1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የመስቀል በዓል አከባበር እና ትርጓሜው በኦሮሚያ ክልል

ሥዩም ጌቱ
ቅዳሜ፣ መስከረም 17 2018

በክርስትና ሃማኖት በተለይም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በታላቅ መንፈሳዊ ትርጉም የሚከበረው የመስቀል በዓል በኢትዮጵያ በተለያዩ አከባቢዎች እጅግ በሚወደድ ባህላዊ መልኩም በድምቀት ይከበራል፡፡

 ኦሮሚያ ክልል
የመስቀል በዓል አከባበር በኦሮሚያ ክልል ምስል፦ Seyoum Getu/DW

የመስቀል በዓል አከባበር እና ትርጓሜው በኦሮሚያ ክልል

This browser does not support the audio element.

 

በክርስትና ሃማኖት በተለይም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በታላቅ መንፈሳዊ ትርጉም የሚከበረው የመስቀል በዓል በኢትዮጵያ በተለያዩ አከባቢዎች እጅግ በሚወደድ ባህላዊ መልኩም በድምቀት ይከበራል፡፡መስቀል በድምቀት ከሚከበርባቸው አከባቢዎች አንዱ በሆነው በኦሮሚያ ልዩ ልዩ አከባቢዎች ከበዓልነቱም አልፎ የወቅት መቀየራ የተስፋ ጊዜ ተደርጎም የሚታይና በጉጉት የሚጠበቅ አውደ ዓመት ነው፡፡አቶ ድሪቢ ደምሴ በገዳ ስርዓት እና ባህል ላይ የተለያዩ ጥናትና ምርምር በማድረግ አራት መጽሃፍትን ጽፈዋል፡፡ ተመራማሪው የመስቀል አከባበርና የበዓሉን ታላቅነት ስገልጹ፤ “መስቀል በኦሮሞ ዘንድ የዓመት መለወጫ ወቅት ነው” ይላሉ፡፡ የክረምቱ ወቅት “አሊዋቶ” ወይም ወቅቶች የሚቀያየሩበት፤ ምድር በዝናብ ተሞልታ ፍሬን የሚሰጡ እጽዋትን የሚያበቅልበት በመሆኑ የዚህ ወቅት መቀየር የሚረጋገጠው በመስቀል ነው ይላሉም፡፡

የመስቀል መምጫ ወቅት

ወቅቶችን ጨምሮ ፈጣሪ ለሰው ሁሉ ለፍጥረትም ሁሉ የሚያስፈልገውን ፈጥሮ ሰጥቷል የሚል እምነት በኦሮሞ ዘንድ መኖሩን የሚገልጹት አቶ ድሪቢ፤ “በክረምቱ ወቅት የማብቂያ ጊዜያት በዝናብ መቀነስ ወንዞች እንደምቀንሱ ግልጽ ነው” በማለት የክረምቱ የመጨረሻ ወቅት ምድር በአበባ በሚታሸበርቅበት የክረምቱ ወቅት መደምደሚያመስቀል እንደሆነም አስረድተዋል፡፡

የመስቀል በዓል አከባበር በኦሮሚያ ክልል ምስል፦ Seyoum Getu/DW

የመስቀል አከባበር

በልዩ ጉጉት በሚጠበቀው በመስቀል እለት አከባበሩም የተለየ ነው የሚሉት የባህል ተመራማሪው አቶ ድሪቢ ደምሴ መስቀል የበዓል ሁሉ ንጉስ በሚል ከትውልድ በሚሸጋገር ተውፊት እንደሚከበርም አመልክተዋል፡፡ “በመስቀል እለት ሰው ሁሉ፤ እንኳን ሰው እንስሳም መትገብ አለበት ስለሚባል ከብቱ ሁሉ ያልተነካ ሳር ላይ ተሰማርተው የሚጠግብበት ነው” በማለትም ስርዓተ ደመራም በተለየ አከባበር የሚከበር መሆኑ ገልጸዋል፡፡

ስርዓተ ደመራው ሰው አንድ ላይ በጎሳ እና በሰፈር ከተከናወነ በኋላ በመስቀል እለት ለሚበራው እሳትም ልዩ ትኩረት ይሰጣል፡፡ “በመስቀል እለት በደመራ ከበራ እሳት ዓመቱን በሙሉ ሳይጠፋ እሳቱን የሚታቆይ ሴት ፀጋ ያት ተብሎ ስለሚታመን ልዩ ክብር ይሰጣታልም” በማለት በደመራው ጎመን እንኳ ቢሆን በዘንድሮ ዝናብ ከደረሰ ምርት ውስጥ በደመራው እንደሚቀርብ አመልክተዋልም፡፡

 

ስዩም ጌቱ

ታምራት ዲንሳ

ፀሐይ ጫኔ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW