1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የመኖርያ ቤት እጦትና የቤት ኪራይ ዋጋ ንረት

እሑድ፣ ጥር 15 2008

አዲስ አበባን በመሳሰሉ ትላልቅ ከተሞች የሚታዩ የቤት ችግሮችን ለማቃለል ኮንደሚኒየም የተባሉ አፓርትመንቶች መገንባታቸዉ ይታወቃል። ይሁንና የተገነቡት ቤቶች፤ የዋጋቸዉ ዉድነት፤ ለኢትዮጳያዊዉ ባሕላዊ አኗኗር ካለመመቸታቸዉ ጋር ተጨምሮ፤ የመኖርያ ቤት እጥረትን ማቃለል አልቻሉም።

Bezahlbarer Wohnraum wird knapp in Addis Abeba
ምስል DW/Y. Gebere Gziabeher

የመኖርያ ቤት እጦትና የቤት ኪራይ ዋጋ ንረት

This browser does not support the audio element.

አንዳንድ ቤት አከራዮች ደግሞ አጋጣሚዉን በመጠቀም የቤት ኪራይ ዋጋ በየጊዜዉ እየጨመሩ ተከራዮችን ያማርራሉ። የከተሞች መጨናነቅ የሕዝብ ብዛት የከተማ መስተዳድሮች ለየከተማዉ መስፋፋት የሚያከናዉኑዋቸዉ ተግባራት ከሕዝብ ቁጥር እድገት ወይም ከሕዝብ ፍላጎት ካለመጣጣሙ ጋር በከተሞች አካባቢዎች የተለያዩ የመሠረተ ልማት አካባቢዎች የተለያዩ የመሠረተ ልማት ችግሮች ጎልተዉ ይታያሉ። የመጠጥ ዉኃ ፤ የትራንስፖርት የመፀዳጃና የመሳሰሉት ችግሮች በተደጋጋሚ የሚነሱ ናቸዉ። ከነዚህ ሁሉ የከፋዉ ግን የመኖርያ ቤት ችግር ነዉ። አንዳንድ ቤት አከራዮች ደግሞ አጋጣሚዉን በመጠቀም የቤት ኪራይ ዋጋ በየጊዜዉ እየጨመሩ ተከራዮችን ያማርራሉ። የችግሩ ምክንያት ምንድን ነዉ፤ መፍትሄዉስ? በጉዳዩ ላይ አቶ መስፍን መንግሥቱ የአዲስ አበባ ከተማ የቤቶች አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ሥራ አስኪያጅ፤ ወ/ሮ አያልሰዉ ወርቅነህ የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር የኮሚኒኬሽን ተወካይ፤ አቶ ኤፍሪም ቦተሪ በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የፖለቲካ ሣይንስና የዓለም አቀፍ ግንኙነት የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪ እንዲሁም ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩን ጋብዘናል።

የድምፅ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን ሙሉዉን ዉይይት እንዲከታተሉ እንጋብዛለን።

አዜብ ታደሰ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW