የመቀሌ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከቤተሰቦቻቸዉ ተገናኙ
ማክሰኞ፣ ሐምሌ 20 2013ማስታወቂያ
መቀሌ-ትግራይ ዩኒቨርስቲ ይማሩ የነበሩ ከ700 በላይ ተማሪዎች አፋር ክልል በሚገኘዉ በሰመራ-ዩኒቨርስቲ በኩል ቤተ-ሰቦቻቸዉ ወደየሚገኙበት አካባቢ መጓዛቸዉ ተነገረ። ትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች የሚማሩ ተማሪዎች ከየቤተሰቦቻቸዉ ጋር እንዲቀየጡ የተባበሩት መንግስታት ይረዳቸዉ ዘንድ የተማሪዎቹ ወላጆችና ቤተሰቦች ባለፈዉ ሳምንት አዲስ አበባ ዉስጥ ባደረጉት ሰልፍ ጠይቀዉ ነበር። የአፋር ክልልላዊ መንግስት ለዶቼ ቬለ እንደገለፀዉ በሁለት ዙር ጉዞ ሠመራ የገቡት ተማሪዎች 725 ናቸዉ።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ሰለሞን ሙጬ ያነጋገራቸዉ የተማሪዎቹ ወላጆች እንዳሉት ደግሞ ተማሪዎቹ ሠመራ የገቡት ከብዙ ችግር በኋላ ነዉ።
ሰለሞን ሙጬ
ነጋሽ መሐመድ
ሸዋዬ ለገሠ