የመቀሌው የሱሰኞች ማገገሚያ
ማክሰኞ፣ ሐምሌ 5 2008ማስታወቂያ
በመቀሌ ዩኒቨርስቲ ስር የተቋቋመው የሱሰኞች ማገገሚያ ተቋም ከመላው ሃገሪቱ ለሚመጡ የሱስ ተጠቃሚዎች የህክምና አገልግሎት እየሰጠ ነው ። በማዕከሉ ህክምና እና የምክር አገልግሎት የተሰጣቸው ታካሚዎች ለዶቼቬለ እንደተናገሩት ከሱስ እየተላቀቁ እና ህይወታቸውም እየተቀየረ ነው ። የሲጋራ የጫት የመጠጥ እና የልዩ ልዩ የአደንዛዥ እጽ ሱሰኞችን የሚያክመውን ይህን ማዕከል ወደፊት የማስፋፋት እቅድ አለ ። ማዕከሉን የጎበኘው ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሄር ተከታዩን ዘገባ አጠናቅሯል ።
ዮሐንስ ገብረ እግዚዘብሔር
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ