1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የመንገደኞች እንግልት በጎሐጽዮን

ሰኞ፣ የካቲት 6 2015

ከጎንደር ህዝብ ጭኖ ወደ አዲስ አበባ ሲሄድ በኦሮሚያ ክልል ጎሐጽዮን ከተማ በፀጥታ ኃይሎች ከጫኑት ህዝብ ጋር እንዲመለሱ ተደርገው አማራ ክልል ደጀን ከተማ መኪናቸውን ማቆማቸውን እንድ የህዝብ ትራንስፖርት አሽከርካሪ ተናግረዋል።በርካታ ለህክምና የሚሄዱ፣ አቅመ ደካሞች፣ ገንዘባቸው ያለቀባቸው ሰዎች በቤተ ክርስቲያንና በመስጊዶች ይገኛሉ ብለዋል፡፡

Brücke über den Blauen Nil Äthiopien
ምስል፦ DW/Azeb Tadesse Hahn

የመንገደኞች እንግልት በጎሐጽዮን

This browser does not support the audio element.

ካለፈው ሐሙስ ጀምሮ ከአማራ ክልል በደጀን አቅጣጫ ወደ አዲስ አበባ የሚጓዙ ተሳፋሪዎች የኦሮሚያ ክልል የፀጥታ ሰዎች ከሰሜን ሸዋ ዞን ጎሐጽዮን ከተማ እንደሚመልሷቸው ተናገሩ። ገንዘብ የሌላቸውና የታመሙ ተጓዦች በቤተክርስቲያናትና በመስጊዶች ተጠልለው ኅብረተሰቡ ምግብ እያቀረበላቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ከ3 ቀናት በፊት ከጎንደር ህዝብ ጭኖ ወደ አዲስ አበባ ሲሄድ ከቀኑ 5 ሰዓት ሲሆን በኦሮሚያ ክልል ጎሐጽዮን ከተማ ላይ በፀጥታ ኃይሎች ከጫኑት ህዝብ ጋር እንዲመለሱ ተደርገው አሁን አማራ ክልል ደጀን ከተማ መኪናቸውን ማቆማቸውን እንድ የህዝብ ትራንስፖርት አሽከርካሪ ተናግረዋል፣ በርካታ ለህክምና የሚሄዱ፣ አቅመ ደካሞች፣ ገንዘባቸው ያለቀባቸው ሰዎች በቤተ ክርስቲያንና በመስጊዶች ይገኛሉ ብለዋል፡፡ 
“ ብዙ ሰው ነው እየተጉላላ ያለው፣ ምክንያቱም አዲስ አበባ ብቻ ለመግባት ተዘጋጅቶ፣ ገንዘብ ሳይዝ የሚወጣ ሰው አለ፣ የአልጋም ሆነ የምግብ ያልያዘ ሰው አለ፣ አዛውንቶች አሉ፣ አሮጊቶች አሉ፣ ነብሰ ጡሮች አሉ፣ ማንኛውም ሰው ለመነሳቱ በፊት ባንቀሳቀስ ጥሩ ነበር፣ ጉዞ ከጀመርክ በኋላ ተመለሱ መባል ግን አግባብ አይደለም የሚጉላላ ብዙ ሰው አለ ታሳቢ ቢደረግ ጥሩ ነው፡፡” 
ከባህርዳር ወደ አዲስ አበባ ሲጓዙ በኦሮሚያ ክልል የጸጥታ ኃይሎች እንደተመለሱና አሁን ደጀን ከተማ እንዳሉ የሚናገሩት ሌላው ተጓዥ አሁን በችግር ላይ እንደሆኑ፣ የተመለሱበትን ምክንያት ቢጠይቁም እንዳልተነገራቸው ፣ ብዙ ለከፍተኛ ህክምና የተላኩ ሰዎች እየተቸገሩ መሆኑን አመልክተዋል፡፡ 
“ጉሐጽዮን ስንደርስ አታልፉም፣ ከዚህ በኋላ ወደዚህ ማለፍ አይቻልም፣ ወደ ክልላችሁ ተመለሱ፣ ብዙ ፊታቸው ያበጠ፣ ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረሰ ህመም ያለባቸው፣ ተቀባይነት የላችሁም ተብለው በግልምጫና በእንግልት ተመልሰዋል፣ የተመቱም አሉ፣ አገር እለን አገር እንደሌለን፣ አውቀናል፣ ማንገላታቱን እንደምንም አያይቱም፣ የሚሰማም የለም፣ ሙስሊሙ በመስጊድ፣ ያለው አልጋ ይይዛል የሌለው መኪና ውስጥ ያድራል፣ በብዛት ደግሞ በቤተ ክርስቲን ተጠልለዋል፣ በተለይ የተቸገሩ የአዲስ አበባ ተጓዦች ናቸው፣ ወደ መጡበት የተመለሱም አሉ፡፡” 
ለባሕላዊና ዘመናዊ ህክምና ወደ አዲስ አበባ እየሄዱ ከነበሩ ሰዎች መካከል ሁለቱ በተፈጠረው ችግር ምክንያት ደጀን ላይ መቀመጣቸውን ያስረዳሉ፡፡ 
ከታማሚዎች አንዱ ለፀበል ህክምና ወደ ሶደሬ እየተጓዘ እንደነበር አመልክቶ ሆኖም መንገድ በመከልከሉ ምክንያት ደጀን ከተማ ውስጥ በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን እንደሚገኝ ገልጧል፡፡ ሌላዋ ከሐረር ወደ አማራ ክልል ፀበል ቆይታ ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የካንሰር ህክምናዋን ለመከታተል ብትፈልግም ከመንገድ እንደተመለሰች ተናግራለች፡፡ 
በቤተ ክርስቲናትና በመስጊዶች የተጠለሉ መንገደኞችን ህዝቡ ሳይሰለች ምግብ እያቀረበላቸው እንደሚገኝ ተናግረዋል፣ ሆኖም ችግሩ በፍጥነት እንዲፈታላቸው ጠይቀዋል፡፡ 
በጣም እየተቸገሩ ያሉት ወደ አዲስ አባባ ከተማ የሚሄዱ እንደሆኑ አስተያየት ሰጪዎቹ ጠቁመው ዛሬ የተከለከለውን ኬላ ለማለፍ የተጠቀሙበት ዘዴም ተቀባይነት እንዳላገኘ ነው በምሬት ያመለከቱት። 
“ያው ደጀን ላይ ከሐሙስ እለት ጀምሮ ቆመናል፣ ዛሬ የኦሮሚያ ታርጋ በለጠፈ መኪና ለመሻገር ሞክረን ነበር፣ ሆኖም ጎሐጽዮን ላይ መለሱን አሽከርካሪው የኦሮሞ ተወላጅ ነበር በቋንቋው ያግዘናል ብለን አስበን ነበር ግን አሽከርካሪውን ሊደበድቡት ነበር እንደገና ለምነን ግባ ብለን ነው የተመለስነው፡፡” የደጀን ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አበጀ ቢምረው በርካታ ሰዎች በተፈጠረው ችግር መንገላታታቸውን ለዶይቼ ቬሌ ገልጠዋል፡፡ “ሰው ከፍተኛ እንግልት ውስጥ ነው ለው፣ ነዋሪው እያዋጣ ሐይማኖት ተቋማት አካባቢ ወጣቱም ያዋጣል፣ የተወሰነው ተጓዥ ወደ መጣበት ተመልሷል፣ አብዛኛው ግን አሁንም እዚህ ነው ያለው፡፡” ብለዋል ስለጉዳዩ አስተያየት እንዲሰጡኝ በኦሮሚያ ክልል ለሰሜን ሸዋ ዞን ኃላፊዎች ያደረግሁት ጥረት አልተሳካለም፡፡ 
ዓለምነው መኮንን 
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ
 

ምስል፦ DW/ Azeb Tadesse Hahn
ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW