የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጉባኤ ዉሳኔ
ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 15 2013
ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባደረገዉ ሥብሰባዉ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን የቦርድ ኃላፊንና የአባላትን ሹመት አፅደቀ። ምክር ቤቱ የመገናኛ ብዙሐን ረቂቅ አዋጅንና የፀረ ሙስና ኮሚሽንን ዳግም ለማደራጀት የተረቀቀዉን ደንብ ለየሚመለከታቸዉ ኮሚቴዎች መርቷል። ምክር ቤቱ የተለያዩ ውሳኔዎችን ያሳለፈበትን ሥብሰባ በይፋ ያደረገዉ ርዕሡ ባልታወቀ ጉዳይ ላይ ለአንድ ሰዓት ያሕል በዝግ ከመከረ በኋላ ነው። ጋዜጠኞችና ለምክር ቤቱ አባላት ገለፃና ማብራሪያ እንዲሰጡ የተጋበዙ ባለ ሥልጣናት ከጉባኤዉ አዳራሽ ውጪ ለመቆየት ተገድደዋል። የአዲስ አበባው ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።