1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የመንግሥት ፀጥታ ኃይላት 2 የዛይሴ ተወላጆች ገደሉ፣ በርካታ አሰሩ

ማክሰኞ፣ ግንቦት 12 2017

ባለፈው ሳምንት የታጠቁ ቡድኖች አንድ የክልሉን የፀጥታ አባል ገድለው አራት ካቆሰሉ በኋላ በአካባቢው ውጥረት እንደነገሰ ይገኛል ፡፡ ሁለት የቤተሰብ አባሎቻቸው ከትናንት በስቲያ በጥይት እንደተገደሉባቸው ለዶቼ ቬለ የተናገሩ አንድ አባት “ የፀጥታ አባላቱ የደበቃችሁትን ሽፍታ አውጡ በሚል እያዋከቡን ይገኛሉ “ብለዋል ፡፡

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጋሞ ዞን ዋና ከተማ አርባ ምንጭ በከፊል።የዛይሴ ማህበረሰብ አባላት በብዛት የሚኖሩት አርባ ምንጭ ወረዳ ዉስጥ ነዉ።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጋሞ ዞን ዋና ከተማ አርባ ምንጭ በከፊል።የዛይሴ ማህበረሰብ አባላት በብዛት የሚኖሩት አርባ ምንጭ ወረዳ ዉስጥ ነዉ።ምስል፦ Arbaminch culture and Tourism office

የመንግሥት ፀጥታ ኃይላት 2 የዛይሴ ተወላጆች ገደሉ፣ በርካታ አሰሩ

This browser does not support the audio element.

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን የዛይሴ ዳንበሊ ነዋሪዎች በፀጥታ አባላት ግድያ ፣ እሥር እና ወከባ እየተፈጸመብን ይገኛል አሉ ፡፡ ባለፈው ሳምንትየታጠቁ ቡድኖች አንድ የክልሉን የፀጥታ አባል ገድለው አራት ካቆሰሉ በኋላ ወዲህ አሁንም በአካባቢው ውጥረት እንደነገሰ ይገኛል ፡፡ ሁለት የቤተሰብ አባሎቻቸው ከትናንት በስቲያ በጥይት እንደተገደሉባቸው ለዶቼ ቬለ የተናገሩ አንድ አባት “ የፀጥታ አባላቱ  የደበቃችሁትን ሽፍታ አውጡ  በሚል እያዋከቡን ይገኛሉ “ ብለዋል ፡፡

 

ሥጋት ላይ ወድቀናል የሚሉት የዛይሴ ዳንበሊ ነዋሪዎች

 ባለፈው ሳምንት የታጠቁ ቡድኖች አንድ የክልሉን የፀጥታ አባል ገድለው አራት ካቆሰሉ በኋላ በአካባቢው ውጥረት እንደነገሰ ይገኛል ፡፡ ሁለት የቤተሰብ አባሎቻቸው ከትናንት በስቲያ በጥይት እንደተገደሉባቸው ለዶቼ ቬለ የተናገሩ አንድ አባት “ የፀጥታ አባላቱ  የደበቃችሁትን ሽፍታ አውጡ በሚል እያዋከቡን ይገኛሉ “ ብለዋል ፡፡

ሁለት የቤተሰብ አባሎቻቸውን ያጡት አባት

አርሶአደር ባንዳ ዶጊሶ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን አርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ የዛይሴ ደንቢሌ ቀበሌ ነዋሪ ናቸው ፡፡ ከትናንት በስቲያ የእሳቸው እና የሚያሳድጉት የእህታቸው ልጅ የጠፋ ከብት ለመፈለግከቤት መውጣታቸው የጠቀሱት አርሶአደር ባንዳ “ ይሁን እንጂ ሁለቱም በጥይት ተመተው ተገድለዋል ፡፡  በሥፍራው ሥደርስ የእህቴ ልጅ ካሳሁን ጋይሮ ወዲያው ነው ነፍሱ የወጣው  ፡፡ ልጄ ሙላቱ ባንዳ ደግሞ አርባምንጭ ሆስፒታል ከደረሰ በኋላ ነው ሕይወቱ ያለፈው ፡፡ ሁለቱንም እሁድ ዕለት ቀብረናቸዋል ፡፡ በልጆቼ ላይ ተኩስ ከፍተው የገደሉት አድማ በታኝ የተባሉ የክልሉ ፀጥታ አባላት ናቸው  “ ብለዋል ፡፡

የእንደራሴ ምክር ቤት አባሉ ምን ይላሉ ?

ዶቼ ቬለ ግድያ ተፈጽሞባቸዋል በተባሉ ወጣቶች እና እየደረሰ ይገኛል የተባለውን እሥር እና ወከባ አስመልክቶ ምላሽ እንዲሰጡት ለጋሞ ዞን ፖሊስ መምሪያም ሆነ ለክልሉ ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ የስራ ሃላፊዎች በሥልክ ለማነጋገር ጥረት አድርጓል ፡፡ ይሁንእንጂ የሥራ ሃለፊዎቹ ምላሽ ለመሥጠት ፍላጎት አላሳዩም ፡፡ ያም ሆኖ የዛይሴ የምርጫ ክልልን በመወከል  የፌዴራል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ አብረሃም አሞሼ የአካባቢው ነዋሪዎች በሥጋት ውስጥ እንደሚገኙ ለዶቼ ቬለ ገልጸዋል ፡፡ የታጠቁ ቡድኖች በህግ አስከባሪዎች ላይ ያደረሱት ተግባር መወገዝ ያለበት መሆኑን የጠቀሱት የምክር ቤት አባሉ “ ነገር ግን የፀጥታ አካላቱ የድርጊቱን ፈጻሚዎች ለመያዝ በሚል በሰላማዊ ነዋሪዎች ላይ እያደረሱ የሚገኘው ጉዳት አሳሳቢ ነው ፡፡  የፀጥታ አባላቱ ሽፍታ ደብቃችኋል በሚል የቤት ለቤት ፍትሻ በማድረግ ግድያ ፣ እስር እና ወከባ ይፈጽማሉ ፡፡ አሁን ላይ በቀበሌው ከተገደሉት ሁለት ወጣቶች በተጨማሪ በርካታ ሰዎችም እየታሰሩ ይገኛሉ “ ብለዋል ፡፡

አርባ ምንጭ።የከተማይቱና የአካባቢዉ የሐገር ሽማግሌዎችና ባለሥልጣናትምስል፦ Fitsum Arega

የአባሉ አቤቱታ

በአሁኑወቅት ለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን /ኢሰማኮ/ እና ለሰላም ሚንስቴር ጉዳዩን ማሳወቃቸውን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባሉ ተናግረዋል ፡፡ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን በአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ውስጥ የሚገኙት የዛይሴ ማህበረሰብ አባላት በልዩ ወረዳ መዋቅር ለመደራጀት የሚያስችላቸውን ጥያቄ እያቀረቡ እንደሚገኙ ይታወቃል ፡፡ የሰሞኑ  የታጣቂዎች ጥቃት ከዚህ ጥያቄ ጋር የተገናኘሥለመሆን አለመሆኑ ግን ማረጋገጥ አልተቻለም ፡፡ ባለፈው የካቲት ወር በዚሁ የዛይሴ ዳንብሊ ቀበሌ ውስጥ የዛይሴ ብሄር አዲስ ዓመትን እናከብራለን በሚል የተሰባሰቡ ወጣቶች ከፀጥታ አካላት ጋር ተጋጭተው የሰዎች ሕይወት ማለፉ የሚታወቅ ነው ፡፡

ሸዋንግዛው ወጋየሁ

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ

 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW