1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የመስቀል እና የደመራ በዓል በኢትዮጵያ

ሰኞ፣ መስከረም 17 2008

የመስቀል በዓል በመላዉ ኢትዮጵያ በኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በደምቀት ተከበረ። በተለይ የአዲስ አበባ ከተማ በመስቀል አደባባይ በታላቅ ሃይማኖታዊ ሥርዓት ሲከበር ደመራ በመለኮሱ ሥነ-ስርዓት የኢትዮጵያና የግብጽ ኮፕቲክ ቤተ-ክርስትያን ፓትሪያርኮች እንዲሁም የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ ተገኝተዋል።

Äthiopien Das Meskel-Fest in Addis Abeba
ምስል DW/Y. Geberegziabeher

[No title]

This browser does not support the audio element.


በመስቀል አደባባይ በተካሄደዉ የደመራ ማብራት ሥነ-ስርዓት ላይ የተገኘዉ ወኪላችን ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር ዘገባ ልኮልናል። በሌላ በኩል በኢትዮጵያ የመስቀል በዓል በድምቀት ይከበራል። በተለይ በጉራጌ ብሔረሰብ በዓሉን ለማክበር ሁሉም በትዉልድ ስፍራዉ በመሰባሰብ ከዘመድ ወላጅ ምርቃትን ይቀበላል፤ የመስቀል በዓልን አስታኮም ቢያንስ በዓመት አንድ ጊዜ ቤተሰቦቹን ዘመድ ወዳጆቹን ይጎበኛል። የመስቀል አከባበር ባህላችን ተሸረሸረ፣ ተረሳ በማለት የጥንት የአከባበር ልማዱን መልሶ ለማደስ ወደ 2 ሺህ እድምተኞች በተገኙበት አንድ ማኅበር መመስረቱ ተሰምቷል። ጌታቸዉ ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ በጉራጌ ማኅበረሰብ የመስቀል አከባበርና አዲስ ተመሰረተ ስለተባለዉ ማኅበር ዝግጅቱ ላይ የተገኙትን ተካፋዮች በማነጋገር ዘገባ ልኮልናል።

ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር

ጌታቸዉ ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

ሸዋዬ ለገሰ

ምስል DW/Y. Geberegziabeher
ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW