የመንግሥትና የተቃዋሚዎቹ ዉዝግብ
ሐሙስ፣ ሚያዝያ 15 2007ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ ሕዝብ ሊቢያ ዉስጥ የተገደሉ ኢትዮያዉያንን ለማሰብን እና ግድያዉን ለማዉገዝ ትንናት ያደረገዉ የአደባባይ ሠልፍ፣ መንግሥትን ወደሚቃወሚያነት መድረክና ግጭት መለወጡ መንግሥትንና ተቃዋሚ ፓርቲዎችን እያወዛገበ ነዉ።የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት ከፀጥታ አስከባሪዎች ጋር የተጋጩትን ወጣቶች ከሠልፉ የቀላቀለዉ ሰማያዊ ፓርቲ ነዉ በማለት ፓርቲዉን ወቅሰዋል።የመላዉ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) እና የሰማያዊ ፓርቲ ባለሥልጣናት ግን የመንግሥትን ወቀሳ አጣጥለዉ ነቅፈዉታል።
ጌታቸዉ ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ነጋሽ መሐመድ
ሒሩት መለሠ