1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ለወጣቶች የሚሰጡት ጥቅምና ጉዳት

ዓርብ፣ ሚያዝያ 17 2017

በበርካታ የመገናኛ ዘዴ መተግበሪያዎች የሚሰራጩ ይዘቶች ጠቃሚ የመሆናቸውን ያህል ቀለል ያሉና እምብዛም ይዘቶቻቸው ጠንካራ መልእክት የማያስተላልፉ ይዘቶች በርካታ እይታን ስያገኙም መመልከት እንግዳ ነገር አይደለም፡፡

በኢትዮጵያ የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች አጠቃቀም የሕብረተሰቡን ባሕል፣ ኃይማኖትና ወግ የሚፀራሩ ይዘቶች በተለይም በወጣቱ የማህበረሰብ ክፍል ዘንድ በስፋት እየተሰራቹ መሆናቸዉ እየተነገረ ይገኛል
በኢትዮጵያ የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች አጠቃቀም የሕብረተሰቡን ባሕል፣ ኃይማኖትና ወግ የሚፀራሩ ይዘቶች በተለይም በወጣቱ የማህበረሰብ ክፍል ዘንድ በስፋት እየተሰራቹ መሆናቸዉ እየተነገረ ይገኛልምስል፦ imago/Schöning

የማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ለወጣቶች የሚሰጡት ጥቅምና ጉዳት

This browser does not support the audio element.

ከሰሞኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ ከኢትዮጵያውያን ባህል፣ ኃይማኖትና ወግ የሚቃረኑ በርካታ ምስሎችን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ያሰራጨን ግለሰብ በቁጥጥር ስር አውሎ በምርመራ እያጣራ እንደሚገኝ ማሳወቁ ይታወሳል።እንደ ፖሊስ መግለጫ ግለሰቡ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች የሚለቃቸው ተንቀሳቃሽ ምስሎች በህብረተሰብ ዘንድ ቅሬታን ማስነሳቱና ከቅሬታውም ባሻገር የኢትዮጵያ የወንጀል ህግ “ፀያፍ” ያለውን ድርጊት በመፈፀም ወንጀልም ተጠርጥሯል።

መሰል ተግባራት በኢትዮጵያ ማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች አጠቃቀም ላይ በተለይም በወጣቱ የማህበረሰብ ክፍል ዘንድ በስፋት እየተስተዋለ ስለመሆኑም እየተነገረ ይገኛል፡፡
ለመሆኑ የአንድ ማህበረሰብ መገለጫ የሆነው ባህል፣ ሃይማኖትና እሴቶቹ በመጠበቅ ረገድ የማህበራዊ ሚዲያዎች አጠቃቀም ምን ጥላ አጥልቷል? ማህበረሰቡ በጥንቃቄ የሚያቸውን እነዚህን እሴቶች መጠበቅስ ፋይዳው ምን ይሆን?

ሰመረ ካሳዬ (በብዙዎች በማህበራዊ ሚዲያ ሰመረ ባሪያዉ) በሚል ስሙ በተለይም ማህበራዊ የመገናኛ ዜዴዎች ላይ የማህበረሰቡን እሴትና ባህልን ተቃርነው የሚለቀቁ ይዘቶችን ጨምሮ የማህበረሰቡን የግንዛቤ ደረጃ “አይመጥኑም” ባላቸው ጉዳዮች ላይ በሚሰጣቸው ሂስ ይታወቃል፡፡ ሰመረ የህግ ባለሙያ ሲሆን መጽሃፍትን በመድረስና በቴሌቪዥን ጣቢያዎች ላይ በሚያቀረብቸው ፕሮግራሞችም ይታወቃል፡፡
የማህበራዊ ሚዲያ ይዘት ከማህበረሰቡ እሴት አኳያ ሲቃኝ

ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ንቁ ተሳትፎን የሚያደርገው ሰመረ ከማህበረሰቡ አመለካከት አኳያ የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች አጠቃቀምን በተመለከተ ትዝብቶቹን እንዲያጋራን ጠይቀነዋል፡፡ በአስተያየቱም በማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ላይ በተለይም በወጣቶች ዘንድ የሚስተዋለው ማህበረሰቡ የማይፈልጋቸው ወይም ከማህበረሰቡ ባህልና እሴት ውጪ የሆኑ ይዘቶች እየተበራከቱ ለመምጣታቸው ሊወቀስ የሚገባው አንዱና ቀዳሚው ነገር በማህበረሰቡ በራሱ የያገባኛል ስሜት እየተቀዛቀዘ መምጣቱ ነው ይላል፡፡ “ጉዳዩን ለማብራራት የተለየ ሙያተኛ መሆንም ያስፈልጋል ብዬ አላምንም” የምለው ሰመረ፤ የነበረን ባህል የተጠበቀው ማህበረሰቡ ውስጥ አርዓያ የሆኑና ንቁ ሆነው ማህበረሰቡን የቀረፁ ሰዎች የመኖራቸውን ያህል አሁን አሁን ግን የነሱ አይነት ነገሮች መላላት፤ ከማህበረሰቡ እሴት ውጪ የሆኑ ይዘቶችን የሚለቁ ሰዎች ምንም ሳይባሉ፣ ተጠያቂም ሳይደረጉ የመታለፋቸው ጉዳዩ ችግር እየሆኑ መጥተዋል የሚል አስተያየቱን አስቀምጧል፡፡
“የህዝቡን ሞራል (እሴት) የሚቃረኑ የሚስነውሩ ድርጊቶችን ማድረግ በኢትዮጵያ ወንጀል ህግም ተካቷል” የሚለው ሰመረ መሰል ይዘቶች ከማህበሰብም ዘንድ የተወገዘ እንደመሆኑ ሊወገዝ እንደሚገባው ነው የሚገልጸው፡፡ ከማህበረሰቡ ፍላጎትና እሴት ውጪ ለሆኑ ይዘቶች መሰራጨት አንዳንዴ የእውቀትና ግንዛቤ ማነስ እንዳለ ሆኖ አንዳንዴ ደግሞ ሆን ተብሎ የሚደረግ ተግባርም እንደሆነም ያነሳል፡፡
የማህበረሰቡ የያገባኛል ተሳትፎ አስፈላጊነት
በቅርቡ ከኢትዮጵያ ማህበረሰብ እሴት ውጪ የሆነን አንድ በማህበራዊ ሚዲያ የተለቀቀን ተንብቀሳቃሽ ምስል የተቸበት ቪዲዮ በመስራቱ ያ ቪዲዮ በ24 ሰዓት ውስጥ ከገጹ መወገዱን የሚገልጸው ሰመረ፤ ከማህበረሰቡ ማንነትና እሴት የሚነካን ጉዳይ ለመታገል የማህበረሰቡ የያገባኛል ተሳትፎና የህግ አካላት ትኩረት እጅጉን ወሳኝ መሆናቸውንም በአስተያየቱ ያነሳል፡፡ “የሚመለከተውም አካል ትኩረቱን የነፈገውና ማህበረሰቡም በግል ህይወቱ ላይ ብቻ በማተኮሩ የማህበረሰቡን እሴት ሚጎዱ ስር እየሰደዱ የመጡ ከማህበረሰቡ ባህል ማንነት ውጪ የሆኑ ጉዳዮች በሚገባው መተቸት ሲገባቸው አልተተቹም” የሚለው ሰመረ፤ መሰል አዝማሚ ያላቸውን ይዘቶች በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያ መተግበሪያዎች መታዘቡንም አስረድቷል፡፡ 

ከማህበረሰቡ ፍላጎትና እሴት ውጪ ለሆኑ ይዘቶች መሰራጨት አንዳንዴ የእውቀትና ግንዛቤ ማነስ እንዳለ ሆኖ ሆን ተብሎ የሚደረግ ተግባርም እንደሆነም ይታመናልምስል፦ Weronika Peneshko/dpa/picture alliance

“አብዛኛውን ማህበረሰብ የሚወክለው ጨዋነቱ ይከበር የሚልን ይዘት ተባብሮ እስከ ማስወረድ የሚዘምቱ የተደራጁም አካላት በማህበራዊ ሚዲያው አሉ” በማለትም ትልቁን ክፍተት የሚፈጥረውም የማህበረሰቡ ዝምታ ነው ሲል አስተያየቱን አክሏል፡፡ “የህግ አካላትም ለመሰል በጉዳዮች ቅድሚያውን መስጠት አለበት” በማለት “እያየን እንዳላየ ማለፉ” መቆም አለበት ሲል ከብዙሃን ፍላጎትና ፋይዳ ውጪ የሆኑ ይዘቶች እየተወገዙ መሄድ እንዳለባቸውም በአስተያየቱ ያስረዳል፡፡ 
የማህበራዊ መገናኛ ዜዴዎች ማህበረሰቡን በአሉታዊም ሆነ በአዎንታዊው ከመገንባት አኳያ ትልቁን ሚና እንደሚጫወቱም የሚያስረዳው ባለሙው፤ የማህበራዊ ሚዲያ ላይ ቴክኖሎጂ ስመጣ ለበጎ ዓላማ ቢሆንም በአሉታዊነት ጥቅም ላይ ስውሉ ግን የሚስከትሉት ጉዳት ከትቅማቸው ልልቅ እንደሚችልም አመልክቷል፡፡ በርካታ የማህበረሰብ ክፍሎች በተለይም ደግሞ ወጣቶች እና ታዳጊዎች የማህበራዊ ሚዲያ ጥገኛ በሆኑበት ባሁን ወቅት በማህበፈራዊ ሚዲያ የሚሰራጩ ይዘቶች በአላስፈላጊ መንገድ ትውልዱን እንዳይመሩ የማህበረሰቡ ንቁ ተሳትፎ በእጅጉ እንደሚያስፈልግም ያነሳል፡፡ 
በማህበራዊ ሚዲያ ጠንከር ያሉ ይዘቶች በበርካቶች ለምን አይመረጡም?
በበርካታ የመገናኛ ዘዴ መተግበሪያዎች የሚሰራጩ ይዘቶች ጠቃሚ የመሆናቸውን ያህል ቀለል ያሉና እምብዛም ይዘቶቻቸው ጠንካራ መልእክት የማያስተላልፉ ይዘቶች በርካታ እይታን ስያገኙም መመልከት እንግዳ ነገር አይደለም፡፡ ቴክኖሊጂ ለሁሉም ሰው የመረጃ አቅራቢነት እድል መስጠቱ መልካም አጋጣሚ ቢሆንም ፈተናዎችም ግን እንዳሉት የገለጹት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጤኝነት መምህር ዮሓንስ ሽፈራሁ (ዶ/ር) ይህን ክፍተት በህግ ብቻ ተከታትሎ መቆጣጠር ግን ቀላል እንደማይሆን ያስረዳሉ፡፡ “ማንኛውንም ይዘት ለማዘጋጀት በጣም ቀላል መሆኑ ሁሉም ሰው ይዘት ይዘው እንዲቀርቡ አስችሏል” ያሉን ዶ/ር ዮሓንስ ይህ በነበረው አሰራር በጋዜጠኝነት ሙያ በብዙ ዝግጅ በሚወጡት መረጃዎች ደረጃ እንደማይሆኑ እሙን ቢሆንም ያንን ደረጃ መጠበቅ አሁን ከባድ እንደሚሆን አስረድተዋል፡፡ አንዳንዴም “ከቀይ መስመር” ውጪ የሚሆኑትን ይዘቶች አቅራቢው በህግ ተጠያቂ እንዲሆን ማስደረግ ብቻልም በዚህ ብቻ ግን ዘላቂ እልባት ማምጣት እንደማይቻልም ገልጸዋል፡፡ ይህም በሚዲያ ይዘቶች ዙሪያ ሚዲያው የሚያሳድረው ተጽእኖ ዙሪያ ለትውልዱ በየደረጃው ስልጠናዎችን መስጠት ነው ብለዋል፡፡

ለማህበራዊ ሚዲያው ቅርበት ያለውናየተለያዩ ሂሶችን በማቅረብ የሚታወቀው ሰመረ ካሳዬም በዚህ ላይ የሰጡት አስተያየት ተቀራራቢ ቢሆንም የማህበረሰቡ ተሳትፎ ግን መጉላት እንዳለበት አጽእኖት ሰጥተዋል፡፡ “ችግሩን ህግ በማስከበር በሚለው ብቻ የምትከላከለው አይደለም” የሚለው ሰመረ የምህበረሰቡ የነቃ ተሳትፎ፣ የሚዲያ አስተዳዳሪ አካል ክትትል እና አላስፈላጊ ይዘቶችን አለማበረታታት ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እጅጉን ትኩረት የሚሹም ናቸው ሲል አስተያየቱን አክሏል፡፡

በማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎች በተለይም ዩቱብና ቲክቶክን በመሰሉት የሚሰራጩ ቪዲዮዎች የሕብረተሰቡን አስተሳሰብ፣ ባሕልና ወቅግ እንዳይፃረሩ ለማድረግ ከሕግ ተጠያቂነት ባሻገር የሕብረቱሰቡ ተሳትፎ እንደሚያስፈልግ ባለሙያዎች ይመክራሉምስል፦ CFOTO/picture alliance

ከህግ አኳያም ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ እና ማህበራዊ ሃላፊነትን በሚዛን ላይ ማስቀመጥ እጅጉን አስፈላጊ ነው በማለት አስተያየታቸውን ያጋሩን በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የህግ መምህርና ባለሙያ የሆኑት በፍቃዱ ድሪባ፤ አስፈላጊ ሲሆን የህግ ካርድን መምዘዙ አስፈላጊና አስተማሪ እንደሚሆን አመልክተዋል፡፡ “አንድ ግለሰብም ሁን ቡድን በመንገድ ላይ በስብሰባም ይሁን በየትኛውም ቦታ እራሱን ሃሳቡን የመግለጽ መብት በህገምንግስቱ የተቸገረ ቢሆንም ያ ግን ልዩ ከምንለው ውጪ መሆን አይገባውም” ነው ያሉት፡፡ ሰዎች ወይም ቡድኖች እራሳቸውን በሚግልጹበት ሰዓት ሃሳቦችን የማራማድ ገደቦች እንዳለ መገንዘብ ገባል ነው ያሉት፡፡ ይህ “አብሶሉት ራይት” የምንላቸው አይደሉም ያሉት ባለሙያው “በሚዲያ የሚሰራጩ ማንኛውም ይዘት የማህበረሰቡን እሴት እንዳይጣረዙ የሚመለከተው የመንግስት አካል እነዚህን ሁለት ጉዳዮች ሚዛናዊ በሆነ መልኩ መጠየቅ ይገባዋልም” ብለዋል፡፡

ሥዩም ጌቱ

ነጋሽ መሐመድ
 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW