የሚያዝያ 2 ቀን 2015 ዓ.ም. የስፖርት ዝግጅት
ሰኞ፣ ሚያዝያ 2 2015
ኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ወደ አሜሪካ እንደሚጓዝ ተነገረ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋልያዎቹ በመጭው ሀምሌ ወር ወደ አሜሪካ እንደሚጓዙ ያስታወቀው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሲሆን ቡድኑ ከ 3 ወራት በኋላ ጉዞውን እንደሚያደርግ ፌዴሬሽኑ አስታውቋል ። ዋልያዎቹ በአሜሪካ በሚኖራቸው ቆይታ ከተለያዩ የካሪቢያን ሀገራት ብሔራዊ ቡድኖች ጋር የወዳጅነት ጨዋታ ይኖራቸዋል ቢባልም እነኝህ ቡድኖች እነማን እደሆኑ የተገለፅ ነገር የለም ።
በቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ18ኛ ሳምንት ጨዋታ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ስታድየም ተስተናግል በሳምንቱ መጨረሻ በተደረገው በዚህ ጨዋታ አዳማ ከተማ በ ሀዋሳ ከተማ 2 ለ 0 ተረቷል ። በጨዋታው በመጀመሪያው ግማሽ አብዱልባሲጥ ከማል ከእረፍት መልስ ደግሞ አቤነዘር ኦቴ ቡድናቸው ሀዋሳ ከተማ በጨዋታው ሙሉ ሶስት ነጥ ይዞ ለመውጣት ያስቻሉትን ጎሎች ከረብመሳርፈዋል ሀዋሳ ከነማ በ አዳማ ለይ ያገኘው ድል በፕሪምየር ሊጉ የነበረውን ደረጃን ለማሻሻል አግዞታል በተመሳሳይ ትላንት ጨዋታቸውን በ12 ሰዓት ላይ ያደረጉት ። ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ወላይታ ዲቻ 1ለ1 ተለያይተው ነጥብ ተጋርተው ወጥተዋል ።
18ኛ ሳምንት የሆነውን ቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድር የደርጃ ሰንጠረዥ ቅዱስ ጊዮርጊስ በ39 ነጥብ ሲመራው ባህርዳር ከተማ በ 3 ነጥብ ዝቅ ብሎ በ36 ነጥብ ሁለተኛ ሆኖ ይከተላል። ዛሬ ማምሻውን ተስተካካይ ጨዋታውን የሚያደርገው ኢትዮጵያ መድን በ 33 ነጥብ ሶስተኛ ሆኖ ይከተላል። ሀዋሳ ከተማ በ28 ነጥብ አራተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
አዳማ ከ18ኛ ሳምንት እስከ 22ኛው ሳምንት የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ውድድሮችን ስታስተናግድ ትቆያለች ሲሉ ለ DW የተናገሩት የ ቤት ኪንግ ፕሪምየር ሊግ ኢትዮጵያ ስራስኪያጅ አቶ ክፍሌ ሰይፈ ሲናገሩ፤
ሰሞኑን የተስተዋለውን የአማራ ክልል መንገድ መዘጋት እና የጸጥታ ቸግር ተከትሎ ከአማራ ክልል የመጡት ሁለቱ ቡድኖች ባህርዳር ከተማ እና ፋሲል ከተማ ምናልባት የደጋፊ ድርቅ ይመታቸው እንደሆነ እንጂ የፕሪምየር ሊጉ ውድድሮች ምንም አይነት መስተጎዋጎል ሳያጋጥማቸው ይቀጥላሉ ብለዋል ።
ቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ዛሬ ማምሻውን ሀዲያ ሆሳዕና ከ ድሬዳዋ ከተማ እንደዚሁም ለገጣፎ ለገዳዲ ከ ኢትዮጵያ መድን ጋር በሚያደርጉት ጨዋታ ቀጥሎ ይውላል ።
የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ
በሳምንቱ መጨረሻ በተለያዩ የእንግሊዝ ከተሞች የፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ተካሂደዋል
ትናንት እንደ ግብ ጠባቂው አረን ራምስዴል ባይሆን ወደ ሊቨርፑል ያቀናው የሰሜን ለንደኑ ቡድን አርሰናል በአንፊልድ ሽንፈትን ተከናንቦ ከመመለስ አያመልጡም ነበር ። የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ድረስ በውጥረት የታጀበ የዳጋፊዎቻቸውን ነፍስ ሰቅዞ የያዘ ነበር ።
በ 54ኛው ደቂቃ መሀመድ ሳላይ የሳተውን የፍጠም ቅጣት ምት ጨምሮ የታየው የቢጫ ካርድ ብዛት ለእለቱ ጨዋታ ውጥረት የተሞላበት እንደነበር ምስክር ነበር ። በመጀመሪያው ግማሽ በ 8ኛው ደቂቃ ማርቲኒች በ 28ኛ ደቂቃ ጋብሪላ ጀሱስ ባስቆጠኡት ጎል አርሰናሎች ቀዳሚ ቢሆኑም
መደበኛው የመጀመሪያው ግማሽ የጨዋታ ሰአት ሊጠናቀቅ ሶስት ደቂቃዎች ሲቀሩት ሳላ ከመረብ ባገናኘው ኳስ ሁለቱ ቡድኖች በአርሰናል 2 ለ 1 መሪነት እረፍት ወጡ። ከእረፍት መልስ የሞት ሽረት ትግል ሲያረጉ ቆይተው ፈርሚኒሆ በ 87 ኛው ደቂቃ ባስቆጠረው ጎል ጨዋታው ተጠናቆ ነጥብ ተጋርተው ወጥተዋል።
ከሊቨርፑል ጋር ሜዳ ገብተው የጨዋታው ታዳሚ ባይሆኑም ማንችስተር ሲቲ ፣ አስቶን ቪላ ፣ ብራይተን ጭምር በጨዋታው ነጥብ ጥሎ የሚወጣውን ቡድን በጉጉት ሲጠብቁት ቆይተዋል።
በተቀሩት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ክርስታል ፓላስ ሊድስን በሜዳው 5 ለ 1 ሲረታ ማንችስተር ዪናይትድ ኤቨርተንን አስቶን ቪላ ኖቲንግሀም ፎረስትን በተመሳሳይ 2 ለ 0 ብራት ፈርድ በ ኒው ካስል ብራይተን በቶትንሀን ሁሉም 2ል1 ተረተዋል ዎልቨር ሀፕተን ቸልሲን 1 ል0 ማንችስተር ሲቲ ሳውዝ ሀምፕተንን 4 ለ1 ረትተዋል።
የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ን ትላንት ነጥብ ተጋርቶ የወጣው አርሰናል በ 73 ነጥብ ሲመራው አንድ ተስተካካይ ጨዋታ የሚቀራቸው ማንችስተር ሲቲ በ 67 ነጥብ ሁለተኛ ኒውካስል ዪናይትድ እና ማንጭስተር ዩናይትድ በግብ ክፍያ ተላያይተው በ 56 ነጥብ ሶስተኛ እና 4 ደረጃ ላይ ይገኛሉ ነቲግሀም ፎረስት ሊስተር ሲቲ እና ሳውዝ ሀምፕተን እንደቅደም ተከተላቸው ከ 18 እስከ 20 ያለውን ደረጃ ይዘዋል።
የጀርመን ቡንደስ ሊጋ የቅዳሜ እና እሁድ ውሎ
ቦሪስያ ዶርቱመንድ ቮልፍስ ቨርግ ን 2ለ0 ሲረታ
ሆፊንሀም ሻልካን በተመሳሳይ 2 ለ 0 አእሽንፎዋል ማይንዝ እና ቪደር ብሪመንን 2 ለ 2ተለያየተው ነጥብ ተጋርተው ወጥተዋል ቫየር ሊቨርኩሰን ፍራንክፈርትን 3 ለ 1 ቦሪሲያ ዶርቱመንድ ኦኘን በርሊንን 3 ለ2 ለ1 ሲያሸንፉ
አጉስ በርግ በ ኮለን 3 ለ 1 ሀርታ በርሊን በ ሊፕዚንግ 1 ለ 0 ተረተው ነጥብ ጥለው ወጥተዋል። ባየር ፍራይበርኝ 1 ለ 0 ረትቷል።
27 ሳምንት የያዘውን የቡንዲስ ሊጋውን የደረጃ ሰንጠረዥ ባየር ሙንሺን በ58 ነጥብ ሲመራ በሁለት ነጥብ ዝቅ ብሎ ቦሪሲያ ዶርቱመንድ በ 56 ነጥብ ሁለተኛ ሆኖ ይከተላል። ኡንየን በርሊን በ 51 ነጥብ ሶስተኛ ሊፕ ዚንግ በ 48 ነጥብ 4 ኛ ነው።
በስፓኒሽ ላሊጋ
ማዮካ እና ሮያል ቫላዶሊድ 3 ለ 3 ተለያይተዋል ። አትሌቲኮ ማድሪድ ሮያል ቮልካኖን በሜዳው 2 ለ1 ረትቷል። ሮያል ሶሲዳድ ጌታቬን 2ለ0 ሲረታ ሪያል ማድሪድ በ ቪላሪያል 3 ለ 2 ተረትቷል።
በላሊጋው የ 28 ኛ ሳምንት ጨዋታ ተስተካካይ ጨዋታውን ዛሬ የሚያደርገው ባርሲሎና በ 71 ነጥብ ሲመራው ቅዳሜ እለት ነጥብ የጣለው ሪያል ማድሪድ በ 59 ነጥብ 2 ኛ አትሌቲኮ ማድሪድ በ57 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
ሃና ደምሴ
ታምራት ዲንሳ