የሙታን አያያዝ
ዓርብ፣ የካቲት 13 2007ማስታወቂያ
ምዕራብ አፍሪቃ ውስጥ በባሕላዊ ሥርዓተ ቀብር ወቅት አስክሬኖችን በመሳም፣ በማጠብ አለያም በመንካት በርካታ ሰዎች በተሐዋሲው ሊጠቁ ችለዋል። በኢቦላ የተነሳ ከሞተ ሰው ቢያንስ አንድ ሜትር ያኽል መራቅ ያስፈልጋል።
በኢቦላ ታማሚ ጥቅም ላይ ውለው የነበሩ ፍራሾች፣ ልብሶች እና ሌሎች ቁሳቁሶች በአጠቃላይ የተሐዋሲውን ስርጭት ለመግታት ያስችል ዘንድ መቃጠል አለባቸው።
ሥርዓተ ቀብር መፈፀም ያለበት በሠለጠኑ ባለሙያዎች ነው። ጊኒ፣ ላይቤሪያ እና ሴራሊዮን ውስጥ በ24 ሠዓት የስልክ አገልግሎት ሊጠሩ የሚችሉ ባለሙያዎችን የቀይ መስቀል ድርጅት በልዩ ሁናቴ አሠልጥኗል። እነዚህ ባለሙያዎች ባህላዊ የእንጨት የሬሳ ሣጥኞችን የሚተኩ ማለትም አስክሬኖቹ ተጠቅልለው የሚቀበሩበት አለያም የሚቃጠሉበት ላስቲኮችን ያቀርባሉ። ምንም እንኳን ጥንቃቄ የተሞላበት አያያዝ ለሰዎች እጅግ አስፈላጊ ቢሆንም ሙታንም በክብር ሊስተናገዱ ይገባል። ያም በመሆኑ የጤና ባለሙያዎች ከክርስቲያን እና ከሙስሊም «የክብር ሥርዓተ ቀብር» ዓውድ አንፃርም መሰልጠን ይገባቸዋል።