የሙርሌ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት አምስት ሰዎች ተገደሉ
ሰኞ፣ ግንቦት 18 2017
የሙርሌ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት አምስት ሰዎች ተገደሉ
በክልሉ አኙዋ ብሔረሰብ ዞን ውስጥ በሚገኘው ዲማ ወረዳ ትናንት ጠዋት 3 ሰዓት ገደማ ታጣዊዎቹ ባደረሱት ጥቃት ሰዎቹ መገደላቸውን ያነጋገርናቸው የአካባቢው ነዋሪዎች አሰታውቋል፡፡ ጉዳቱ የደረሰው በአንድ የህዝብ ማመላለሻ ባስ ላይ ታጣቂዎቹ በከፈቱት ተኩስ እንደሆነው የወረዳው አስተዳደርም አመልክተዋል፡፡
ታጣቂዎቹ መኪናውን በማስቆም በሁለት አቅጣጫ ጥቃት መሰንዘራቸውን የዲማ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ኡጁሉ ኡማን ተናግረዋል። የሙርሌ ታጣቂዎች ከዚህ ቀደምም በተደጋጋሚ ንብት መዝረፋቸውን የተናገሩት አቶ ኡጁሉ በተለያዩ ወቅቶች በአካባቢው ሚሊሻዎች በሚያደርጉት ክትትል የተዘረፉ ከብች መመለሳቸውን አክልዋል፡፡በጋምቤላ አምስት ስደተኞች ባልታወቁ ሰዎች መገደላቸውን ክልሉ ፖሊስ አስታወቀ
በዲማ ወረዳ የሙርሌ ታጣቂዎች ጥቃት
መነሻቸው ከደቡብ ሱዳን ነው የተባሉት የሙርሌ ታጣቂዎች በአዋኙዋ ዞን ዲማ ወረዳ በተደጋጋሚ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃት እንደሚያደርሱ ያነጋርናቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡ ትናንት ጠዋት ከዲማ ወደ ጎግ ወረዳ ይንቀሳቀስ በነበረው መለስተኛ የህዝብ ማመላለሻ ባስ ላይ ባደረሱት ጥቃት አሽርካሪውን ጨምሮ አምስት ሰዎች ሲገደሉ ስድስት ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን አቶ ጊሎ አቡላ የተባሉ የአካባቢው ነዋሪ ተናግረዋል፡፡
ከታጣቂዎቹ አንዱ በጸጥታ ሐይሎች በመገደሉ የታጣቂዎቹ መነሻ ከደቡብ ሱዳን የተሻገሩ የሙርሌ ታጣቂ መሆናቸው መረጋገጡን ነዋሪ ገልጸዋል፡፡ የወረዳው ሌላው ነዋሪም ጥቃቱ በአንድ ባስ ላይ መድረሱን እና ሰላማዊ ሰዎች መሞታቸውን ተናግረዋል፡፡ ከዚህ ቀደምም በተደጋጋሚ በወረዳው የሙርሌ ታጣቂዎች የቁም እንስሳት በመዝረፍ ወደ ደቡብ ሱዳን እንደሚመለሱ አመልክተዋል፡፡ ባለፈው ሳምንት ውስጥ በወረዳው ገጠራማ ስፍራዎች ላይ ሁለት ጊዜ በሙርሌና ያልታወቁ ሐይሎች ጥቃት መድረሱን ገልጸዋል፡፡በደቡብ ሱዳናውያን መካከል በተከሰተ ግጭት ኢትዮጵያኑ ጉዳት ደረሰባቸው
‹‹ከሙርሌ ታጣቂዎች አንዱ ተገድለዋል፡፡››
በአኙዋ ብሔረሰብ ዞን የዲማ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ኡጁሉ ኡማን ታጣቂዎቹ ደፈጣ ይዞ በህዝብ ማመላለሻ ባስ ላይ ባደረሱት ጥቃት አምስት ሰዎች መገደላቸውን አረጋግጠዋል፡፡ ወረዳው ጠረፋማ በመሆኑ የሙርሌ ታጣቂዎች በተለያየ ወቅቶች ከደቡብ ሱዳን በቀላሉ ወደ ወረዳው በመሻገር ህጻናትን እንደሚያግቱ፣የነዋሪውን ከብትም እንደምዘርፉ ተናግረዋል፡፡ ከሁለት ቀን በፊት ደግሞ በወረዳው አጁዋ በተባለ ቦታ አንድ የሚሊሻ አባል እንደዚሁ ባልታወቁ ሰዎች በደረሰበት ጥቃት መገደሉን አስታውቋል፡፡ የሙርሌዎችን ጥቃት ለመከላል መስመሩ በቋሚነት እንዲጠበቅ ይደረጋል ብሏል፡፡ በጋምቤላ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች በሙርሌ ታጣቂዎች ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የቁም እንስሳትን ከመዝረፍ አልፎ ወደ ከተሞች በመዝለቅ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃት ማድረስ መጀመራቸውን ከዚህ ቀደምም በተደጋጋሚ ተዘግበዋል፡፡ በጋምቤላ ክልል በኮሌራ በሽታ 30 ሰዉ ሞተ፤ ከ1000 በላይ ታመመ
በቅርቡ ግንቦት 13/2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የዳሎል ማዕከላዊ ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጀነራል ዘውዱ በላይ እና የደቡብ ሱዳን መከላከያ ሀይል የፓጋግ አካባቢ አዛዥ ብርጋደር ጀነራል ዋል ዴንግ በጋምቤላ ላሬ ወረዳው በድምበር አካባቢ ጸጥታ ጉዳይ ላይ መምክራቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመለክታል፡፡ ሁለቱ ሀገራትን የሚያዋስኑ ድምበሮች ሰላማዊ ሆነው እንዲቀጥሉ የጸጥታ አካላት የመረጃ ልውውጣቸውን እንደሚያጎለብቱ ሁለቱ የጦር አዛዦች የመከሩ ሲሆን በድምበር አካባቢ ወንጀሎች እና ህገ ወጥ ንግድ እንዳይፈጸም ጥብቅ ቁጥጥርም ይደረጋል ማለታቸው ተመላክቷል፡፡
ነጋሳ ደሳለኝ
አዜብ ታደሰ
ታምራት ዲንሳ