1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የሐይማኖት መሪዎችና የአገር ሽማግሌዎች አዲስ አበባና መቐለን ሊያሸማግሉ ነው

ሰኞ፣ ሰኔ 8 2012

የሐይማኖት መሪዎችና ሽማግሌዎች የኢትዮጵያ ፌድራል መንግሥትና የትግራይ ክልላዊ መሥተዳድርን ለማስታረቅ ጥረት መጀመራቸውን አስታወቁ። የኢትዮጵያ የሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ ሐጂ መስዑድ አደም የኢትዮጵያ ነባራዊ ፖለቲካ የሐይማኖት መሪዎችና የአገር ሽማግሌዎችን "ጣልቃ ገብነት ይፈልጋል" ሲሉ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።

Ethiopian religious leaders met with the head of Tigray regional government Dr. Debretsion Gebremichael
ምስል፦ DW/M. Haileselassie

በፌድራል መንግሥት እና በትግራይ መካከል "ጣልቃ ገብነት ይፈልጋል" ብለዋል

This browser does not support the audio element.

የኢትዮጵያ የሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ እና የአገር ሽማግሌዎች ጥምረት በጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ የፌድራል መንግሥት እና በትግራይ መካከል የተካረረውን ልዩነት ለማስታረቅ ወደ መቐለ ሊያመሩ ነው። የኢትዮጵያ የየሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ ሐጂ መስዑድ አደም የኢትዮጵያ ነባራዊ ፖለቲካ የሐይማኖት መሪዎች እና የአገር ሽማግሌዎችን "ጣልቃ ገብነት ይፈልጋል" ሲሉ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል። ለሽምግልናው ይሁንታ የሰጡት የትግራይ ክልል ከፍተኛ አመራሮች የሐይማኖት ተቋማት መሪዎች እና የአገር ሽማግሌዎች በሚያደርጉት ጥረት እንደሚገኙ ገልጸዋል።

ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር
ነጋሽ መሐመድ
 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW