የመኢአድ መግለጫ
ማክሰኞ፣ ኅዳር 11 2005ማስታወቂያ
ተቃዋሚው የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት በምህፃሩ መኢአድ በአባላቱና በደጋፊዎቹ ላይ ተፈፀመ የሚለው የሰብአዊ መብት ረገጣ ና አፈና እንዲቆም ጠየቀ ። መኢአድ ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ በሰጠው መግለጫ በተለይ በደቡብ ክልልና በአሶሳ አካባቢ አባላቶቹ ላይ የሚካሄደው የሰብአዊ መብት ጥሰት ተጠናክሮ መቀጠሉን አስታውቋል ። በአባላቶቹ ላይ ስለ ሚፈፀመው የመብት ረገጣ ለሚመለከታቸው የመንግሥት አካላትም ሆነ ለሰብአዊ መብት ድርጅቶች ቢያሳውቅም ችግሩ አለመወገዱን የመኢአድ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ተናግረዋል ። መግለጫውን የተከታተለው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ዝርዝሩን ያቀርብልናል ።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ሂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ