1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ፀረ ሁኒዎች ጥቃት፤ ለየመን የወደፊት ዕጣ ፈንታ የሚደረገው ፍልሚያ

ረቡዕ፣ መስከረም 27 2019

የመን ውስጥ በመንግሥት እና በሁቲ አማጽያን መካከል ውጊያው ተባብሷል። ዓለም አቀፉ እውቅና ያለው የየመን መንግሥት በሁቲዎች ላይ የሚያደርገውን ጥቃት አጠናክሯል

Jemen Dhubab 2026 | Regierungskämpfer feuern bei Offensive gegen Huthi
ምስል፦ Southern Giants Brigades/Handout via REUTERS

የመን ውስጥ የተባባሰው ውጊያ

This browser does not support the audio element.

 

 

የመን ውስጥ በመንግሥት እና በሁቲ አማጽያን መካከል ውጊያው ተባብሷል። ዓለም አቀፉ እውቅና ያለው የየመን መንግሥት በሁቲዎች ላይ የሚያደርገውን ጥቃት አጠናክሯል። ሁቲ ሚሊሺያችም በሀገር ውስጥ ከሚያደርጉት ውጊያ ጎን ለጎን ሳውድ አረቢያ ላይ የሚያደርሱት ጥቃት መቀጠሉ እየተነገረ ነው።

የየመን መንግሥት ኃይሎች የሁቲ አማጽያን በቀይ ባሕር ላይ የመርከቦችን እንቅስቃሴ ለማስተጓጎል የሚያደርሱትን ጥቃት ለማስቆም የቆረጡ መስሏል። ሁለቱም ወገኖች በቀይ ባሕር ባብ ኤል ማንዳብ መስመር የበላይነትን ለመያዝ ፍልሚያ ቀጥለዋል። እንደ ኬርስተን ክኒፕ የመንግሥት ኃይሎች ባብ ኤል ማንዳብን ለመቆጣጠር የሚያደርጉት ጥረት የመሳካቱ ነገር አከራካሪ ነው። ይህን ለማድረግ የተከፋፈሉት ሁቲዎችን የሚቃወሙት ቡድኖች ኃይላቸውን ማስተባበር ይኖርባቸዋል ባይ ነው። 

ባለፈው ነሐሴ ወር መጀመሪያ ላይ በተደረሰው የመካ ስምምነት መሠረት ቱርክ እና ፓኪስታን የየመንን መንግሥት በኢራን ከሚደገፉት የሁቲ አማጽያን ጥቃቶች ለመከላከል ወታደሮቻቸውን ወደ ሳውድ አረቢያ ለመላክ ቃል ገብተዋል። የሁቲ ሚሊሺያዎች አሁንም ከየመን መንግሥት ጋር እየተፋለሙ ሳውድ አረቢያ ላይም ጥቃት ማድረሳቸውን ቀጥለዋል። በሪያድ የሚመራው ወታደራዊ ጥምረትም በየመን የአየር ድብደባውን አጠናክሯል። የየመን መንግሥት ኃይሎችም መጠነ ሰፊ ጥቃት ሁቲዎች ላይ ፈጽመዋል፤ ስልታዊ ጠቀሜታ ባለው የባብ ኤል ማንዳብ መስመር የተሻለ ድል እንዳስመዘገቡ ተናግረዋል። ሁቲዎች ይህን ውድቅ በማድረግ፤ በቀይ ባሕር አቅራቢያ በየመን ደቡብ ምዕራብ በምትገኘው ታይዝ ከተማ ዙሪያ ኃይላቸው እየገፋ መሆኑን ይገልጻሉ።

የመንን ለመቆጣጠር የሚደረገው ፍልሚያ

ሁለቱም የየመን ተቀናቃኝ ኃይሎች የሀገሪቱን የሥልጣንም ሆነ የፖለቲካ የበላይነት ለመቆጣጠር ይፈልጋሉ። በመጨረሻ በየመን የፖለቲካ የበላይነትን ይዞ የግዛት ሉአላዊነትንና ሕዝቡን የሚያስተዳድረው ማን ነው የሚለው ዋናው ጥያቄ ነው። በዮርዳኖስ የኮንራድ አደናወር ተቋም የባሕረ ሰላጤው ሃገራት ጉዳይ ዘርፍ ኃላፊ ፊሊፕ ዲንስትቢር፤ የኃይል የበላይነት ከማን ጋ ነው የሚለውን ከርቀት መገመት አይቻልም ነው የሚሉት።

«ይህ ምን ያህል ውጤታማ እንደሆነ ለመናገር በጣም አስቸጋሪ ነው። ምክንያቱም የመንግሥት ኃይሎች ወደ ሞካ እየተቃረቡ ነው የሚለው አዎንታዊ ዜና ቢሰማም፤ በተመሳሳይ የሁቲ አማጽያን ታአዚዝን ሊይዙ እየተቃረቡ መሆናቸው ይነገራል።እንደሚመስለኝ ሁኔታው በቀጣይ እንዴት እንደሚሆን መጠበቅ ያስፈልጋል። እናም የደቡብ የመን ኃይሎች ማለትም የየመን መንግሥት ኃይሎች ማለት ነው፣ በዚህ ረገድ ምን ያህል ስኬታማ ናቸው የሚለውን ከውጪ ሆኖ ለመገመት አስቸጋሪ ነው።»

ምስል፦ Southern Giants Brigades/Handout via REUTERS

 

የየመን መንግሥት ዋናው ችግር የውስጥ መበታተን ነው። ፀረ ሁቲ ኃይሎች አንድንዴ ፈጽሞ የተለያዩ የፖለቲካ ዓላማ ያላቸው ቡድኖችን ያካትታሉ። ለምሳሌ ደቡብ የሽግግር ምክር ቤት የሚባለው፤ ነጻ የደቡብ የመንን ለማግኘት የሚታገል ነው። በምሥራቅ የመን በሚገኘው የሃድራሙት ክልል ውስጥ የራስ ገዝነት ጥያቄ አቅርቧል። እንዲህ ያለው መበታተን ወታደራዊ ቅንጅትን በእጅጉ ያወሳስባል። የተለያዩት ኃይሎች እርስ በእርስ ጥሩ ግንኙነት ስለሌላቸው የተለያዩ ፍላጎቶችን ያሳድዳሉ ይላሉ በሃምቡርግ የጀርመን የዓለም አቀፍ እና የአካባቢ ጥናት ተቋም የባሕረ ሰላጤው አካባቢ ባለሙያ ጄኔስ ሄይባች። በዚህ መሀል በኢራን የሚደገፉት የሁቲ አማጽያን የሚያደርሱት ጥቃትም በቀላል እንደማይታይ ነው ያመለከቱት።

«የጦር መሣሪያ ስለሚያገኙ ሁቲዎች የመርከቦችን እንቅስቃሴ ከአካባቢው ብቻ ሳይሆን በርቀት ከሀገር ውስጥም ሆነው ማስተጓጎል ይችላሉ። በዚህ የተነሳም በቀይ ባሕር ላይ በተለይ በቅርብ ርቀት የሚያካሂዱት ዘመቻ ለእነሱ በጣም ቀላል ነው። ሆኖም ግን በመካከለኛም ሆነ በረዥም ጊዜ ሂደት ሁኔታው ለሳውዲ አረቢያ የነዳጅ ሽያጭም ሆነ ለአጠቃይ የጭነት ማጓጓዝ ዘላቂ መፍትሄ አይደለም። በሌላ በኩል ሁቲዎች በቀይ ባሕር ዳርቻ ይዞታቸውን አጥብቀው ከያዙ ቁጥጥራቸውን ማጠናከር ይችላሉ። ይህ ደግሞ በእርግጥ እውነት ነው።»

አሁናዊ ኹነት

በዛሬው ዕለትም የሁቲ ሚሊሻዎች የኤደን ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያን በሚሳኤል እና ቦብም በተጫኑ ሰው አልባ አውሮፕላኖች መደብደባቸውን የየመንን የመጓጓዣ ሚኒስቴር አስታውቋል። ሰሞኑን የተባባሰው የየመን መንግሥትና የሁቲ አማጽያን ውጊያ በተለይ የመርከቦች መተላለፊያ በሆነው በባብ ኤል ማንዳብ መስመር ተጠናክሮ መቀጠሉን ዘገባዎች ያመለክታሉ። አካባቢው በኢራን አሜሪካ መካከል የሚካሄደው ጦርነት የነዳጅ ዘይት መተላለፊያ የሆነችው የሆርሙዝ ሰርጥ መዘጋቱን ተከትሎ ዋነኛ የንግድ መስመር መሆኑ የተፋላሚዎቹን ኃይሎች ትኩረት ስቧል።

ሸዋዬ ለገሠ /ኬርስተን ክኒፕ

እሸቴ በቀለ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW