1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

«መንግሥት ከፋኖ ጋር ውይይት ጀምሯል» ማለቱን የተመለከተ የሕዝብ አስተያየት

ዓርብ፣ ሐምሌ 26 2016

በአማራ ክልል መንግሥት የክልሉን ልዩ ኃይል እና የፋኖ ታጣቂዎችን በአጭር ጊዜ ውስጥ ትጥቅ አስፈታለሁ በሚል የጀመረው ወታደራዊ ዘመቻ ዓመት ሆነው። አሁንብ በተለያዩ የአማራ ክልሉ አካባቢዎች በመንግሥት ኃይሎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ውጊያ መቀጠሉ እየተነገረ ነው።

የፋኖ ተዋጊ በላሊበላ
የፋኖ ተዋጊ በላሊበላ ፎቶ ከማኅደር ምስል Solan Kolli/AFP/Getty Images

የሕዝብ አስተያየት

This browser does not support the audio element.

በዚህ መሀልም ጠቅላይ ሚኒስተር አቢይ አህመድ ስለጀመሩት የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሃግር ለመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ማብራሪያ በሰጡበት አጋጣሚ፤ በአማራ ክልል ከመንግሥት ጋር ከሚዋጉ አንዳንድ ቡድኖች ጋር ውይይት መጀመሩን ለመጀመሪያ ጊዜ ፍንጭ ሰጥተዋል። ምንም እንኳን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በክልሉ ከሚንቀሳቀሱ የታጠቁ ኃይሎች ጋር ውይይት መጀመሩን ይግለጹ እንጂ፤ ከየትኛው ቡድን ጋር የሚለው ግን አልገለፁም። ይህን አስመልክተን አስተያየታቸውን ከጠየቅናቸው የአማራ ክልል ነዋሪዎች አንዳንዶቹ ውይይት መጀመሩ መልካም ነገር እንደሆነ ሲያመለክቱ ሌሎች ደግሞ የተባለው እውነትነት ላይ ጥርጣሬ እንዳላቸው ነው የገለጹት።

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW