የመድሃኒት ኩባኒያዎች እና የመድሃኒት አቅርቦቱ
ማክሰኞ፣ መስከረም 14 2006እንደ ሳኖፊ ያሉ የፈረንሳይ የመዳህኒት አምራች ኩባኒያዎች ለአዳጊ ሀገራት መድሀኒት በቅናሽ ዋጋ እንደሚያቀርቡ ይናገራሉ። ለአደጉት ሀገራት በአንፃሩ ተመሳሳዩን መድሀኒት በውድ ዋጋ እንደሚሸጡ የሳኖፊ መድሀኒት አምራች ኩባንያ ባልደረባ ፍራንኮስ ቦምፓር ያብራራሉ። « ክትባትን ብንወስድ ይህ በደንብ ስኬታማ ሲሆን ይስተዋላል። ተመሳሳይ ክትባት እንበል በዮናይትድ ስቴትስ እና በአውሮፓ 50 ዮሮ ድረስ ይሸጣል። ይህው መድሀኒት ደግሞ በአፍሪቃ 3 እና 4 ዮሮ ያወጣል። በአጠቃላይ ይህ አሰራር ስኬታማ የሆነው በመካከል እንደ ብራዚል፣ ደቡብ አፍሪቃ እና ታይላንድ ያሉ ሀገሮች ስላሉ ነው። እነሱ ደግሞ ከ10 እስከ 20 ዮሮ ይከፍላሉ። »
ኢትዮጵያ ደሀ ከሚባሉት እና መድሃኒት በቅናሽ ዋጋ ከሚሸጥባት ሀገራት አንዷ ናት። ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የመድሃኒት ዋጋ አቅርቦት፣ የማከፋፈል ሂደት እንዲሁም የአገልግሎት ጊዜ በባለሙያዎች፤ በተጠቃሚ ( በሽተኛው) እና አከፋፋዮች መካከል ልዩነት አንዳንዴም ውዝግብ ሲፈጠር ይስተዋላል። መድሃኒት ወደ ኢትዮጵያ የሚገባው እንዴት ነው?መድሃኒቶች በሰዓቱ ለተጠቃሚዎች የማይደርሱበት ምክንያትስ? በኢትዮጵያ በአንድ የመድሃኒት አከፋፋይ የሚያገለግሉ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ባለሙያ ፤መድሃኒት ወደ ሀገሪቱ ለማስገባት መሟላት ያለበትን ዋና መስፈርት ገልፀውልናል።
እንዲሁም ወ/ሮ ናዲያ አብዱር ከፉር በአዲስ አበባ የሚገኝ «የአባድር ፋርማሲ» ባለቤት ናቸው። ለተጠቃሚ የሚያቀርቡትን መድሀኒት በቀጥታ ከውጭ ከአምራች ኩባንያዎች ሳይሆን ከአገር ውስጥ ነው የሚገዙት። ዋጋው ላይ ያለውን ትልቅ ልዩነት በምሳሌ አነፃፅረውልናል።
የሁሉንም አስተያየት ከድምፅ ዘገባው ያገኙታል።
ልደት አበበ
ነጋሽ መሐመድ