1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሕወሓት ባለሥልጣናት ክፍፍል የቆየ ነዉ ተባለ

ዓርብ፣ ጳጉሜን 1 2016

ህወሓት መከፋፈል ውስጥ ባለበት በተደረገ ጉባኤ የፓርቲው ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ሆነው የተመረጡት ዶክተር ፍስሃ ሃፍተፅዮን፥ ፓርቲያቸውን ወክለው ትላንት ማምሻው በህወሓት ዋናው ፅሕፈት ቤት የሰጡት መግለጫ በተለይም የፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት መነሻ፣ ሂደት እና አፈፃፀም ላይ ትኩረቱ ያደረገ ነበር

ዶክተር ፍስሃ ሃፍተፅዮን እንደሚሉት የፕሪቶሪያዉ ድርድር ሲደረግ በሕወሓት መልዕክተኞች መካከል ልዩነት ነበር
የህወሓት ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ሆነው የተመረጡት ዶክተር ፍስሃ ሃፍተፅዮንምስል Million Haileselasie/DW

የሕወሓት ባለሥልጣናት ክፍፍል የቆየ ነዉ ተባለ

This browser does not support the audio element.

                             
የኢትዮጵያ ፌደራዊ መንግስትና ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ፕሪቶርያ ዉስጥ የተፈራረሙት የሰላም ስምምነት በፌደራሉ መንግሥትና በሕወሓት የዉስጥ ክፍፍል ምክንያት ገቢር አለመሆኑን ሕወሓት አስታወቀ።በፕሪቶሪያ ድርድር ህወሓትን ከወከሉት እና በቅርቡ በተደረገ ጉባኤ የህወሓት ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ሆነው የተመረጡት ዶክተር ፍስሃ ሃፍተፅዮን እንደሚሉት የፕሪቶርያው ስምምነት በሚፈረምበት ወቅት ጭምር በህወሓት ተወካዮች መካከል ልዩነት ነበረ። 

ህወሓት መከፋፈል ውስጥ ባለበት በተደረገ ጉባኤ የፓርቲው ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ሆነው የተመረጡት ዶክተር ፍስሃ ሃፍተፅዮን፥ ፓርቲያቸውን ወክለው ትላንት ማምሻው በህወሓት ዋናው ፅሕፈት ቤት የሰጡት መግለጫ በተለይም የፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት መነሻ፣ ሂደት እና አፈፃፀም ላይ ትኩረቱ ያደረገ ነበር። የሁለት ዓመቱ ጦርነት ያስቆመ የፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት ሲፈረም፥ ህወሓትን ወክለው በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ ከነበሩ ልኡካን መካከል የሆኑት ዶክተር ፍስሃ ሃፍተፅዮን፥ ከተፈረመ ሁለት ዓመት ሊሞላው ጥቂት ወራት የቀሩት ስምምነት በውስጣዊ እንዲሁም በፌደራሉ መንግስት ምክንያት ተግባራዊ ሳይሆን መቅረቱ ገልፀዋል። አሁን ህወሓት ውስጥ ያለው ልዩነት፥ ድንገት አሁን ላይ የጀመረ እንዳልሆነ ያብራሩት ዶክተር ፍስሃ፥ በፕሪቶርያ የሰላም ስምምነቱ ሲደረግ በነበረበት ወቅትምት ቢሆን በህወሓት ልኡካን መካከል ልዩነት እንደነበረ፥ አንዱ በቅርቦ ሌላው የማራቅ ዝንባሌዎች ማስተዋላቸው አጋልጠዋል። ይህም ሌላ ሴራ የነበረው መሆኑ እንደሚገነዘቡ ዶክተር ፍስሃ ሃፍተፅዮን ተናግረዋል።

በክፍፍሉ ወቅት የተደረገዉ የሕወሓት ጉባኤ ምስል Million Haileslasse/DW

ዶክተር ፍስሃ ሃፍተፅዮን "ሂደቱ እንደሚታወቀው አስር ቀን አካባቢ የወሰደ ነበረ። መጀመርያ አካባቢ ሁላችንም በሓላፊነት ስሜት የምንሳተፍበት ሁኔታ ነበረ። በሂደት ግን አንዱ ባለቤት ሌላው ወደኃላ የሚገፋበት፥ ትክክለኛ ያልሆነ አካሄድ ነው የነበረው። ተጋግዞ በከፍተኛ ደረጃ የትግራይ ጥቅም ማስከበር የሚቻልበት ዕድል ይቻል ነበር። በኃላ ላይ ግን የተወሰኑ ባለቤት እና የፈለጉት የሚያደርጉ፣ ሌሎች የሚገፉበት እና ተሳትፎ የማያደርጉበት ሁኔታ ነው የተፈጠረው። አሁን ላይ ሆነን ስናየው፥ ይህ ሆን ተብሎ የተደረገ ነገር ነው የሚል እምነት ነው ያለን። ማስረጃዎችም እየወጡ ስለሆነ" ብለዋል።

ህወሓት የፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት ለማፍረስ እየሰራ ነው፣ ከኤርትራ ሐይሎች ጋር እየተመሳጠረ ነው፣ የጦርነት ፍላጎት አለው የሚሉ የሐሰት መረጃዎች እየተሰራጩ ናቸው የሚሉት እኚህ የህወሓት ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል፥ ህወሓት ከኤርትራ ጋር ግንኙነት እንደሌለው በአንፃሩ ግን በውስጣችን ያሉት የትግራይ መሬት የወረሩት ደጋፊዎች ናቸው ሲሉ ከሰዋል። ከዚህ በተጨማሪ ግዚያዊ አስተዳደሩ ግማሽ የትግራይ ክፍል እያስዳደረ ያለ፣ ደካማ አስተዳደር ሲሉ የተቹት ዶክተር ፍስሃ፥ የፕሪቶርያው ውል እንዳይፈፀምም ከፌደራል መንግስቱ በተጨማሪ ዕንቅፋት በመፍጠር ላይ ይገኛል ሲሉ ገልፀውታል።

ዶክተር ፍስሃ "ከዋነኛ የልዩነት ነጥቦች አንዱ የፕሪቶርያ ውል አፈፃፀም የሚመለከት ነው። ከህወሓት በኩል ውሉ በስምምነቱ እንደተቀመጠው መሰረት እንዲተገበር፥ የሚቻለውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ ሆኖ ነው የቆየው፥ አሁንም ዝግጁ ነው። ይሁንና እንደምታውቁት ስምምነቱ ሊተገበር አልቻለም። ስምምነቱ እንዳይተገበር ያደረገው ብዙ ምክንያቶች አሉ። አንዱ ከውስጣችን የሚነሳ ነው። ሌላው ደግሞ ከተደራዳሪው ሐይል ነው። ከዚህኛው ሐይል ጋር የሚተባበር የውስጥ ሁኔታ አለ። እነዚህ ተባብረው ውሉ ሊተገበር አልቻለም። በሌላ በኩል ደግሞ፥ ሐላፊነት ወደ ሌላ የመጣል የሚመስል ሁኔታ አለ" ብለዋል።

የትግራይ ጊዚያዊ ፕሬዝደንት አቶ ጌታቸዉ ረዳምስል Million Haileselassie/DW

ከህወሓት በኩል የተነሱት ክሶች አስመልክቶ ከግዚያዊ አስተዳደሩ መሪዎችምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። ይህ በእንዲህ እንዳለ የግዚያዊ አስተዳደሩ መሪዎች ዛሬ ጨምሮ ሰሞኑን በተለያዩ የትግራይ ከተሞች በመዘዋወር ህዝባዊ ስብሰባዎች እና ሌሎች መድረኮች በማድረግ ላይ ናቸው። በያዝነው ሳምንት ብቻ አቶ ጌታቸው ረዳ ጨምሮ በርካቶች የአስተዳደሩ መሪዎች የተገኙባቸው ስብሰባ እንዲሁም የአደባባይ ትእይንቶች የተስተዋሉባቸው አጋጣሚዎች በዓዲግራት፣ ማይጨው እና መኾኒ በተለያዩ ቀናት ተካሂደዋል።

ሚሊዮን ኃይለሥላሴ

ነጋሽ መሐመድ

እሸቴ በቀለ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW