1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

በሲዳማ ክልል እና በጋሞ ዞን በትራፊክ አደጋ የ9 ሰዎች ህይወት አለፈ። በ7 ሰዎች ላይ ቆሰሉ

ዓርብ፣ ጥር 8 2018

በወረዳው የሰደዋሬ ቀበሌ ነዋሪዎች ሁለቱን ወጣቶች ደግሰው ከዳሯቸው ገና ሳምንት አልሞላቸውም ፡፡ የሚያውቋቸው እንደሚሉት ሙሹሮቹ ከሀዋሳ ወደ በንሳ በሚወስደው አውራ ጎዳና ዳርቻ ላይ በምትገኝ የሳር ጎጆ ውስጥ የጫጉላ ጊዚያቸውን በማጣጣም ላይ ነበሩ ፡፡

የመኪና አደጋ
ፎቶ፤ ከማሕደራችን
የመኪና አደጋ ፎቶ፤ ከማሕደራችንምስል፦ DW/S. Muchie

ሁለት ሙሽሮች የሞቱበት የመኪmና አደጋ

This browser does not support the audio element.

በሲዳማ ክልል እና በጋሞ ዞን በደረሱ የትራፊክ አደጋዎች የ 9 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በ7 ሰዎች ላይ የመቁሰል አደጋ መድረሱን የትራፊክ ፖሊስ ጽህፈት ቤት ሃላፊዎች አስታወቁ ፡፡ በሲዳማ ክልል  የትራፊክ አደጋው የደረሰው የሠሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3 ቢ 94617 አአ የሆነ አይሱዙ የጭነት ተሽከርካሪ ከመንገዱ በመውጣት የመኖሪያ ጎጆ ደርምሶ በመግባቱ መሆኑን የክልሉ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል ፡፡ በአደጋው አራት ሰዎች መሞታቸውን የትራፊክ ደህንንትና ቁጥጥር መምሪያ ሃላፊው  ዋና ኢንስፔክተር መለሰ ቡኑራ ገልጸዋል፡፡

በተኙበት የቀሩት ሙሽሮች አሳዛኝ አደጋ

ሽመልስ ሽብሩ እና ቆንጅት በቀለ ነዋሪነታቸው በሲዳማ ክልል በንሳ ወረዳ ነው ፡፡ በወረዳው የሰደዋሬ ቀበሌ ነዋሪዎች ሁለቱን ወጣቶች ደግሰው ከዳሯቸው ገና ሳምንት አልሞላቸውም ፡፡ የሚያውቋቸው እንደሚሉት ሙሹሮቹ ከሀዋሳ ወደ በንሳ በሚወስደው አውራ ጎዳና ዳርቻ ላይ በምትገኝ የሳር ጎጆ ውስጥ  የጫጉላ ጊዚያቸውን በማጣጣም ላይ ነበሩ ፡፡ እንደአለመታደል ሆኖ አዲሶች ተጋቢዎች የዛሬ ዓርብን ፀሐይ ለማየት አልታደሉም ፡፡ ዛሬ ሊነጋጋ ሲል የሞቀ የጫጉላ ጎጇቸውን ደርምሶ በገባው ተሸከርካሪ ለህልፈት መዳረጋቸውን ነው  ከሰፈሩ ነዋሪዎች አንዱ ሲራሮ ሶሌ ለዶቼ ቬለ የተናገሩት  ፡፡

የአደጋው መንስዔ

በክልሉ የትራፊክ አደጋው የደረሰው አይሱዙ የጭነት ተሽከርካሪ መንገዱን በመሳት የመኖሪያ ጎጆ ደርምሶ በመግባቱ መሆኑን የክልሉ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል ፡፡ በአደጋው ከሙሹሮቹ በተጨማሪ የአይሱዚው አሽከርካሪና ረዳቱ ህይወት ማለፉን የትራፊክ ደህንንትና ቁጥጥር መምሪያ ሃላፊው  ዋና ኢንስፔክተር መለሰ ቡኑራ ገልጸዋል፡፡ በክልሉ አብዛኞቹ አደጋዎች መንስኤያቸው ከፍጥነት በላይ ማሽከርከር መሆኑን  የጠቀሱት ዋና ኢንስፔክተር መለሰ የዛሬው አደጋ መንስኤ እየተጣራ እንደሚገኝ ተናግረዋል ፡፡

የጋሞ ዞኑ አደጋ

በጋሞ ዞን ቦረዳ ወረዳ አሁንም ሌላ አይሱዙ ጭነት ተሸከርካሪትናንት ተገልብጦ የአምስት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የወረዳው ፖሊስ ጽህፈት ቤት አስታውቋል ፡፡ አደጋው የደረሰው በጭነት ተሽከርካሪ ተሳፍረው የቀብር ሥርዓት ለመታደም በመጓዝ ላይ በነበሩ ሰዎች ላይ ነው ያሉት  የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ረዳት ኢንስፔክተር አብረሃም አየለ በአደጋው 5 ሰዎች ወዲያውኑ ሲሞቱ በሌሎች 7 ሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል ብለዋል ፡፡
 የአደጋው መንስኤ ተሽከርካሪ ዳገት ላይ ሲደርስ ወደ ኋላ ተንሸራቶ ጥልቀት ያለው ገደል ውስጥ በመግባቱ መሆኑን የተናገሩት አዛዡ አሁን ላይ ከተሽከርካሪው ደህንነት ጋር የተያያዘ ችግር መኖር አለመኖሩን በተጨማሪ ምርምራ ለማረጋገጥ እየተሠራ ይገኛል ብለዋል ፡፡
ሽዋንግዛው ወጋየሁ
ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር
ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW