1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የትግራይ ክልል የጤና ችግር፣ የመድሕን ዕቅድ

ዓርብ፣ የካቲት 14 2017

አስቀድሞ በቀላሉ መቆጣጠር ይቻሉ የነበሩ እና የስርጭት መጠናቸው ዝቅተኛ ሆኖ የነበረ እንደነ ወባ እና ኤችአይቪ ጨምሮ ሌሎች በሽታዎች የሕብረተሰብ ጤና ስጋት ሆነው ያሉ ሲሆን አሁን ላይ ደግሞ በመቐለ ጨምሮ በሌሎች አካባቢዎች የህፃናት ልምሻ ወይም ፖልዩ እየታየ መሆኑ የትግራይ ጤና ቢሮ ገልጿል።

በትግራይ ክልል የጤና ተቋማት መዉደም፣ የመድሐኒና የሕክምና ቁሳቁሶች እጥረት ሕዝቡ ሕክምና ለማግኘት እየተቸገረ መሆኑን ነዋሪዎች ይናገራሉ።
በትግራይ ጦርነቱን ተከትሎ በተፈጠረ ውድመት በተለይ የጤና አገልግሎት በከፋ ሁኔታ ተጎድቷል። አስቀድሞ በቀላሉ መቆጣጠር ይቻሉ የነበሩ ወባና እና ኤችአይቪ ጨምሮ ሌሎች በሽታዎች የሕብረተሰብ ጤና ስጋት ሆነዋልምስል፦ Million Haileselasie/DW

የትግራይ ክልል የጤና ችግር፣ የመድሕን ዕቅድ

This browser does not support the audio element.

 

በትግራይ ክልል የጤና አገልግሎትን ለማዳረስ ይረዳል የተባለ የጤና መድህን ፕሮግራም እንደሚጀምር የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ።በክልሉ በጦርነቱ ምክንያት የተጎዳው የጤና ስርዓት ወደነበረበት ለመለስ ጥረቶች ቢቀጥሉም የበሽታዎች ስርጭት አሳሳቢ ሆኖ ይገኛል። የመድሃኒቶች እና የሌሎች የሕክምና ግብአቶች አቅርቦት እጥረት የጤና ባለሙያዎች ውሱንነት የክልሉ የጤና ስርዓትን እየፈተኑ ካሉ ችግሮች መካከል ናቸው ተብሏል።

 

በትግራይ ጦርነቱ ተከትሎ በተፈጠረ ውድመት በተለይ የጤና አገልግሎት በከፋ ሁኔታ ተጎድቷል። አስቀድሞ በቀላሉ መቆጣጠር ይቻሉ የነበሩ እና የስርጭት መጠናቸው ዝቅተኛ ሆኖ የነበረ እንደነ ወባ እና ኤችአይቪ ጨምሮ ሌሎች በሽታዎች የሕብረተሰብ ጤና ስጋት ሆነው ያሉ ሲሆን አሁን ላይ ደግሞ በመቐለ ጨምሮ በሌሎች አካባቢዎች የህፃናት ልምሻ ወይም ፖልዩ እየታየ መሆኑ የትግራይ ጤና ቢሮ ገልጿል። 

በመቐለ የታየው የህፃናት ልምሻ ወይም ፖልዩ አምጪ ቫይረስ ተከትሎ ከነገ ጀምሮ ከአምስት ዓመታ በታች ለሆኑ ህፃናት የክትባት ዘመቻ እንደሚጀምር የትግራይ ጤና ቢሮው አስታውቋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በትግራይ የተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ ጤና ተቋማት አብዛኞቹ በከፊል ወደ ስራ ቢመለሱም፥ በመድሃኒቶች እና የሕክምና መሳርያዎች እጥረት እንዲሁም በሕክምና ባለሙያዎች ውሱንነት እየተፈተኑ ነው። ተገልጋዮች እንደሚሉት ጤና ጣብያዎች እና ሆስፒታሎች በሚጠበቅባቸው ሁኔታ እያገለገሉ አይደለም።

ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ በትግራይ የሕክምና ባለሙያዎች ፍልሰታ ይበልጥ አሳሳቢ እየሆነ እንዳለ በተገልጋዮች እና በጤና ዘርፉ ዙርያ ባላ ተቋማት በተደጋጋሚ ይገለፃል።

በርካታ ችግሮች እየገጠሙት ያለው የትግራይ ጤና ስርዓትለማሻሻል፥ የእርዳታ ለጋሾች ድጋፍ እንደሚጠበቅም የክልሉ መንግስት ይገልፃል። ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ በክልሉ ከጦርነቱ በፊት የነበሩ የጤና አገልግሎቶች የመመለስ ስራ እየተከወነ መሆኑ የትግራይ ጤና ቢሮ የሚገልፅ ሲሆን፥ ከነዚህ መካከል የሆነ የጤና መድህን የተባለ ፕሮግራም ለመመለስም እንቅስቃሴዎች መጀመራቸው አስታውቋል።

መቀሌ ዉስጥ የሚገኘዉ የትግራይ ክልል የአይደር ሪፈራል ሆስፒታል በከፊል።እንደ ብዙዎቹ የክልሉ የጤና ተቋማት ሁሉ አይደር ሆስፒታልም ችግር አጋጥሞታል።ምስል፦ Million Haileselasie/DW

በትግራይ ሊጀመር የታቀደው የጤና መድህን ፕሮግራም አጥኚዎች  እንደሚሉት፥ የአገልግሎቱ አባል የሚሆኑ አካላት የሚጠበቅባቸው ዓመታዊ ክፍያው በእያንዳንዱ ተገልጋይ እና ቤተሰብ የኑሮ ሁኔታ የሚወሰን ሲሆን ከዝቅተኛ 720 ብር እስከ ከፍተኛ 1930 ብር ይደርሳል ተብሏል። የትግራይ ጤና ቢሮ ሐላፊ ዶክተር አማኑኤል ሃይለ "የጤና መድህን ፅንሰ ሐሳብ በርካታ አባላት ይኖርህና ከእነዛ ውስጥ 20 ወይ 30 በመቶ ከታመመ በተዋጣው ገንዘብ ይገለገላል ማለት ነው። በህዝቡ ዘንድ ፍላጎቱ እንዳለ ቢታወቅም የመክፈል አቅም ግን አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል" ይላሉ።

ጦርነቱ በትግራይ በሚገኝ የጤና መሰረተ ልማት እና አጠቃላይ የጤና ስርዓት ከፍተኛ ውድመት ማስከተሉ የዓለምአቀፉ ተቋማት እና የትግራይ ጤና ቢሮ መረጃዎች ያመለክታሉ። በጦርነቱ ወቅት 80 ከመቶ በሚሆኑ የትግራይ ጤና ተቋማት ላይ በተለያየ ደረጃ የሚገለፅ ውድመት መድረሱ የክልሉ ጤና ቢሮ መረጃ የሚያመልክት ሲሆን፥ እነዚህ ተቋማት ወደ ስራ የመመለስ ስራም ሂደት ላይ መሆኑ ተነግሯል።

ሚሊዮን ኃይለሥልሴ 

ነጋሽ መሐመድ

ኂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW