1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የማህበራዊ መገናኛ ዘዴ አጠቃቀም ያስነሳዉ የሕግ ጥያቄ በኢትዮጵያ

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 9 2017

ከሰሞኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ የኢትዮጵያውያንን ባህል፣ ኃይማኖትና ወግ የሚፀረር መልዕክትና ምስል በማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎች አሰራጭቷል ያለዉን ግለሰብ በቁጥጥር ሥር አውሎ እየመረመረ መሆኑን አስታውቋል

የአዲስ አበባ ፖሊስ እንዳስታወቀው ግለሰቡ በጎዳናዎች ላይ የተለያዩ አፀያፊ በተለይም የሴቶችን ክብር የሚነካ ኢ-ሞራላዊ ድርጊቶች በመፈፀም የቀረፃቸውን ምስሎች አሰራጭቷል
የአዲስ አበባ ፖሊስ የኢትዮጵያውያንን ባህል፣ ኃይማኖትና ወግ የሚፀረር መልዕክትና ምስል በማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎች አሰራጭቷል ያለዉን ግለሰብ በቁጥጥር ሥር አውሎ እየመረመረ መሆኑን አስታውቋልምስል፦ Solomon Muchie/DW

የማህበራዊ መገናኛ ዘዴ አጠቃቀም ያስነሳዉ የሕግ ጥያቄ በኢትዮጵያ

This browser does not support the audio element.

 

ከሰሞኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ የኢትዮጵያውያንን ባህል፣ ኃይማኖትና ወግ የሚፀረር መልዕክትና ምስል በማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎች አሰራጭቷል ያለዉን ግለሰብ በቁጥጥር ሥር አውሎ እየመረመረ መሆኑን አስታውቋል።ፖሊስ እንደሚለዉ ሚሊዮን ድሪባ የሚባል ግለሰብ በተለያዩ የማህበራዊ መገኛ ዘዴዎች ያሰራጫቸዉ  ተንቀሳቃሽ ምስሎች በህብረተሰብ ዘንድ ቅሬታ አስከትሏል።የኢትዮጵያ የወንጀለኛ መቅጫ  ህግ “ፀያፍ” ያለውን ድርጊት ፈፅሟልም።ሥዩም ጌቱ ከአዲስ አበባ።

 

የአዲስ አበባ ፖሊስ እንዳስታወቀው ግለሰቡ በጎዳናዎች ላይ የተለያዩ አፀያፊ በተለይም የሴቶችን ክብር የሚነካ ኢ-ሞራላዊ ድርጊቶች በመፈፀም የቀረፃቸውን ምስሎች በመልቀቅ በፈፀመው ህገ ወጥ ተግባርና በለቀቀው ተንቀሳቃሽ ምስል በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ እንደሚገኝ ፖሊስ ገልጿል።በአንዳድ ማህበራዊ ሚዲያዎች የሚለቀቁ አንዳንድ ምስሎች ተገቢነታቸውን የሳቱና ያፈነገጡ እየሆኑ መምጣታቸውን ፖሊስ ገልፆ ህገ ወጥ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን በሚለቁ ግለሰቦች ላይ የሚወስደውን ህጋዊ እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።   

ሥዩም ጌቱ

ነጋሽ መሐመድ

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW