1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የመስቀል ደመራ በአል አከባበር በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢዋ

አበበ ፈለቀ
ዓርብ፣ መስከረም 17 2017

የመስቀል ደመራ በአል በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢዋ በደማቅ ስነስርዓቶች ትናንት ተከብሯል። በበአሉ ላይ የተገኙት የሃይማኖት አባቶችና ምዕመናን በኢትዮጵያ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው መድረስ አስፈላጊ መሆኑን አጽንዖት ሰጥተዋል። በኢትዮጵያ ሰላም እንዲሰፍንያላቸውን ምኞትም ገልጸዋል።

USA | Äthiopische Gemeinde in Washington DC feiert Meskel
ምስል Abebe Feleke/DW

የመስቀል ደመራ በአል አከባበር በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢዋ

This browser does not support the audio element.


የመስቀል ደመራ በአል በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢዋ በደማቅ ስነስርዓቶች ተከበረ። በተለይም በሜሪላንድ ግዛት በሰሜን አሜሪካ የዋሽንግተን ዲሲና አካባቢዋ ሃገረ ስብከት ሊቀጳጳስ አቡነ ፋኑኤል በተገኙበት በሰባት አብያተ ክርስትያናት ታዳሚነት ነው የተከበረው። በበአሉ ላይ የተገኙት የሃይማኖት አባቶችና ምዕመናን በኢትዮጵያ ለሚገኙ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው መድረስን አስፈላጊነት አጽንዖት የሰጡ ሲሆን፣ በኢትዮጵያ ሰላም ሰፍኖ ለማየትያላቸውን ምኞት ገልጸዋል።
የመስቀል ደመራ በአል በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢዋ በደማቅ ስነስርዓቶች ተከበረ። በተለይም በሜሪላንድ ግዛት በሰሜን አሜሪካ የዋሽንግተን ዲሲና አካባቢዋ ሃገረ ስብከት ሊቀጳጳስ አቡነ ፋኑኤል በተገኙበት በሰባት አብያተ ክርስትያናት ታዳሚነት ነው የተከበረው። በበአሉ ላይ የተገኙት የሃይማኖት አባቶችና ምዕመናን በኢትዮጵያ ለሚገኙ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው መድረስን አስፈላጊነት አጽንዖት የሰጡ ሲሆን፣ በኢትዮጵያ ሰላም ሰፍኖ ለማየት ያላቸውን ምኞት ገልጸዋል።

የመስቀል በዓል አከባበር በዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው።ምስል Abebe Feleke/DW

ትላንት ማምሻውንየመስቀል ደመራ በአል በዲሲና በአካባቢዋ በደመቀ ሁኔታ ነው የተከበረው። በቨርጂኒያ ያሉ አብያተ ክርስትያናት በቨርጂኒያው ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስትያን ታድመው በጋራ አክብረዋል። የዋሽንግተን ዲሲ አብያተ ክርስትያናት ደግሞ በዲሲው ደብረምህረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስትያን ተሰባስበው አክብረዋል። ሜሪላንዶች ደግሞ በሜሪላንዷ ሆህተ ምስራቅ ቅድስት ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስትያን አክብረዋል። ቤተክርስትያኒቱ ለመግዛት እየተደራደረችበት በሚገኘው ሰፊ ቦታ ላይ በደመቀ ሁኔታ ነው ያከበሩት ።
መላከ አርያም ብርሃኑ ጎበና፣ የዲሲና የአካባቢዋ ሃገረ ስብከት ዋና ጸሃፊና የኪዳነ ምህረት ቤተክርስትያን አስተዳዳሪ ቦታው እጅግ ሰፊ በመሆኑ በርካታ መዕመናን መገኘታቸውን ጠቁመዋል። መላከ አርያም ብርሃኑ ልክ እዚህ ያሉ መዕመናን በዓሉን በሰላም እንዳከበሩት ሁሉ፤ ለኢትዮጵያም ሰላምና ፍቅር ይሰፍንላት ዘንድ ተመኝተዋል።

የመስቀል በዓል አከባበር በዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው።ምስል Abebe Feleke/DW

አመት በዓሉን ከሚያከብሩት ምዕመናን  ውስጥ አንዷ ወ/ሮ ጽጌ ከ13 አመታት በላይ በሜሪላን ነዋሪ እንደሆነች ገልጻ፣ ምንም ይሁን ምን ከሃገር ርቆ በዓልን ማክበር ቅር የሚለው ነገር እንዳለ ገልጻለች። ያም ሆኖ በዚህ ሰዓት በተለያዩ ምክንያቶች ችግር ላይ ላሉ ወገኖች ድጋፍ የማድረግ ባህልን አበረታታ፣ ለሃገር ለወገን ሰላምን ተመኝታለች።
ሌላው የበዓሉ ታዳሚ አቶ ይሄነው አንዷለም ወደ አሜሪካ ለጉብኝት የመጡ እንግዳ ናቸው። በበዓሉ የመታደማቸውን ደስታም አልሸሸጉም። አቶ ሄኖክ ተፈራ በበኩላቸው በዓሉ እጅግ በደመቀ መልኩ መከበሩን ገልጸዋል። ወ/ሮ ታደለች ለማ ኑሯቸውንኢትዮጵያ ያደረጉ፣ እዚህ ልጃቸውን ሊጠይቁ የሚመጡ መሆናቸውን ገልጸዋል። በአሉን እዚህ ቢያከብሩም ልባቸው ሃገራቸው ላይ ነውና መረዳዳትና መደጋገፍ ግድ ነው ብለዋል።
በዚሁ በሜሪላንድ ሆህተ ምስራቅ ቅድስት ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስትያን ተገኝተው ቃለ ቡራኬ የሰጡት፣ ሰባቱን አብያተ ክርስትያናት እየመሩ ደመራውንም ያስለኮሱት የዋሽንግተን ዲሲና አካባቢዋ ሃገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ብጹዕ አቡነ ፋኑኤል ናቸው። ብጹዕነታቸው አምላክ ሰላምን፣ ፍቅርንና አንድነትን ያምታልን ብለዋል።  

አበበ ፈለቀ
ታምራት  ዲንሳ
ፀሐይ ጫኔ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ
ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW