1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የመስከረም 23 ቀን 2015 የስፖርት መሰናዶ

ሰኞ፣ መስከረም 23 2015

በለንደን ማራቶን ኢትዮጵያዊቷ ያለምዘርፍ የኋላው አሸናፊ ሆናለች። በወንዶች ኬንያዊው አሞት ኪፕሮት አንደኛ ኢትዮጵያዊው ልዑል ገብረስላሴ ሁለተኛ ወጥተዋል። በጣልያን በግማሽ ማራቶን በተካሔዱ ውድድሮች ታምራት ቶላና ብሩክታዊት ደገፋው አሸንፈዋል። ኢትዮጵያ እና አልጄሪያ ለቻን ውድድር በአንድ ምድብ ተደልድለዋል።

Premier League | West Ham United v Manchester City
ምስል David Klein/Newscom/picture alliance

የመስከረም 23 ቀን 2015 የስፖርት መሰናዶ

This browser does not support the audio element.

በሳምንቱ መጨረሻ በተለያዩ የአውሮፓ እና የእስያ ከተሞች የአትሌቲክስ ውድድሮች ተካሂደዋል። ከ40ሺህ በላይ ተወዳዳሪዎች የተካፈሉበት የለንድን ማራቶን ውድድር በሴቶች አትሌት ያለምዘርፍ የኋላው አሸፊ ሆናለች። የ23 አመቷ አትሌት ያለም ዘርፍ ርቀቱን 2 ሰዓት ከ17 ደቂቃ ከ25 ሰከንድ በሆነ ሰዓት ጨርሳለች። ይህ ሰአት በለንደን ማራቶን ሶሰኛው ፈጣን የሴቶች ሰአት ሆኖ ተመዝግቧልል። ኬንያዊትዋ አትሌት  ጂፕ ኮስጊ ሁለተኛ ስትሆን አለም መርጊያ ሶስተኛ በመሆን አጠናቃለች።
በወንዶች የማራቶን ውድድር ኬንያዊው አትሌት ኣሞስ ኪፕሮቶ በ2 ሰኣት ከ4 ደቂቃ ከ39 ሰከንድ ውድድሩን ያጠናቀቀ ሲሆን ልኡል ገብረስላሴ በ33 ሰከንድ ተቀድሞ ሁለተኛ ሆንዋል። ሶስተኛ በመሆን ውድድሩን ያጠናቀቀው ቤልጂየማዊው አትሊት ሲሆን ክንዴ አጥናው እና አትሌት ቀነኒሳ በቀለ 4ኛ ና 5 ኛ በመሆን ውድድሩን አጠናቀዋል። 
በጣልያን የግማሽ ማራቶን እና የ10 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድሮችን ኢትዮጵያ አትሌቶች በበላይነት አጠናቀዋል። የዓለም ሻምፒዮናው አትሌት ታምራት ቶላ እሁድ በጣልያን ትሪንቶ ከተማ ባደረገው የግማሽ ማራትን ውድድር ሲያሽንፍ አዲስ የቦታውን ሰዓት በመስመዝገብ ጭምር ነው።  በተመሳሳይ በተደረገ የሴቶች ውድድር አትሌት ብሩክታይት ደገፋው 1 ሰአት ከ 09 ደቂቃ 41 ሰከንድ በመግባት የጣልያኑን ግማሽ ማራቶን ኣሽናፊ ሆናለች 
በ10 ኪሎ ሜትር  ርቀት በተደረገው ውድድር ደግሞ አትሌት ሙክታር ኢድሪስ አእሽናፊ ሆኗል። በሌላ የአትሌቲክስ ውድድር  ዜና በስሎቫኪያ በተደረገ የማራቶን ውድድር በወንዶች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ኬንይዊውን አትሌት ሩብን ኪፕሮፕን ተከትለው በመግባት አሸናፊ ሆነዋል ።ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አያቸው ባንቲ፣ ዮናስ መካሻ እና አዳነ ከበደ እንደ ቅደም ተከተላቸው ከሁለተኛ እስከ አራተኛ ያለውን ደረጃ በመያዝ  ውድድራቸውን  አጠናቀዋል።  

አፍሪካ ሻንፒየንስ ሊግ የቻን ውድድር  የምድብ ድልድል 

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በአፍሪካ ሻንፒዮስ የቻን ውድድር  ከኣስተናጋጇ ሀገር  አልጀሪያ ጋር  በምድብ ሀ   ተደልድለዋል። በ2023 በአልጄሪያ አስተናጋጅነት የሚከናወነው የቻን ውድድር ለመጀመሪያ ጊዜ በ18 ብሔራዊ ቡድኖች መካከል ከጥር 5 -27 ድረስ እንደሚከናወን ይጠበቃል። በሳምንቱ መጨረሻ በተከናወነው የአፍሪካ ሀገራት ቻምፒየንሺፕ (ቻን)  ጨዋታ የዕጣ ማውጣት ስነስርዓት 18 ሀገራት በ5 ምድብ ተደልድለዋል። ሶስት ምድብ እያንዳንዳቸው 4 ሀገራት ሲይዙ ሁለቱ ደግሞ 3 3 ሀገራት ይዘዋል። በወጣው እጣመሰረት ኢትዮጵያ ከ አተናጋጇ ሀገር አልጀሪያ ጋር በምድብ ሀ ተደልድላለች።  
በሳምንቱ መጨረሻ ከተካሄዱት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች መከከል የሁለቱ ማንችስተሮች ጨዋታ በእጅጉ መነጋገሪያ ሆኗል። በኢትሀድ ስታድየም የተካሄደው የማንችስተር ደርቢ ጨዋታ ሁለት ተጫዋቾች ሀትሪክ የሰሩበት የዩናይትድ ጎል የውሀ መንገድ የሆነላቸው በተቃራኒው ማን ዩናትድ በሽንፍት የደቀቀበት ነብር ። 
የሰሜን ለንደኖቹ አርሰናል እና ቶትንሀም በኤምሬትስ ስታድየም ያደረጉት ጨዋታ በአርሰናል አሽናፊነት ተጠናቅዋል። የፕርምየር ሊጉ መሪ አርሰናል ቅዳሚ የነበረበትን የደርቢ ጨዋታ 3 ለ 1 ማሽነፉ ፕሪምየር ሊጉን በአንድ ነጥብ እንዲመራ አስችሎታል።  በሰልህስት ፓርክ የተደረገው የክሪስታል ፓላስ እና የቸልሲ ጨዋታ በቸልሲ 2 ለ አንድ የበላይነት ተጠናቋል። 
9 ኛ ሳምቱን በያዘው በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ  አርሰናል በ21 ነጥብ ሲመራ ማንችስተር ሲቲ በ20 ነጥብ ሁለተኛ ነው። ቶትንሀም በ17 ነጥብ ሶስተኛደረጃ ላይ ይገኛል። ዎልቨር ሀምፕተን ፣ኖቲንግሀም እና ሌስተር ሲቲ እንደቅደም ተከተላቸው የወራጅ ቀጠና ላይ ይገኛሉ። 
ወደ ማዮርካ ተጉዞ የነበረው ባርሴሎና በሎቫንዶቭስኪ ጎል 3 ነጥብ ይዞ ከመውጣቱም በሻገር በላሊጋውን በመሪነት እንዲሰነብት አስችሎታል። ባርሴሎና ተቀናቃኙን ያሽነፈበት ብቸኛ ጎል የተመዘገበው ከረፍት በፊት በ20ኛው ደቂቃ ላይ በሮበርት ሎቫንዶቭስኪ ነበር። ከረፍት መልስ  ተጨማሪ ጎል ሳይመዘገብ ጨዋታው በባርሳ  1ለ0 አእሽናፊነት ተጠናቋል። በተቀሩት የፕሪምየራ ሊጋ ጨዋታዎች ጊቲቭ በሪያል ቫላዶሊድ 2 ል3  ሲቪላ በአትሌቲኮ ማድሪድ 2 ለ0 ረተዋል
ከስፒን ላሊጋ ወደ ጀርመን ቡንዲስ ሊጋ የሳምቱ ጨዋታዎች ስናቀና  ኮለን ቦሪስያ ዶርትመንድን 3 ለ 2 ረትዋል። ፍራክፈርት የቡንዲስ ሊጋውን መሪ ዩንየን በርሊንን 2ለ 0 ረትዋል።   
የሜዳ ቲንስ 
በእስራኤል ሲካሀድ በነበረው የቲላቪቨ ኦፕን የሜዳ ቲንስ  ኖቫክ ጃኮቪች አሽነፊ ሆንዋል  ከዊንብልደን ድሉ በሁዋላ ለመጀምሪያ ግዜ ያሽነፈው ጃኮቪች ኮሮና ቫይረስ ክትባት አቁዋሙ ምክኛት የአሜሪካው ኦፕን የሚዳቲንስ ውድድር ሳይካፈል ቅረቱ ይታወሳል  ከሶስት ወራት የውድድር ቆይታ በሁዋላ ለፍፃሜውድድር ይረበቃው 35 አመቱ ጃኮቪች ተጋጣሚውን አሪን ቺሊንቺን   የረታው 6ለ3 6 ለ 4 በአጠቃልይ 2ለ0 በሆነ ውጤት ነው።
በኢንዶኔዥያ በምሥራቅ ጃቫ  ማላንግ  ከተማ  በሜዳው  ይጫውት የነብረው አሬማ  እግርኩዋስ ቡድን በተጋጣሜው የደረሰበት  የ 2ለ 3  ሽንፈት ተከትሎ ግጭት መከሰቱን  ተዘግቡዋል በግጭቱ ምክንያትም ህይወታቸው ማለፍይ ከነገረው 125 ሰዎች በተጨማሪ ቢያንስ 180 ያህል ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ ግጭቱ የተከሰተው  ዳኛው የጨዋታውን ማብቂያ ፊሽካ ካሰሙ በሁዋ የቡድናቸን ሽንፈ ያበሳጫቸውና ወደሚዳ የገቡ ተመልካቾችን ለመበተን ፖሊስ ያስለቃሽ ጭስ  ከተኮሰ በሁዋላ ነው በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከስቴዲየሙ ለመውጣት በፈጠሩት መገፋፋት ብዙዎች መታፈናቸው ታውቆዋል፡፡ የኢንዶኔዥያው ፕሪዝዳንት ምርመራ እስከሚደረግ ድረስ በ ሀገራቸው የሚደረጉ የ ከፍተኛ ሊግ  ጨዋታዎች በሙሉ እንዲቆሙ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል ፡፡
ሐና ደምሴ 
እሸቴ በቀለ
 

በኢንዶኔዥያ በምሥራቅ ጃቫ  ማላንግ  ከተማ  በሜዳው  ይጫውት የነብረው አሬማ  እግርኩዋስ ቡድን በተጋጣሜው የደረሰበት  የ 2ለ 3  ሽንፈት ተከትሎ ግጭት መከሰቱን  ተዘግቡዋል በግጭቱ ምክንያትም ህይወታቸው ማለፍይ ከነገረው 125 ሰዎች በተጨማሪ ቢያንስ 180 ያህል ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ምስል Yudha Prabowo/AP/picture alliance
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በአፍሪካ ሻንፒዮስ የቻን ውድድር  ከኣስተናጋጇ ሀገር  አልጀሪያ ጋር  በምድብ ሀ   ተደልድለዋል። ምስል Haimanot Turuneh/DW
ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW