የሕዳሴ ግድብ፣ መገናኛ ዘዴዎችና የባለሙያ አስተያየት
ረቡዕ፣ ጳጉሜን 5 2017
ትናንት የተመረቀው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብየዓለም የምመገናኛ ብዙኃንን ትኩረት እስከዛሬም ድረስ እንደሳበ ነው። ሁሉም የዓለማችን ትልልቅ የቴሌቪሽንና የህትመት ሜዲያዎች የግድቡን ግንባታና መጠን በማድነቅ፣ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአካባቢው አገሮች ጭምር የሀይል ምንጭ የመሆን አቅም ያለው መሆኑን በመግለጽና ከሁሉም በላይ ግን ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እድገት ትልቅ እመርታ የሚፈጥር መሆኑን በሰፊው ገልጸዋል። ጋዜጦቹና መገናኛ ብዙኃኑ የታችኛው ተፋሰሥ አገሮች በተለይም ግብጽ ግን በግድቡ ግንባታ፤ የውኃ አሞላልና አስተዳደር ላይ ከፍተኛ ተቃውሞ ያላት በመሆኑ በሁለቱ አገሮች መካከል ያለው አለመግባባት ሊቀጥልና ሊያድግ እንደሚችልም ያላቸውን ስጋት አንስተዋል።
ግድቡ ታሪክ ለዋጭ ነው ስለመባሉ
ኢትዮጵያ ግን ከዚህ ግድብ መገንባትና ወደሥራ መግብት በጎላ ሌላ ምራፍ ውስጥ የምትገባ መሆኑንን በርክታ ባለሙያዎችም እየተናገሩ ነው። ደቡብ አፍርካ የሚገኘው የሴኩሪቲ ጥናት ተቋም ያፍርካ ቀንድ ተመራማሪ የሆኑት ሚስተር ሞሴስ ክሪስፐስ ኦኬሎ ግድቡን ታሪክ ለዋጭ ብለውታል።
ጥራትና ደረጃውን በሚመለክት የባለሙያ አስተያየት
ዲደብሊው የውኃ ሀብት መሀንዲስና የህዳሴው ግድብየባለሙያዎች አማካሪ ቡድን አባል የሆኑትን ዶክተር ጥሩ ሰው አሰፋን ስለዚህ ብዙ እየተነገረለት ስላለው የህዳሴ ግድብ ግንባታ፤ ጥራትና ደረጃ ተጨማሪ አስተያየት ጠይቆ ነበር። እሳቸው እንደሚሉት ግድቡ በዘመናዊ ቴክኖሎጂና ያለማቀፍ ባለሙያዎች የሰጧቸው አስተያየቶችም ተካተው የተሰራ በመሆኑ እስካሁን ካዩአቸው ግድቦች የተለየ ነው ።
ግብጽ በዚሁ ግድቡ በተመረቀበት ዕለት ጭምር ተቃውሞ ማሰማቷንና ለመንግስታቱ ድርጅት አቤት ማለቷን በማስታወስም፤ ኢትዮጵያ ወደ ታችኛው ተፋሰስ አገሮች የሚፈሰው ውሀ ሳይቀንስ ግድቡን መሙላት መቻሏ የግብጽን ጩኸት ሊቀንሰው ባይችልም ሰሚ አታገኝም`` በማለትም ለሁሉም የሚያዋጣው በመተባበር መስራትና መጠቀም መሆኑን አስታውሰዋል።
ገበያው ንጉሴ
ነጋሽ መሐመድ
ማንተጋፍቶት ሥለሺ