የማኅበረሰብ አቀፍ ጤና መድኅን አገልግሎት በአማራ ክልል
ሰኞ፣ ነሐሴ 12 2017
በአማራ ክልል ከ 3.6 ሚሊዮን በላይ እማውራና አባውራዎችን የማኅበረሰብ አቀፍ ጤና መድኅን አገልግሎት ተጠቃሚ ማድረግ ተቻለ በቤተሰብ ደረጃም 15 ሚልየን አባላትን ማፍራት ተችሎል። የክልሉ ጤና ቢሮ የማኅበረሰብ አቀፍ ጤና መድኅን ሥራ በማኅበረሰቡ ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት ያገኘ መሆኑን ተገልፆል በ2017 በጀት ዓመት ብቻ 5.6 ቢሊዮን ብር በላይ ሃብት ማሰባሰብ ተችሏል ። ከ12 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ የኅብረተሰብ ክፍሎች በጤና ተቋማት ተገኝተው በጤና መድኅን አገልግሎት ካርዳቸው የሕክምና አገልግሎት ማግኘት ችለዋል። ይሁን እንጂ ተገልጋዮች አገልግሎቱ የመድኃኒት አቅርቦት ላይ ሰፊ ችግር አለበት ይላሉ።
የደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በ2017 ዓ/ም አገልግሎት ከሰጣቸው 650,000 በላይ የህክምና ተገልጋዮች 80 በመቶዎቹ የጤና መድህን አገልግሎት ተጠቃሚዎች ናቸው፡፡ በሆስፒታሉ ቅጥር ግቢ ውስጥ ህክምና እየተከታተሉ ያገኘናቸው ተገልጋዮችም በጤና መድህን አገልግሎት አስፈላጊውን ህክምና እያገኙ መሆናቸውን ይገልፃሉ፡፡
‹‹የሚሰጡት አገልግሎት ጥሩ ነው፡፡ ያለውን ነገር እንጠቀማለን፤ አንዳንድ መድሃኒቶችም ይሰጡናል፡፡ ብዙ ጊዜ ግን ካርድ ላይ የምንጠቀምበት፡፡›› የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ህክምና አገልግሎት ተጠቃሚዎች እንደሚያነሱት በሆስፒታሎች ምርመራ ተኝቶ መታከሚያ ክፍል ማግኘት ጨምሮ የተወሰኑ መድሃኒቶችን በሆስፒታሎች የመድሃኒት መሸጫ ፋርማሲ ውስጥ ለነፃ ለመጠቀም ብንችልም አብዝሃኛውና ውድ የሚባል መድሃኒትን ግን በጤና መድህን አባልነት ማግኘት አይቻልም ይላሉ፡፡ ‹‹የጤና መድህን ካርድ ለማውጣት፣አልጋ ለመያዝ ካልሆነ በስተቀር መድሃኒት ውጭ ላይ ነው የምንገዛው የራስ ምታት መድሃኒት ብቻ ነው የምናገኘው ከባድና ውድ መድሃኒቶችን ከውጭ ነው የምንገዛው›› አወዛጋቢው የወሎ ተርሸሪ ኬር ሆስፒታል ግንባታ
በክልሉ 2.6 ቢልየን ብር ለጤና መድኅን ታካሚዎች ወጭ ሆኖል
የማህበረሰብ ጤና መድህን አገልግሎት ስላለ ወደ ህክምና ማዕከላት የመምጣት ልምዱ ጨምሯል የሚሉት የደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር ሐይማኖት አየለ ናቸው፡፡
‹‹ደሴ ሆስፒታል በ5 ዞን በ2 ክልል 59 ወረዳዎች የጤና መድህን አገልግሎት ውለታ ወስደን እንሰራለን፤ የጤና መድህን አገልግሎት አሁን እየተለመደ ነው፡፡ የጤና ሽፋን በማግኘቱ ብቻ የሆስፒታሉ ታካሚ ቁጥርም ጨምሯል፡፡ ›› የጤና መድህን አገልግሎት ፈተና የሆነው መድሃኒትን ለአባላቱ የማቅረብ ችግር በደሴ ሪፈራል ሆስፒታልም የሚታይ ሲሆን ከኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ ድርጅት ውጭ የሚመጡ መድሃኒቶችን ገዝቶ ለማቅረብ መድሃኒት ላይ ያለው የዋጋ ጭማሪ እንቅፋት ሆኗል ይላሉ፡፡ ደሴ ከተማ ደሞዝ ይጨመርልን አደባባይ የወጡ የህክምና ባለሞያዎች ታሰሩ
15 ሚልየን ሰዎች የጤና መድኅን አገልግሎት ቡክልሉ ያገኛሉ
‹‹ችግራችንም እሱ ነው መድሃኒት አቅርቦት ብቸኛው በፌዴራልም የሚታወቀው የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ ድርጅት ነው፡፡ በእሱ በኩል ያለው ምንም የሚቀረን የለም፡፡ አሁን ጨረታ ስናወጣ ጊዜያዊ የዋጋ ንረት አውጥተን የማናገኛቸው መድሃኒቶች አሉ፤ ግልጽ ጨረታ አውጥተን የመጀመሪያ አሸናፊ ስንጠይቀው አላቀርብም፤ ዋጋ ጨምሯል ይላል፡፡ ከማቅረብ ይልቅ ሲፒኦ እንድንወርስ የሚፈልጉ አቅራቢዎች ነው ያሉት፡፡›› በአማራ ክልል ዘንድሮ 3.6 ሚሊየን በላይ እማወራና አባወራዎች የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አገልግሎት አባላት ሲሆኑ 5.6ቢሊየን ብር በላይ የአባልነት ክፍያ ተሰብስቧል፡፡ በተመዘገቡ የጤና ተቋማት ህክምናቸውን እየተከታተሉ አባለቱም በተሰጠ አገልግሎት 2.6 ቢሊየን ብር ክፍያ ፈጽሟል ይላሉ፡፡ የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ክሽን ወልዴ፡፡
‹‹ማኅበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን በክልላችን ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው አባላት ይዞ እየሰራ ነው በዚህ ዓመትም 3.6 ሚሊየን አባወራና እማዎራዎችን በቤተሰብ ደረጃ 15 ሚሊየን አባላት ማፍራት ተችሏል፡፡ ከአባላቱም 5.6 ቢሊየን ብር ተችሏል፡፡ ›› አሁን ላይ በክልሉ እየተሰጠ ላለው የማህበረሰብ ጤና መድህን አገልግሎት እንቅፋት የሆነን የመድሃኒት እጥረት ለመፍታት 52 አዳዲስ የማህበረሰብ አቀፍ መድሃኒት ቤቶችን ተከፍተው አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ ተብሏል፡፡
‹‹አንዱ የሚነሳው የመድሃኒት እጥረት ነው እሱን ለመፍታት ደግሞ የክልሉ ጤና ቢሮ የማህበረሰብ አቀፍ መድሃኒት ቤቶችን ከ52 በላይ በተለያዩ አካባቢዎች ከፍቶ የግብዓት አቅርቦት ስራ እየተሰራ ነው፡፡ ይህ ጅምር ነው፤ በሁሉም አካባቢ ቢያንስ በወረዳ ከ2 እስከ 3 እንዲኖር እየተሰራ ነው ትልቁ አላማችን ግን የመንግስት ተቋማት ላይ ግብዓት ለማሟላት ሥራ እየሰራን ነው፡፡›› በአማራ ክልል የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አገልግሎት 16 በመቶው እድገት ማሳየቱን እና 80 በመቶ የክልሉ ሽፋን መድረሱ ተገልጿል፡፡
ኢሳያስ ገላዉ
አዜብ ታደሰ
ታምራት ዲንሳ