1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የመጀመሪያው የአስመራ በረራ

ረቡዕ፣ ሐምሌ 11 2010

ኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል እርቀ ሰላም ከወረደ በኋላ በዛሬው ዕለት የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመጀመሪያውን የመንገደኞች በረራ ጀመረ። አዣንስ ፍራንስ ፕረስ ከአስመራ እንደዘገበው አውሮፕላኑ አስመራ አየር ማረፊያ ሲደርስ ይጠባበቅ የነበረው ሕዝብ በዘፈን ጭፈራ ብቻ ሳይሆን በእምባም ጭምር ነው የተቀበለው።

Eritrea Asmara erster Linienflug aus Äthiopien eingetroffen

ሁለት አውሮፕላኖች ናቸው ዛሬ ወደ አስመራ የተጓዙት

This browser does not support the audio element.

በሁለቱ ሃገራት መካከል ለ20 ዓመታት ገደማ የተቋረጠው ግንኙነት ከወዲያ እና ወዲህ የሚኖሩ ቤተሰቦችን አለያይቶ ከርሟል። መንገደኞቹን የጫኑት ሁለት አውሮፕላኖች በደቂቃዎች ልዩነት መነሳታቸው ነው የተነገረው። አውሮፕላኑ ዛሬ ከአዲስ አበባ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ሲነሳ የነበረው አሸኛነት የተከታተለው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ተከታዩን ልኮልናል።

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW