጥሩ መሆን የመመለስ ተስፋ የታየበትን ሀይቅ ተጨባጭ ሁኔታን በመረጃ ለመደገፍ እና ከዳግም ጥፋት ለመታደግ በዩኒቨርሲቲው ቀደም ሲል የተጀመረ ስራ ተጠናክሮ በመሰራት ላይ ነው ብለዋል፡፡አንድ በአካባቢው ተወልደው ማደጋቸውን የገለፁ አስተያየት ሰጪ ሀይቁ ዳግም አንሰራርቶ በማየታቸው መደሰታቸውን ለዶይቸ ቬሌ(DW) ተናግረዋል፡፡

መሳይ ተክሉ

ታምራት ዲንሳ

አዜብ ታደሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW