የመኢአድና የባለራዕይ ወጣቶች ፕሬዝደንቶች መታሠር7 ግንቦት 2007ዓርብ፣ ግንቦት 7 2007የምርጫ ቦርድ እዉቅና የነፈገዉ የመላዉ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት በምህፃሩ መኢአድ ፕሬዝደንት አቶ ማሙሸት አማረና የባለ ራዕይ ወጣቶች ማኅበር ፕሬዝደንት ወጣት አለማየሁ አበበ በፖሊስ ቁጥጥር ዋሉ።ማገናኛዉን ኮፒ አድርግምስል BilderBoxማስታወቂያ ሁለቱም ባለፈዉ ራሱን እስላማዊ መንግሥት የሚለዉን ፅንፈኛ ቡድን ለመቃወም መንግሥት በጠራዉ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ሁከትና ብጥብጥ ፈጥረዋል በሚል ጥርጣሬ መያዛቸዉንና በጊዜ ቀጠሮ በፖሊስ ጣቢያ እንደሚገኙ ባልደረቦቻቸዉ ለዶቼ ቬለ ገልጸዋል። ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ከአዲስ አበባ ዝርዝሩን ልኮልናል። ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ሸዋዬ ለገሠ ነጋሽ መሐመድ