«የሙስሊሙ ማሕበረሰብ የረዥም ጊዜ ጥያቄ ተመልሷል፤ ተደስተናል።»
ዓርብ፣ ሰኔ 5 2012
ማስታወቂያ
ለረጅም አመታት ሲጠየቅ የኖረው የህዝበ ሙስሊሙ የህጋዊነት ጥያቄ ምላሽ ማግኘቱ ደስታ እንደፈጠረለት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ዛሬ በሰጠው መግለጫ ገለጸ።
ጉዳዩ ሃገራዊና የመብት ጥያቄ ነበር ያሉት የምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ዑመር ኢድሪስ መንግስት ከህጋዊነት ጥያቄው ባሻገር የባንክ መመስረት እና የመስጊድ መገንቢያ ስፍራዎች ጭምር የተፈቀዱበትና ለዚህ ጥያቄም ምላሽ ማግኘት ኢትዮጵያዊ ክርስትያኖችም የታገሉበት በመሆኑ ፣ ለሁሉም ምስጋና ይገባል ብለዋል።
ሰለሞን ሙጬ
ታምራት ዲንሳ
አዜብ ታደሰ