የመጀመሪያው የወባ መከላከያ ክትባት በአፍሪቃ ሊሰጥ ነው
ሐሙስ፣ መስከረም 27 2014ማስታወቂያ
የዓለም ጤና ድርጅት የመጀመሪያው የወባ መከላከያ ክትባት ስራ ላይ እንዲውል መፍቀዱን አስታውቋል። በአፍሪቃ ለሚገኙ ህጻናት የሚሰጠው ይህ ክትባት የበሽታውን ስርጭት ለመቀነስ የሚደረገውን ጥረት የማጠናከር ተስፋ ተጥሎበታል። የድርጅቱ ዋና ፀሀፊ ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ክትባቱ ስራ ላይ እንዲውል የተፈቀደበትን ወቅት ታሪካዊ ብለውታል። ድርጅቱ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው ከጎርጎሮሳዊው 2019 አንስቶ በመካሄድ ላይ በነበረ ምርምር በጋና በኬንያ እና በማላዊ ከ800 ሺህ በላይ በሚሆኑ ህጻናት ላይ ከተካሄደ ክትትል በኋላ መሆኑን አስታውቋል።ገበያው ንጉሴ ከብራሰልስ ዝርዝሩን አዘጋጅቷል።
ገበያው ንጉሴ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ