የማሊ ዳግም ግንባታ ጉባኤ
ረቡዕ፣ ግንቦት 7 2005ማስታወቂያ
በርስ በርስ እና በዉጪ ጣልቃ ገብ ጦር ዉጊያ፥ በመፈንቅለ መንግሥትና በፖለቲካ ሽኩቻ የወደመችዉ ማሊን መልሶ ለመገንባት የሚያስፈልገዉ ገንዘብ የተዋጣበት ዓለም አቀፍ ጉባኤ ዛሬ ብራስልስ-ቤልጂየም ዉስጥ ተካሒዷል።በጉባኤዉ ላይ የአስር ሐገራት መሪዎች፥ የአንድ መቶ ሠወስት ሐገራት እና ድርጅቶች ተወካዮች ተካፍለዋል።በርካታ ገንዘብ ተዋጥቷል።ጉባኤዉ ያዘጋጁት የማሊ አማፂያንን የምትወጋዉ፥ የቀድሞዋ የማሊ ቅኝ ገዢ ፈረንሳይ እና የአዉሮጳ ሕብረት ኮሚሽን ናቸዉ።በጉባኤዉ ላይ እንደተገለፀዉ ምዕራብ አፍሪቃዊቱን ሐገር መልሶ ለመገንባት አራት ቢሊዮን ዩሮ ያስፈልጋል።የብራስልሱ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴ ዝር ዝር ዘገባ ልኮልናል።
ገበያዉ ንጉሴ
ነጋሽ መሐመድ
አርያም ተክሌ