1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሁለት አዋጆችን አጸደቀ

ሰለሞን ሙጬ
ሐሙስ፣ ጥር 1 2017

የንብረት ማስመለስ አዋጅ "የፖለቲካ ማጥቂያ መሣሪያ እንዳይሆን" በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ተጠየቀ።ዛሬ ጥር 1 ቀን በአብላጫ ድምጽ የጸደቀው ይህ አዋጅ "የተወሰኑ ግለሰቦችን፣ እና ቡድኖችን ለማጥቃት ከፖለቲካ ፍላጎት የመነጨ ነው" በሚል ተቃውሞ ተነስቶበታል። ምክር ቤት የነዳጅ ውጤቶች ግብይት ሥርዐት አዋጅም አጽድቋል።

Äthiopien FDRE-House
ምስል፦ Ethiopian Press Agency

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሁለት አዋጆችን አጸደቀ

This browser does not support the audio element.

የንብረት ማስመለስ አዋጅ "የፖለቲካ ማጥቂያ መሣሪያ እንዳይሆን" በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ተጠየቀ።ዛሬ ጥር 1 ቀን በአብላጫ ድምጽ የጸደቀው ይህ አዋጅ "የተወሰኑ ግለሰቦችን፣ እና ቡድኖችን ለማጥቃት ከፖለቲካ ፍላጎት የመነጨ ነው" በሚል ተቃውሞ ተነስቶበታል።

የፍትሕ ተቋማት "ገለልተኛነት እና የማስፈጸም አቅም" ጥያቄ ውስጥ በወደቀበት በዚህ ጊዜ ይህንን ሕግ ማጽደቅ ከፍተኛ ጉዳት ያስከትላል የሚሉ ጥያቄዎችም ተነስተው ነበር።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የነዳጅ ውጤቶችን ግብይት ሥርዐት ለመደንገግ የወጣውን አዋጅም በዛሬው መደበኛ ጉባሬኤው አጽድቋል።

የአዋጁ ዝርዝር ጉዳዮች ምንድን ናቸው? 

በ 3 ተቃውሞ እና በአራት ድምጽ ተአቅቦ፣ በአብላጫ ድምጽ የጸደቀው የንብረት ማስመለስ አዋጅ "አላማው ግልጽ አይደለም"፣ "ከጥቅሙ ይልቅ በዜጎች መካከል ማህበራዊ ትስስርን የሚበጥስ" ያልተገባ መጠቋቆም እንዳያስከትል በሚል አከራክሯል።

አዋጁ "የወንጀል ፍሬ የሆኑ ንብረቶችን እና ገንዘቦችን ውጤታማ በሆነ መልኩ ለመያዝ፣ ለማገድ፣ ለመውረስ ወይም ለማስተዳደር የሚያስችል" እና "ማንም ሰው ከሕገ - ወጥ ድርጊት ማናቸውንም አይነት የኢኮኖሚ ጥቅም እንዳያገኝ ለማድረግ" ያለመ ነው ተብሏል።

"የኢኮኖሚ ወንጀል በሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ በመሆኑ" ወንጀሉን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር መውጣቱ ተነግሯል።

ከመንግሥት እና ሕዝባዊ ድርጅት ሠራተኞች ውጭ ባለ ማንኛውም ሰው፣ የሕግ ሰውነት ባላቸው ድርጅቶች ላይም ተፈፃሚ እንደሚሆንም ተመላክቷል። ሆኖም ይህ ጥያቄ አስነስቷል።

የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤትምስል፦ DW/Y. Gebreegiziabher

የምክር ባት አበላት የሰጧቸው አስተያየቶች

"የመንግሥት፣ የሃይማኖት ተቋማት፣ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ላይ ይህ አዋጅ ተፈፃሚ አይደረግባቸውም። ለምን" የሚሉ ጥያቄዎች ተነስተዋል።

ረቂቅ አዋጅ "በወንጀል ሕጉ መሠረት በጥፋተኝነት ላይ የተመሠረተ የንብረት መውረስ የሚደረግ ቢሆንም በወንጀል ሕጉ መሠረት ተከሰው ንብረታቸው የማይወረስ የሕግ ሰውነት ያላቸው ተቋማት በፈፀሙት ሕገ - ወጥ ድርጊት ጥቅም ካገኙ የንብረት መውረስ ክስ ሊቀርብባቸው የሚችልበት አዲስ ሥርዓት ተዘርግቷል" ይላል። ሆኖም የሕዝቦችን ትስስር የሚበጥስ አደጋ እንዳያስከትል አስግቷል።

"ይህ ጉዳይ በሕዝቦቻችን መካከል የመጠራጠር፣ የመጠፍልፋት፣ የመወነጃጀል ነገር እንዳያመጣ ምን ያህል ጥንቃቄ እናደርጋለን"?

የምክር ቤት አባላት ከፍትሕ ተቋማት ገለልተኛነት በመነሳትም የአዋጁ አስፈላጊነትላይ ጥያቄ አንስተዋል።የፍትሕ ተቋማት ነጻ፣ ገለልተኛ እና በቂ የሆነ አቅም በሌላቸው ኹኔታ እንደዚህ አይነት አዋጅን ያስፈጽማሉ ብየ አልገምትም።"
ይህ የንብረት ማስመለስ አዋጅ ፖለቲከኞችን፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችን፣ ባለሃብቶችን ለማጥቃት እንዳይውል የሚል ሥጋትም ተንፀባርቆበታል።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አዲስ አበባፎቶ ከማኅደርምስል፦ Solomon Muche/DW

"ይህ አዋጅ የፖለቲካ ማጥቂያ መሣሪያ እንዳይሆን ምን ያህል ጥንቃቄ ተደርጎበታ?" 
በስምንት ክፍል እና በ 57 አንቀጾች የተዋቀረው የዚህ አዋጅ  አስፈላጊነት በራሱ ጥያቄ ቀርቦበታል።
ለዚህ ጥያቄ በምክር ቤቱ የሕግና ፍትሕ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ እፀገነት መንግስቱ ምላሽ ሰጥተዋል።
"የአዋጁ ዓላማ ግልጽ ነው። በዚህች ሀገር ኢኮኖሚ ውስጥ ተረጭተው ያሉ እንደተፈለገ የሚዘወርባቸውን ሀብቶች መሰብሰብ ነው"።

ሌላኛው ዛሬ የፀደቀው አዋጅ

ምክር ቤቱ ዛሬ ጥር 1 ቀን 2917 ዓ.ም ባደረገው 14ኛ መደበኛ ጉባኤው የነዳጅ ውጤቶችን ግብይት ሥርዐት ለመደንገግ የቀረበውን አዋጅም ፀድቋል።ይህንን በተመለከተው ውይይት ሕገ ወጥ የነዳጅ ግብይት በየሰፈሩ ይሸጣል፣ የቁጥጥር መላላትም አለ የሚለው በስፋት ተነስቷል።

መንግሥት የአቅርቦት ችግር ላይ ቢያተኩር፣ የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስርሚኒስቴር በየወሩ ነዳጅን በዘፈቀደ ማሻሻያ የሚያደርግበት ሥልጣን ቢገደብ፣ አዋጁ ችግሩን ይፈታልም፣ አይፈታምም የሚሉ ሀሳቦችም ተስተጋብተዋል። ሕግ ማውጣት ብቻውን ትርጉም የለውም፣ ክትትል እና ቁጥጥር እስካልተደረገ ድረስ አሁንም ችግሩ ይቀጥላል የሚሉ ሀሳቦችም ቀርበዋል።

የነዳጅና ኢነርጁ ባለሥልጣን የበላይ ሀላፊ ነዳጅ በታሪፍ እየተሸጠ አለመሆኑን አምነው አንድ ሊትር ቤንዚን ከ 300- 600 ብር ይሸጥ እንደነበር ተናግረዋል።

ከትናንት በፊት የተደረገው የነዳጅ ዋጋ ማሻሻያም መንግሥት ያደረገውን የውጭ ምንዛሪ ግብይት ማሻሻያ ተከትሎ ስለመሆኑ ተገልጿል።

ሰለሞን ሙጨ
እሸቴ በቀለ 
ፀሐይ ጫኔ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW