1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የመንገድ ኮሪደር ልማቱ እና የተነሺዎች ጥድፊያ በአዲስ አበባ

ማክሰኞ፣ መጋቢት 17 2016

አዲስ አበባ ውስጥ የመንገድ ኮሪደር ልማት በሚል በቅርቡ የተጀመረው የቤቶች ፈረሳ በንግድ ላይ የተሰማሩትን በርካታ ነጋዴዎች ስነማስነሳቱ እየታየ ነው፡፡ ተነሺ ነጋዴዎቹም የልማቱ ተቃርኖ ባይኖራቸውም የሚሰጠው ጊዜ እጅግ ከማነሱም የተነሳ ጥድፊያ የሚስተዋልበት ነው ይላሉ፡፡

Äthiopien Addis Abeba | Abrissarbeiten wegen Straßenbau
በአዲስ አበባ የመንገድ ዳር ልማት ቤቶች ሲፈርሱምስል Seyoum Getu/DW

በአዲስ አበባው የልማት ኮሪደር የመንገድ ዳር ተነሺዎች እየተዋከብን ነው አሉ

This browser does not support the audio element.

ለአዲስ አበባው የመንገድ ዳር ልማት የተነሺዎች ጥድፊያ

አዲስ አበባ ውስጥ የመንገድ ኮሪደር ልማት በሚል በቅርቡ የተጀመረው የቤቶች ፈረሳ በንግድ ላይ የተሰማሩትን በርካታ ነጋዴዎች ስነማስነሳቱ እየታየ ነው፡፡

ተነሺ ነጋዴዎቹም የልማቱ ተቃርኖ ባይኖራቸውም የሚሰጠው ጊዜ እጅግ ከማነሱም የተነሳ ጥድፊያ የሚስተዋልበት ነው ይላሉ፡፡

ይህ ደግሞ ንብረታቸውን እንኳ በአግባቡ ለማስነሳት ማሰቢያ ጊዜ እንዲያጥራቸው ማድረጉን ያስረዳሉ፡፡

አንድ የፖለቲካል ኢኮኖሚ ባለሙያ እንደሚሉት በያንዳንዱ የልማት ስራዎች ህብረተሰቡን ማወያየትና የስራው ትብብር አካል ማድረግ ለልማቱ ግብ ዘለቄታዊነት ጉልህ ሚና የሚኖረው ተግባር ነው፡፡

የመንገድ ኮሪደር ልማት ተነሺዎች

 “ትልቁ ችግር ያከራዩን የህንጻ ባለቤቶችም ሆኑ ከመንግስት አካል የተነገረን የለም፡፡ ቤቶቹ የሚፈርሱበትን የልማት ዓላማውን ሳሆን በጥድፊያ እላያችን ላይ መፍረሱን ነው የምቃወመው” የሚሉት የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ መሸጫ ሱቅ ነጋደው በዛሬው እለት በማለዳው ተነስተው የሱቅ እቃዎቻቸውን በተሽከርካሪ ጭነው ወደ ሌላ ስፍራ ለማጋዝ ይባትላሉ፡፡በሸገር ከተማ ቤቶች መፍረስ እና የኢሰመኮ መግለጫ

ይህ ስፍራ ከመገናኛ ወደ አያት (ደራርቱ አደባባይ) በሚወስደው አውራ ጎዳና ላይ ከደራው የንግድ ሱቆች መገኛ ጉርድ ሾላ ተብሎ የሚጠራ አከባቢ ነው፡፡ ከትናንት ከሰዓት ጀምሮ በዚህ አከባቢ ከልብስ መሸጫ ሱቆች አስከ የቤት መገልገያ እና ሌሎችም የኤሌክትሮኒክ መሸጫ ሱኮች የታላቅ ቅናሽ ማስታወቂያ ጽሁፎችን ከበራቸው ላይ ለጥፈው ከወትሮ በእጅጉ ዝቅ ባለ ዋጋ እቃዎቻቸውን ይሸጣሉ፡፡ አጋጣሚውን ለመጠቀም ያሰፈሰፉ የሚመስሉ በሸቀጦች ዋጋ ንረት የተማረሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ደግሞ የቅናሽ ዋጋ ሽያጩን ለመጠቀም በሚመስል መልኩ የማጣሪያ ዋጋ የወጣላቸው አልባሳት እና እቃዎቹ ላይ ሲሻሙ ይስተዋላል፡፡

ከትናንት ከሰዓት ጀምሮ በዚህ አከባቢ ከልብስ መሸጫ ሱቆች አስከ የቤት መገልገያ እና ሌሎችም የኤሌክትሮኒክ መሸጫ ሱኮች የታላቅ ቅናሽ ማስታወቂያ ጽሁፎችን ከበራቸው ላይ ለጥፈው ከወትሮ በእጅጉ ዝቅ ባለ ዋጋ እቃዎቻቸውን ይሸጣሉ፡፡ምስል Seyoum Getu/DW

የተነሺዎች ጥድፊያ እና አቤቱታቸው

በነገሩ የተማረሩ ከአነስተኛ እስከ መካከለኛ ንግድ ላይ የተሰማሩቱ ነጋዴዎች ግን “አስቀድመን ሳንዘጋጅ መጣብን” ያሉት ለመንገድ ዳር ልማት ተብሎ የሚከወነውን የቤቶቹ ፈረሳ እውን መሆኑን በውል ካወቁት ገና ሁለተኛ ቀናቸው መሆኑን ያስረዳሉ፡፡ “ከትናት በስቲያ እሁድ ቀን መጥተው ነው እንደሚፈርስ የነገሩን፡፡ ጊዜ ስጡን ስንላቸው እላያችሁ ላይ በዶዘር እናፈርሳለን አሉን፡፡ ከዚያን እንደምትመለከተው ንብረታችን በስርዓት የማውታት ጊዜ እንኳ አጥተን ተዋከብን፡፡ ብያንስ ንብረታችን ወይ ሽጠን ወይ በስርዓት አስቀምጠን የምንወጣበት ጊዜ ብሰጠን መልካም ነበር፡፡ ስራው መተዳደሪያችን ነበር፡፡ ልጆቻችን የምናስተምርበትም ጭምር፡፡ አስቸጋሪ ነው፡፡ የልማት ተቃዋሚ ሆነን ሳሆን ጊዜ ሳይሰጠን መፍረሱ ነው መጥፎ” ብለዋል፡፡«አዲስ አበባን ጥቅም አልባ የማድረግ» እንቅስቃሴ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቅርቡ በከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ ተላለፈ ባለው በከተማዋ በተለያዩ አቅጣጫዎች የመንገድ ኮሪደር ልማትና የስማርት ሲቲ ግንባታ ላለው የልማት ግብ ስራዎቹ በፍጥነት እየተከናወኑ መሆኑን ያስረዳል፡፡ የከተማ አስተዳደሩ ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ዛሬ እንዳመለከተውም የመንገድ ኮሪደር ልማቱን በወራት ውስጥ ለማጠናቀቅ “ሌት ተቀን ይሰራሉ” ብሏል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቅርቡ በከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ ተላለፈ ባለው በከተማዋ በተለያዩ አቅጣጫዎች የመንገድ ኮሪደር ልማትና የስማርት ሲቲ ግንባታ ላለው የልማት ግብ ስራዎቹ በፍጥነት እየተከናወኑ መሆኑን ያስረዳል፡፡ምስል Seyoum Getu/DW

የልማቱ ፋይዳ እና አብሮ ሊወሰዱ ሚገቡ እርምጃዎች

እንዲህ ያሉ ልማቶች አስፈላጊነታቸው አያጠያቅም የሚል አቋም አንጸባርቀው ሂደቱ ላይ ግን ጥያቄ እንዳላቸው የሚገልጹት የፖለቲካል ኢኮኖሚ ተንታኝ እና የዲመቴ መጽሃፍ ደራሲው ሸዋፈራሁ ሽታሁን፤ “አሮጌ ሰፈር ፈርሰው ደረጃውን በጠበቀ ልማት መተካታቸውን በሁለት መንገድ የምደግፈው ነው፡፡ አንድም ከህብረተሰቡ ፍላጎት አንጻር ነው፡፡ ሌላው ከተማዋ የአፍሪካ ህብረት መዲና እና የዓለም ሶስተኛ ዲፕሎማቲክ ማዕከል ስትባል ያንን ደረጃ በሚመጥን መሆን ስላለበት፡፡ ግን ጥያቄዬ ህደቱ ላይ ነው፡፡ ወደ ፈረሳው ከመከዱ በፊት ምን ያህል ህብረተሰቡን የማማከር እና ለሚፈርሰው ቤታቸው ምን ህል በቂ የዝግጅ ጊዜ ተሰጠ የሚለው ነው፡፡ ይህ ደግሞ መደረጉን እጠራጠራለሁ” ነው ያሉት፡፡ቤት የፈረሰባቸው አባወራዎች ቅሬታ

መሰል የልማት ስራዎቹ ህብረተሰቡ ቅራኔን በሚያስነሳበት መንገድ ሳይሆን ህብረተሰቡን የልማቱ አካል በሚያደርግ መልኩ መሆን ያለበት ነው ያሉን ባለሙያው፤ የመልሶ ልማት ሂደቱ ውስጥ ቅሬታን መቀነስ በእጅጉ አስፈላጊ እንደሆነም ሃሳባቸውን አክለዋል፡፡ “ተነሺዎቹ ተመጣጣኝ ካሳ ማግኘታቸውን መንግስት ማረጋገት አለበት፡፡ ከፈረሳውም በኋላ የሚሰራው ልማት ምን እንደሆነ ለህብረተሰቡ ተነግሮታል ወይ የሚል ጥያቄም መነሳት አለበት፡፡ ምክኒያቱም በአንድ አከባቢ ሚሰራ ልማት የህብረተሰቡን ድጋፍ ማግኘት ያለበት ነው” ብለዋል፡፡ አክለውም ህብረተሰቡን የማስነሳቱ ስራ ስከወን አቅሙ ላላቸው ለአከባቢው ተነሺዎች የመኖሪያም ሆነ የንግድ ግንባታዎችን በጋራ እንዲገነቡ ቅድሚያ መስጠት አስፈላጊነቱ ጉልህ መሆኑን እንደ መፍትሄ ሃሳብም አስቀምጠዋል፡፡

ስዩም ጌቱ 
ታምራት ዲንሳ 
ማንተጋፍቶት ስለሺ

 

 

 

  

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW