የመምሕሩ መታሰርና ሲፒጄ
ማክሰኞ፣ መስከረም 24 2009ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ መንግሥት በቅርቡ ያሰረዉ የአምቦ ዩኒቨርስቲ መምሕርና የአምደ መረብ ፀሐፊ ስዩም ተሾመ ባስቸኳይ እንዲለቀቅ ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት ጠየቀ። «ሲ ፒ ጄይ» በሚል የእንግሊዘኛ ምሕፃረ ቃል የሚጠራዉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት እንዳስታወቀዉ መምሕርና የአምደ መረብ ፀሐፊ ስዩም ተሾመ የታሰረዉ ባለፈዉ ዕሁድ ሳይሆን አይቀርም። ስዩም ሐሳቡን በነፃነት ከመግለፅ ሌላ የፈፀመዉ ወንጀል እንደሌለም ድርጅቱ አስታዉቋል። የዋሽግተን ዲሲዉ ወኪላችን በ«ሲ ፒ ጄይ» የምሥራቅ አፍሪቃ ተጠሪን አነጋግሮ የላከልን ዘገባ አለ።
መክብብ ሸዋ
ነጋሽ መሐመድ
አዜብ ታደሰ