«የሚመጣዉን ለመቀበል ዝግጁ ነኝ» ልደቱ አያሌዉ
ረቡዕ፣ ግንቦት 2 2015
ማስታወቂያ
እዉቁ የኢትዮጵያ መንግስት ተቃዋሚ ፖለቲከኛ ልደቱ አያሌዉ በቅርቡ መንግስት ያወጀባቸዉን የአሸባሪነት ክስ በአካል ተገኝተዉ ለመሟገት መወሰናቸዉን አስታወቁ።የኢትዮጵያ መንግስት ለሕክምና ዩናይትድ ስቴትስ የሚገኙትን አቶ ልደቱ አያሌዉን ጨምሮ 11 ሰዎችን «የሽብር ፕሮፓጋንዳ በመንዛት፣ የክልልና የፌደራል መንግስትን በኃይል ለመጣል በማሴር ወንጅሏቸዋል። የኢትዮጵያ የፀጥታና ደሕንነት የጋራ ግብረ-ኃይል ባለፈዉ ሚያዚያ 22 ባወጣዉ መግለጫዉ «የሽብር ኃይሎች» ያላቸዉን ሰዎች ለመያዝና ኢትዮጵያ ዉስጥ ለፍርድ ለማቅረብ ተጠርጣሪዎቹ ከሚኖሩባቸዉ ሐገራት የፀጥታ ኃይሎችና ከከዓለም የፖሊስ ድርጅት (ኢንተር ፖል) በጋራ እየሰራ መሆኑን አስታዉቋል።አቶ ልደቱ እንዳሉት ግን ራሳቸዉ ሔደዉ ክሱን ለመጋፈጥ ወስነዋል።ከአቶ ልደቱ ጋር ያደርግነዉን ሙሉ ቃለ መጠይቅ ያድምጡ
ነጋሽ መሐመድ
ሸዋዬ ለገሰ