1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የመንግሥት ባለሥልጣናት ጉብኝት በአፋር ክልል

ሐሙስ፣ ጥቅምት 13 2018

የኢትዮጵያ ፌደራዊ መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት፣ የጦር አዛዦችና የአፋር ክልል ባለሥልጣናት ኤርትራ ድንበር አጠገብ የምትገኘዉን ሥልታዊቷን የቡሬ ከተማን መጎብኘታቸው ዛሬ ተዘግቧል ።

ጋዜጠኛ ነጋሽ መሐመድ
ጋዜጠኛ ነጋሽ መሐመድምስል፦ Florian Görner/DW

ከባልደረባችን ነጋሽ መሐመድ ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ

This browser does not support the audio element.

የኢትዮጵያ ፌደራዊ መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት፣ የጦር አዛዦችና የአፋር ክልል ባለሥልጣናትኤርትራድንበር አጠገብ የምትገኘዉን ሥልታዊቷን የቡሬ ከተማን መጎብኘታቸው ዛሬ ተዘግቧል ። የጠቅላይ ሚንስትር ዓብይ አሕመድ የምሥራቅ አፍሪቃ ጉዳይ አማካሪ ጌታቸዉ ረዳ፣ የኢትዮጵያ የብሔራዊ መረጃና ደሕንነት አገልግሎት የበላይ ኃላፊ ሬድዋን ሁሴይን፣ ከፍተኛ የጦር መኮንኖችና የአፋር ክልል ባለሥልጣናት የቡሬ ጉብኝታቸዉን አጠናቅቀዉ ዛሬ ቀትር ላይ ሠመራ እንደነበሩም ተገልጧል ። ቡሬ ከኢትዮጵያ፣ ኤርትራና ጅቡቲ አዋሳኝ ድንበር በቅርብ ርቀት ላይ የምትገኝ ሥልታዊ ሥፍራ ናት። ከኤርትራ የወደብ ከተማ ከአሰብም 80 ኪሎ ሜትር ያሕል ትርቃለች። 

በረሐማዋ የአፋር ክልል ከተማ ቡሬና አካባቢዋ ኢትዮጵያና የኤርትራ ከ1990-1992 ባደረጉት ጦርነት የሁለቱ ሐገራት ጦር ኃይላት ለተከታታይ ወራት ከፍተኛ ዉጊያ ያደረጉበት አካባቢም ነዉ።የኢትዮጵያና የኤርትራ መንግሥታት አንዱ በሌላዉ ላይ «ጦርነት ለመክፈት» እየተዘጋጀ ነዉ በሚል በሚወቃቀሱበት ባሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት አካባቢዉን የጎበኙበት ትክክለኛ ምክንያት በዉል አልታወቀም።ባለሥልጣናቱ ቡሬን መጎብኘታቸዉንና ዛሬ ቀትር ላይ አፋር ክልል ርዕሠ ከተማ ሠመራ እንደሚገኙ ግን ከባለሥልጣናቱ አንዱ በሥልክ ለዶቸ ቬለ አረጋግጠዋል።ዝርዝሩን ግን፣ ባለሥልጣኑ «ጉዞ ላይ ነኝ« በሚል ከመናገር ተቆጥበዋል።
የባለሥልጣናቱ ጉብኝት ምንን ያመለክታል?

ነጋሽ መሐመድ/ማንተጋፍቶት ስለሺ

አዜብ ታደሰ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW