1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሕዳሴ ግድብ አራት ተርባይኖች ኃይል እያመነጩ ነው መባሉ

ሰኞ፣ ነሐሴ 20 2016

የኅዳሴ ግድብ ግንባታን ለማስተጓጎል ባለፉት ዓመታት የውጪ ኃይሎች “15 ሺሕ የሚጠጉ የተለያዩ ቡድኖች አሰማርተውብናል” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናገሩ። ዐቢይ የውጪዎቹንም ሆነ “ተሸጠዋል” ያሏቸውን የኢትዮጵያ ቡድኖች ማንነት አልተናገሩም። “ብዙ ጊዜ እና ገንዘብ አጥፍተዋል” ያሉት ዐቢይ ጉዳዩ “ለንግግር አይመችም” ሲሉ ተደምጠዋል።

የኅዳሴ ግድብ ውኃ የተኛበት ቦታ
የኅዳሴ ግድብ ውኃ የተኛበት ቦታ ወደ ኋላ ከ200 ኪሎ ሜትር በላይ እንደሆነ የገጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጥልቀቱ 133 ሜትር ደርሷል ብለዋልምስል AMANUEL SILESHI/AFP

የሕዳሴ ግድብ አራት ተርባይኖች ኃይል እያመነጩ ነው መባሉ

This browser does not support the audio element.

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሕዳሴ ግድብ አራት ተርባይኖች አሁን እየሰሩ መሆናቸውን ተናገሩ።´ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቀጣይ ሦስት ወይም አራት ወራት ውስጥ ተጨማሪ ሦስት ተርባይኖች ሥራ እንደሚጀምሩም በብሔራዊ ቴሌቪዥን በሰጡት ማብራሪያ ገልፀዋል።

ለታችኛው ተፋሰስ ሀገራት የግድቡ የውኃ ማስተንፈሻ በሮች ተከፍተው ተጨማሪ 2800 ሜትር ኪውብ ውኃ በሰከንድ ማፍሰስ መጀመሩንም አስታውቀዋል። ግድቡ የጣና ሐይቅን ሁለት እጥፍ ያህል ውኃ መያዙን፣ አጠቃላይ ሥራው ከዓመት በኃላ የክረምቱ  ወቅት ሲያበቃ ይጠናቀቃል ተብሎ እንደሚጠበቅም ገልፀዋል።


ግድቡ ከአንድ ዓመት በኋላ ይጠናቀቃል ተብሏል


ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ እስከ ቀጣዩ ዓመት ታኅሳስ ድረስ ግድቡ ከ70 ቢሊዮን ሜትር ኪዩብ በላይ ውኃ እንደሚይዝ፣ አጠቃላይ የግድቡ ግንባታ ከዓመት በኋላ እንደሚጠናቀቅ ገልፀዋል።

ግድቡ በኡሁኑ ወቅት ከ205 እስከ 210 ኪሎ ሜትር ቦታ  ወደኋላ ውኃ እንዲተኛ ማስቻሉን እና 62.5 ቢሊዮን ሜትር ኩዩብ ውኃ መያዙንም ገልፀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የግድቡ ይህን ያህል መጠን ውኃ መያዝ ለታችኛው የተፋሰስ ሀገራት "ትልቅ በረከት እና ሲሳይ ነው" ብለውታል።

 የኢትዮጵያ ሕዝብ ለሕዳሴ ግድብ 19 ቢሊዮን ብር ማዋጣቱ ተነገረ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ "መደማመጥ፣ መወያየት እና መተባበር ያስፈልጋል "ባሉበት ማብራሪያቸው "ሱዳንና ግብጽ ሊደግፉት የሚገባ ግድብ ነው ብለዋል። ያም ሆኖ ግን ግድቡ እዚህ ደረጃ የደረሰው "የተሸጡ እና የተገዙ፣ የእኛ" ያሏቸው ሰዎች የግድቡ ሥራ እንዳይቋጭ እንቅፋት ለመሆን ለፍተዋል ሲሉ ከሰዋል።

የታላቁ የኅዳሴ ግድብ አራት ተርባይኖች ኃይል በማመንጨት ላይ መሆናቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናግረዋል። ምስል Minasse Wondimu Hailu/AA/picture alliance

ከዚህም ባለፈ አንድ ተርባይን ከጅቡቲ ወደ ግድቡ ለማድረስ ከአንድ ወር ተኩል በላይ ጊዜ እንደሚፈጅ፣ ይሄው ዕቃ ሲጓጓዝ በየመንገዱ ፈንጅ እየተቀበረ ከባድ ፈተና ይታለፍ እንደነበርም ገልፀዋል።

የባለሙያ አስተያየት 

የግድቡ እዚህ ደረጃ ላይ መድረስ ለኢትዮጵያዉያን ምን ትርጉም አለው የሚለውን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የውኃ ምህንድስና ትምህርት ክፍል መምርህ እና የድርድሩ የቴክኒክ ቡድን አባል የሆኑትን ዶክተር በለጠ ብርሃኑን ጠይቀናቸዋል።

በናይል ወንዝ ላይም የብቻ ተጠቃሚነትን በፀና ሁኔታ ከሚያራምዱት የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ቀዳሚዋ ግብጽ አሁን የግድቡን ከዳር መድረስ ተከትሎ የአቋም ለውጥ ያደርጉ ይሆን? በሚል የጠየቅናቸው የውኃ ምህንድስና መምርህሩ ዶክተር በለጠ ይህ ነባራዊ ሁኔታ በተለይ ለግብጽ "ተጨማሪ ሥጋት ፣ተጨማሪ ጉዳይ ነው እየሆነ ያለው" ብለዋል።

 የህዳሴ ግድብ ድርድር ክሽፈት፣ የግብፅ «ዛቻ»

ከግድቡ በሚመረተው የኤሌክትሪክ ኃይል ልክ ማስፋፋትና ማዳረስ አሁን እንደማይቻልና ያንን ለማድረግ የሚያስፈልጉ መሠረተ ልማቶች እንደሚቀድሙ የገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ ግድቡ አሁን የገንዘብም ሆነ የቴክኒክ ሥጋት እንደሌለበት አስታውቀዋል።

ሰለሞን ሙጬ
እሸቴ በቀለ
ማንተጋፍቶት ስለሺ 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW