1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የመቅደላ ዩኒቨርስቲ የመካነ ሰላም ካምፓስ ሊከፈት ነዉ

ኢሳያስ ገላው
ማክሰኞ፣ መስከረም 13 2018

በአማራ ክልል ያለው የፀጥታ ችግር በዘላቂነት መፍትሄእስኪያገኝ ድረስ በመቅደላ አምባ ዩኒቨርስቲ መካነሰላምካምፓስ ተዘግቶ መቆየት የለበትም የሚሉ ነዋሪዎች ተመሳሳይየፀጥታ ሁኔታ ላይ ያሉ ዩኒቨርስቲዎች የመማር ማስተማርሥርዓቱን በመቀጠላቸው መካነ ሰላም ካምፓስ ሊከፈት ይገባልየሚል ተደጋጋሚ ጥያቄዎችን ጠይቀናል ይላሉ፡፡

የኢትዮጵያ ትምሕርት ሚኒስቴር ዋና መስሪያ ቤት አዲስ አበባ።በአማራ ክልል የሚገኘዉ የመቅደላ ዩኒቨርስቲ  የመካነ ሰላም ካምፓስ ሊከፈት ነዉ
የኢትዮጵያ ትምሕርት ሚኒስቴር ዋና መስሪያ ቤት አዲስ አበባ።በአማራ ክልል የሚገኘዉ የመቅደላ ዩኒቨርስቲ የመካነ ሰላም ካምፓስ ሊከፈት ነዉምስል፦ Alemnew Mekonnen/DW

የመቅደላ ዩኒቨርስቲ የመካነ ሰላም ካምፓስ ሊከፈት ነዉ

This browser does not support the audio element.

 

በፀጥታ ችግር ምክንያት ለሁለት አመታት የተዘጋዉየመቅደላ አምባ ዮንቨርስቲ መካነ ሰላም ካምፓስ ዘንድሮ ተማሪዎች እንደሚቀበል የዩኒቨርስቲዉ ባለሥልጣናት አስታወቁ።ዩኒቨርስቲዉ ላለፉት ሁለት ዓመታት መዘጋቱን የአካባቢዉ ነዋሪዎች ሲቃወሙ ነበር።ነዋሪዎቹ እንደሚሉት የዩኒቨርስቲዉ መዘጋት ተፅዕኖ አሳድሮባቸዋል።በ2010 ዓ/ም የመማር  ማስተማር ስራውን የጀመረው የመቅደላአምባ ዩኒቨርስቲ መካነ ሰላም ካምፓስ ባለፉት 2ዓመታት በአማራ ክልል በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ምክንያት ሥራውተቋር ቆይቷል፡፡ ዩኒቨርስቲው ስራውን ማቋረጡ ደግሞበአካባቢው ማህበረሰብ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴላይ የጎላ ጉዳት አድርሷል የሚሉት የመካነ ሰላም ከተማነዋሪዎች ዩኒቨርስቲው እንዲዘጋ የሚያደርግ ከባድ የጸጥታችግር በአካባቢው አልነበረም ይላሉ፡፡ 

‹‹ከባድ ነገር ተፈጥሮ አልነበረም የተዘጋው ምክንያቱም ሌላቦታ ያሉ ዩኒቨርስቲዎች ከተማ ውስጥ የጸጥታችግርእየተፈጠረ ሲያስተምሩ ነበር፡፡ ደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲአልተዘጋም፤ የዚህ ግን ሆን ተብሎ ተቋርጦየነበረው፡፡›› 

በፀጥታ ችግር ምክንያት ማስተማር ያቆመዉ ዮንቨርሲቲ

አሁን በአማራ ክልል ያለው የፀጥታ ችግር በዘላቂነት መፍትሄእስኪያገኝ ድረስ በመቅደላ አምባ ዩኒቨርስቲ መካነሰላምካምፓስ ተዘግቶ መቆየት የለበትም የሚሉ ነዋሪዎች ተመሳሳይየፀጥታ ሁኔታ ላይ ያሉ ዩኒቨርስቲዎች የመማር ማስተማርሥርዓቱን በመቀጠላቸው መካነ ሰላም ካምፓስ ሊከፈት ይገባልየሚል ተደጋጋሚ ጥያቄዎችን ጠይቀናል ይላሉ፡፡ 

‹‹ተደጋጋሚ በነበሩ ስብሰባዎች ላይ ዩኒቨርስቲ ይከፈትልንሰላሙ ላይ ያለው ነገር ለዘላቂነት መፍትሄ እስኪያገኝድረስእንደማንኛውም አካባቢ ዩኒቨርስቲ መከፈት አለበት አሁንእንደአጠቃላይ አማራ  ክልል ተመሳሳይ ወቅታዊችግር ነውያለውና የእኛ ተነጥሎ ለምን ተዘጋ የሚል ትልቅ ቅሬታ ስናነሳነበር፡፡›› 

የመቅደላ ዩኒቨርስቲ መካነሰላም ካምፓስ መከፈት የንግዱንማህበረሰብ እንቅስቃሴ ወደላቀ ደረጃ ከማሸጋገሩም ባለፈበርካታ የሥራ እድል መፍጠሩ ነው የመካነ ሰላም ከተማነዋሪዎች የሚገልፁት፡፡ 

‹‹የዩኒቨርስቲው መዘጋት ከፍተኛ ተፅዕኖ ነው የፈጠረብንለምሳሌ፡- ነጋዴ ነኝ እኔ ዩኒቨርስቲው በመከፈቱ ብዙጥቅምአግኝቼ ነበር፡፡ በመዘጋቱ ግን ስራዎች ተቀዛቀዙ፤ ተማሪውእዚህ መሆን ለከተማው ከፍተኛ ጠቀሜታነበረው፡«ዩኒቨርስቲው ከተዘጋ በኋላ ግን ኢኮኖሚውን አውርዶታል፡፡›› 

በዘንድሮዉ የትምህርት ዘመን ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጂት ተደርጓል 

ባለፉት 2 ዓመታት በአካባቢው በመንግስት እና በፋኖ ሀይሎችመካከል ሲደረግ የነበረው ጦርነት ምክንያት ሥራውየተቋረጠው በመቅደላ አምባ ዩኒቨርስቲ መካነሰላም ካምፓስዘንድሮ ከመስከረም 15 ጀምሮ ተማሪዎችን ይቀበላል ያሉት አቶአብድሮህማን አወል የካምፓሱ ዳይሬክተር ሰላም ማጣት ብዙዋጋ እንደሚያስከፍል የተረዳንበት ነው ይላሉ፡፡ 

‹‹መስከረም 15 /2017 ዓ/ም ተማሪ ይገባል ዝግጅት ጨርሰናል፤ በፀጥታ ችግር ምክንያት የተዘጋ ስለነበር አሁንአስተማማኝፀጥታ ስላለ ማስተማር ትችላላችሁ ተብለናል፡፡ እኛተማሪዎችን ጠርተናል፤ ምንም ችግርአይገጥማቸውምማህበረሰቡ ዝግጁ ነው፡፡ ተቋማችን ተዘጋጅቷል ፤ ትልቅተፅዕኖ አሳድሮብናል፡፡ ይህ እንግዲህየሰላም ችግር  ነው፤ ሰላም ምን ያህል ዋጋ እንደሚያስከፍል ማህበረሰቡም ሆነሌላው አካል የተረዳውይመስለኛል፡፡›› 

የአማራ ክልል የትምሕርት ቢሮ አርማ።በአማራ ክልል መቅደላ ዩኒቨርስቲ የመካነ ሰላም ካምፓስ ሊከፈት ነዉ ምስል፦ Amhara Region Education Office

ከጎንደር ዮንቨርሲቲ የተወሰደ ተሞክሮ

በዋናነት ባለፉት 2 ዓመታት ዩኒቨርስቲው የመማር ማስተማርስራውን ያቋረጠው ኃላፊነት የሚወስድ አካል በመጥፋቱ ነውየሚሉት የመካነ ሰላም ከተማ ነዋሪዎች ከጎንደር ዩኒቨርስቲተሞክሮ በመውሰድ ተማሪዎችን እንደልጅ ተቀብለንልናስተምር ተዘጋጅተናል ሲሉ ይናገራሉ፡፡ 

‹‹ኃላፊነቱን አንወስድም ችግር ቢፈጠር የሚል አካል ስለነበርኃላፊነት ካልወሰዳችሁ ዩኒቨርስቲውን እኛምማስከፈትአንችልም በሚል በመቅደላ አምባ ቱሉ አውሊያ ካምፓስ ነበርተማሪዎች ሲማሩ የነበሩት፤ አሁንመጥተዋል ተብሏል፡፡ እኛም ከጎንደር ዩኒቨርስቲ ልምድ ወስደን ተማሪዎችን ልክእንደወላጅ ሆነን በቃል ኪዳንተረክበን እንደ ልጆቻችንበሚደርስባቸው ማንኛውም ነገር በመጋራት ዝግጁ ሆነንነው ያለነው።›› 

የመቅደላ አምባ ዩኒቨርስቲፕሬዚዳንት ዶ/ር ካሳ ሻወልበበኩላቸው ዩኒቨርስቲው በመካነ ሰላም ካምፓሱ ትምህርትለማስጀመር መዘጋጀቱን እና ከማህበረሰቡ  ጋር መግባባት ላይመደረሱን ይገልፃሉ፡፡ 

‹‹ሙሉ ዝግጅት አድርገናል፤ አሁን የሚገቡት ሲኒየርተማሪዎች ናቸው፡፤ ማህበረሰቡ ልጆቹን እንደራሱአድርጎአይቶ ትምህርታቸውንም በማህበራዊም በማንኛውም ነገርክትትል እና ድጋፍ እንዲያደርግላቸውተነጋግረን ጥሩ ተቀባይነት አግኝተው ወደ ሥራ ገብተናል፡፡›› 

ኢሳያስ ገላዉ 

ነጋሽ መሐመድ

ታምራት ዲንሳ 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW