የሙስሊሞች ተቃውሞ በአንዋር መስጊድ
ዓርብ፣ ጥር 17 2005ማስታወቂያ
በአዲስ አበባው ታላቁ አንዋር መስጊድ በርካታ ሙስሊሞች ከስግደት በኋላ ዛሬ ከወትሮ በተለየ በብዛት ተሰባስበው ተቃውሞአቸውን ማሰማታቸዉን ወኪላችን አስፍራዉ ገልፆልናል። ሙስሊም ምዕመናኑ ዛሬ ከዚህ ቀደም ያቀርቧቸው የነበሩትን ጥያቄዎችና አዳዲስ መፈክሮችም ያሰሙ እንደነበርም ተመልክቷል። ከሌሎቹ ጊዜያት በተለየ ዛሬ በአካባቢው ብዙ ፖሊሶች በጥበቃ ላይ ተሰማርተው ነበር። በስፍራው የተገኘውን የአዲስ አበባውን ወኪላችንን ስቱድዮ ከመግባቴ በፊት በስልክ አነጋግሬዋለሁ ።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ሂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሰ